ተአምረ ማርያም - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Sunday, May 24, 2020

ተአምረ ማርያም


- እግዚአብሔር ያክብራችሁ መላአክትም ጻድቃንም ምስጋናዋን መፈጸም የማይቻላቸው የእመቤታችንን ተአምር ለመስማት ዓይነ ልቡናችሁን ያብራላችሁ፡፡ በርካታ ልመናዋ ከሕዝበ ክርስትያኑ ጋር ለዘላለሙ ይኑር፡፡
-   ከተአምር አስቀድሞ ይህ ይነበብ ሕዝቡም እዝነ ልቡናቸውን ከፍተው ይስሙ ፡፡ በዕብራይስጥ ማርያም የምትባል የእመቤታችንን ክብሯንና ልዕልናዋን ምስጋናዋን በልቡናቸው አስፍት አኑሩት፡፡
- ማርያም ማለት መንግስተ ሰማይ መርታ የምታስገባ ማለት ነው፡፡ እመቤታችን ማርያም ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ልቡና ታስባ ትኖር ነበር፡፡ ፍጥረት ሁሉ እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጠረ አዳምና ሔዋንም እመቤታችን ከነሱ ልትወለድ ተፈጠሩ፡፡ አዳምም እመቤቴን ማርያም ከሱ አብራክ እንድትካፈል ከሔዋንም ማኅፀን እንድትወለድ አውቆ ሔዋንን ሕይወቴ ነሽ ይላት ነበር፡፡ የእመቤታችንን ክበሯ ምስጋናዋ ሁሉ ተጽፎ ቢሆን ምን ብራና በቻለው ነበር፡፡ ሊሰማው የሚችለው ምን ጆሮ ነው፡፡ ሊወስነው የሚችለውስ ምን ልብ ነው፡፡ አስቦ ሊደርሰውስ የሚቻለው እንደምን ያለ ሕሊና ነው፡፡ ነገር ግን የተቻለንን ያህል ከምስጋናዋ ጥቂት እንነግራችኋለን፡፡


