ምክረ አበው (ክፍል ሁለት) - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Saturday, September 17, 2022

ምክረ አበው (ክፍል ሁለት)

ራስህን በሐሰት አትውቀስ ራስን መክሰስ ትህትና አይደለም ታላቁ ትህትና ሰዎች ሲወቅሱህ መታገስ   ነው፡  ቅዱስ ስራፕዮን

  2.    የማታምንበትን ነገር ለሰው ስትል አትስራው ከሰራኸው እንደምትጠፋበት እወቅ ፡፡ መጽሐፈ ምክር
menekuse

  3.     አንደበቱን ከቧልት ከሐሜት ያየውንም ምስጢር ከመናገር የሚከለከል ሰው ልቦናውን ከኀልዮ ኃጥያት ያርቀዋል፡፡ አረጋዊ መንፈሳዊ
  4.    ጸጋ ቢሰጥህ በተሰጠህ ጸጋ አመስግን ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እንዳታጣ፡፡  ማር ይስሐቅ
  5. ራሱን የሚንቅ የሚያቃልል ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ እውቀትን ያገኛል አዋቂ ነኝ የሚል ሰው ከፈጣሪው ጥበብ ይለየዋል፡፡ አረጋዊ መንፈሳዊ
  6.    ‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው  ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ››    አባ እንጦንስ
  7.     ‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻልናል››  ቅዱስ አትናቴዎስ
  8.    ‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል››  ቅዱስ ሚናስ
  9.    ‹‹በማንም ላይ ክፈትን አትስሩ አትፍርዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና››  ታላቁ አባ መቃርስ
  10.  ‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናልሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም›› ቅዱስ አርሳንዮስ
  11.    ‹‹ቤተክርስትያን መጠጊያችን ነች ቤተክርስትያን የኖኅ መርክብ ነች በውስጧ እንጠለላልን ከውጭዋ ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል››   ቅዱስ እንድርያስ
  12.   ‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከኾነው ከምድራዊው ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ነጹሕ ካደረግነው በጸጋ መንፈስቅዱስ የተሞላን እንሆናለን›› አባ አብርሃም መፍቀሬ ነዳያን
  13.  ‹‹ስጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ህይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው›› ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
  14.  ‹‹የቤተክርስቲያን ህይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ህይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ›› ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
  15.  ‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትፀልይ እደር›› ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ
  16.   ‹‹ኃጥያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል  ኃጥያታችንን እኛ እረስትን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል››  ቅዱስ እንጦስ

 

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages