በጎንደር ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መመሪያ ከቤተ ክህነት ጋር በመተባበር በሲኒማ አዳራሽ የአለም የቱሪዝም በዓልንና የመስቀልን በዓልን ምክንያት በማድረግ
#የቅኔ ምሽት ኘሮግራም ተካሄደ ።
በቅኔ ዘረፍ ኘሮግራሙ ላይ በርካታ ሊቃውንቶች ምዕመናንን እና የከተማ አመራሮች ተሳትፈዋል ።
በቅኔ ዘረፍው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ ቻላቸው ዳኘው በሀገሪቱ ከተመዘገቡት የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች መካከል የመስቀል በዓልና የጥምቀት በዓል መሆናቸውን ገልጸዋል ።
በቀጣይም ይህን እሴት ይበልጥ በማሳደግ ወደ አደባባይ የሚመጣ ኩነት በማድረግ ለአለም የቱሪዝም ገቢያ ከሚቀርቡ ሃብቶች ውስጥ አንዱ እንዲሆን አልመን እየሰራን ነው ብለዋል ።
የጎንደር ከተማ ብልፅግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አወቀ አስፈሬ የእንኳን ለብርሃነ መስቀሉ ዋዜማና ለአለም ቱሪዝም ቀን በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
ይህንን የቅኔ የዕውቀት ይበልጥ በማጎልበት በማዘመንና በማሰናዳት ከውስጥ የቤተክርስቲያን አገልግሎት የበለጠ ወደ ሰፊና ብዙሃንን ተደራሽ የሚያደርግ እርካብ ማሳደግ ይኖረብናል ብለዋል።
በቀጣይም ዛሬ በአዳራሽ የጀመርነውን አንቅስቃሴ በአደባባይ በመግለፅ የስልጣኔ ቀንዲልነታችን ለማስረዳት አመታዊ የቅኔ ውድድር ስርዓትን ፈጥረን በማያቋርጥ መንገድ ማካሄድ አለብን ብለዋል ።
በዓሉም የሰላምን፣የ ፍቅርን ፣ የአንድነትንና ታላቅነትን ልንሰብክበት ይገባል ብለዋል ።
በቅኔ ምሽት ዝግጅት ላይም የበገና መዝሙር ፣ በተለያዩ ሊቃውንቶች የቅኔ ዘረፍ እና የሆያ ሆየ ጭዋታዎች ተከናውኗል ።
No comments:
Post a Comment