እመቤታችን ማርያም ከአዳም ጀምሮ እስከ አብርሃምና እስከ ሙሴ ድረስ ትነገር ነበር፡፡ከሙሴ ጀምሮ እስከ እሰይ ልጅ እስከ ዳዊትም ድረስም በብዙ ምሳሌ እየታየች ትነገር ነበር፡፡ የእመቤታችን ትውልዷ ባቧቷ በኩል ከንጉሡ ከዳዊት ወገን ነው በናቷ በኩል ከሊቀ ካህናቱ ከአሮን ወገን ነው፡፡ የአባቷ ስም ኢያቄም ነው የእናቷም ስም ሐና  ነው፡፡ ሥጋዊ ነገር ከማሰብ መጠበቅ ከአዳም ልጆች ለማን ተሰጠው፡፡ ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ በመላእክትስ እንኳን አልተቻላቸውም ፡፡ በቀደመው ወራት ያልተሰጣቸውን ሽተው በድለው ከሰማይ ወደ ምድር ወርደዋልና፡፡ እንደ እመቤታችን እንደ ማርያም የአብ ማረፊያ የሆነ ማነው፡፡ እንደ እመቤታችን እንደ ማርያም የወልድስ ማደሪያ የሆነ ማነው፡፡ እንደ እመቤታችን ማርያም የመንፈስ ቅዱስ ቤት የሆነ ማነው፡፡ ለሰው ኃጢአት ሣይሠራ መኖር ይቻለዋልን ከአራቱ ባሕሪያት ከተፈጠረ ሰው ከመቤታችን በቀር እሳትን የተሸከመ ኃጢአትንም ያልሰራ የለም እመቤታችን ማርያም ከመላእክት ይልቅ ንፅሕት ናት እመቤታችን ማርያም ከሴቶች ሁሉ ትበልጣለች፡፡ የመቤታችን ማርያም አሳብ እንደ አምላክ አሳብ ነው፡፡ የእመቤታችን ማርያም መልኳ እንደ አምላክ መልክ
ነው፡፡ የአምላክን መልክ ይመስላል፡፡ እመቤችን ማርያም ንጽሕት በመሆኑዋ አምላክን እንዲያድባት አደረገችው፡፡ እመቤታችን ማርያም ለአምላክ የደስታ ማደሪያ ሆነችው፡፡ እመቤታችን ማርያም አምላክን በድንግልናዋ ወለደችው፡፡ እመቤታችን ማርያም በነቢያት ትነገር ነበር፡፡ እመቤታችን ማርያም በሐዋርያትም ትነገር ነበር፡፡ እመቤታችን ማርያም በፍጥረት አንደበት ትመሰገናለች የቤተክርስቲያን ልጆች አክብሯት ለናንተ ለኃጥአን መድኃኒታችሁ ስለሆነች ፡፡ በጎ አገልግሎትም ለሚያገለግሉት ዋጋውን ትሰጠዋለች ሳትጠራጠሩ በፍጹም ልቦናችሁ እመኑባት እሷ መድኃኒታችሁ ናትና፡፡ በሥዕሏ ፊት ስገዱ ለሥዕሏም ያልሰገደ ግን ከቆመበት ቦታ ይጥፋ ስም አጠራሩም አይታወቅ፡፡ በሰማይ ያሉ መላእክትም ይደረግ ይሁን ይበሉ፡፡ እሰግድ ለኪ እሰግድ ለኪ እሰግድ ለኪ ፡፡
እግዚአብሔር ካንቺ ሰው ሆኖ ሙሽራ ከጫጉላው እንዲወጣ ካንቺ የወጣ እመቤቴ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ ብሎ ዮሐንስ አፈወርቅ በድርሳኑ እንዳመሰገነሽ እኔም አመሰግንሻለሁ ፡፡ የጠፋ በግ አዳምን የፈለገው ባገኘው ጊዜ የተሸከመው እውነተኛ ቸር ጠባቂችን ክርስቶስ ካንቺ የተወለደ እመቤቴ ማርይም ሆይ ደስ ይበልሽ ፡፡እግዚአብሔር በብሩህ ደመና ተጭኖ መጥቶ በማኅፀንሽ ያደረ እመቤቴ ማረያም ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ በቅዱሳን ነቢያት በቅዱሳን መላእክት አድሮ የሚኖር ካንቺ ተወልዶ የተገለጸልን እመቤቴ ማርይም ሆይ ደስ ይበልሽ ፡፡ በቅዱሳን ነቢያት በቅዱሳን መላእክት አድሮ የሚኖር ካንቺ ተወልዶ የተገለጸልን እመቤቴ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ ከአብ  ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የምንሰግድላት ቃል የሚባል እግዚአብሔር ባንቺ ባሕርይ ካንቺ ይወለድ ዘንድ የወደድሽ እመቤቴ ማርይም ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ እኔ ለምእመናን ወንጌልን የማስተምርለት የጌታ እናቱ እመቤቴ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ ፡፡ ከወለድሽው በኋላ ማኅተመ ድንግልነሽ እንዳይለወጥ አድርጎ የጠበቀሽን አማኑኤልን የወለድሽው እመቤቴ ማርይም ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ ማኅተመ ድንግልናሽ ሳይለወጥ ንጉስ ክርስቶስን የወለድሽ እመቤቴ ማርይም ሆይ ሰልምታ ይገባሻል፡፡ ልዩ መድኃኒታችንን በመውለድሽ እናትም አገልጋይን ተብለሻልና፡፡ እግዚአብሔር ባሕርይሽን ባሕሪይ አድርጎ ባለ ሟነትን አግኝተሸልና እመቤቴ ማርይም ሆይ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ 

እኛ ከምንወደው እሱም ከሚወደን ልጅሽ ኃጢአታችንን ያስተሰርይልን ዘንድ ለምኚልን፡፡

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages