ጥምቀት ሰው በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም ተጠምቆ የእግዚአብሔር ልጅ የሚሆንበት ታላቅ
ምሥጢር ነው። ጥምቀት ማለት አጥመቀ ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም መዘፈቅ፤
መቀበር፤ በውሃ ውስጥ ገብቶ መውጣት ወይም መጥለቅ፤ መነከር ሲሆን
ምሥጢሩ ደግሞ የሥላሴ ልጅነት የሚገኝበትና፤ የኃጢአት ሥርየት የሚገኝበት ይኸውም በዓይን የማይታይ ስውር ሃብት ስለሆነ ምሥጢር
ተባለ። ጥምቀት ማለት መገለጥ ማለት ነው (ክርስቶስ ሲጠመቅ አብ፤ ወልድ፤ መንፈስ ቅዱስ ተገልጠዋልና)፤ ጥምቀት በግሪክ ቋንቋ
ሲተረጎም ኤጲፋንያ ይባላል በግ ዕዝ ቋንቋ ደግሞ አስተርአዮ ይባላል። ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመጠመቁ በፊት ብዙ
ተአምራትን እንዳደረገ መጽሐፍት ያናገራሉ። ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሰው በመጠን በማደግ ሕግን ሁሉ ከኃጢአት
በቀር ፈጽሟል። የጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መምጣት ዋና ዓላማው አዳምን ለማዳን ነውና የማዳኑን ሥራ
የጀመረው በጥምቀት ነው። በመጥምቀ መለኮት በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ወንዝ ከተጠመቀ በኋላ ሳይውል ሳያድር ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ
በመሄድ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከጾመ በኋለ በቃና ዘገሊላ ሠርግ ቤት ከእናቱና ከሐዋርያት ጋር በመገኘት በእመቤታችን ቅድስት
ድንግል ማርያም አሳሳቢነትና ምልጃ የመጀመሪያውን ተአምር አደረገ። ዮሐ 2፤11 ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እያስተማረና
እየፈወሰ እስከ ዕለተ ስቅለቱ ድረስ ብዙ ተአምራትን አድርጓል። በመስቀል
ተሰቅሎ ሞቶ ተቀብሮ መነሳትን የጥምቀት ምሳሌ የሚሆነውን የመጨረሻውን የማዳኑን ሥራ ሠርቶ አሳየን። አሁንም ቅድስት ቤተክርስቲያን
በአርባ እና በሰማንያ ቀናቸው የልጅነት ጥምቀትን ስታጠምቅ ይህንን ምሥጢር በማመልከት ምሥጢረ ጥምቀቱንና ምሥጢረ ትንሳኤውን በሚያጠይቅ
መልኩ ታጠምቃለች። በአርባ እና በሰማንያ ቀን መጠመቃችን አዳም በተፈጠረ
በአርባ ቀኑ ሔዋን በተፈጠረች በሰማንያ ቀኗ ጸጋ ያገኙበት በመሆኑ ሲሆን
በመጽሐፍም ወንድ በተወለደ በ40 ቀን ሴት በተወለደች ደግሞ በ80 ቀን የመንጻት ሥርአት እንዲደረግ የታዘዘ በምሆኑም ጭምር
ነው። ዘሌ. 12፡ 1-9።
ሦስት ጊዜ በውኃ ውስጥ ብቅ ጥልቅ አድርጎ ካህኑ ሕፃኑን/ሕፃኗን ሲያጠምቅ
ü
ጥምቀቱን በሚመስል ጥምቅት ከክርስቶስ ጋር
እነተባበራለን፡፤
ü
ከሰማይ ወርዶ ሞትን ድል አድርጎ በሦስተኛው ቀን
እንደተነሳም፤ መጀመሪያ ወደ ውኃው ስንነከር ከሰማይ መውረዱን
ü
ከዚያም በከርሰ መቃብር ማደሩን ሙትና መቃብርን አጥፍቶ መነሳቱን
በሚያመለክት፤ ከውኃው በመውጣት ይህንም 3ጊዜ በመፈጸም ምስጢረ
ጥምቀትን ከሚስጥረ ትንሳኤ ጋር በማስተባበር ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ልጅነትን በመስጠት እና በማስማር ትመሰክራለች።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳስተማረው በጥምቀትም ከእርሱ ጋር ተቀብራችሁ፥ በጥምቀት ደግሞ፥ ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር አሠራር በማመናችሁ፥ ከእርሱ ጋር
ተነሣችሁ። እናንተም በበደላችሁና ሥጋችሁን ባለመገረዝ ሙታን በሆናችሁ ጊዜ፥ ከእርሱ ጋር ሕይወትን ሰጣችሁ። በደላችሁን ሁሉ ይቅር አላችሁ። እንዳለ ቆላ. 2፡
የጥምቀት አመሠራረት
በትምህርት፦ ጌታችን መድሃኒታችን ኢይሱስ ክርስቶስ ለኒቆዲሞስ እንዳስተማረው ዮሐ3፤5
በትዕዛዝ፦
ሑሩ ወመሐሩ ኩሎ አሕዛበ ወእንዘ ታጠምቅዎሙ በሉ በስመ
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ማቴ 28፤19
በተግባር፦ ተጠምቆ
እንድንጠመቅ በማድረጉ
v ጥምቀትን የመሠረተው ጌታችን ሲሆን
፤ የተጠመቀበትም ምክንያት ።
v በብሉይ ኪዳን ያልተገለጸ አንድነት ሶስትነቱን (ምሥጢረ ሥላሴን) ለመግለጽ ።
ማቴ 16 ፥
17 ።
v እንዴት በማንና የት
መጠመቅ እንዳለብን ሊያስተምረን አብነት ሊሆነን ።
ዮሐ 13 ፥
12 ።
v ጠላት ዲያብሎስ በዮርዳኖስ የጣለውን የዕዳ
ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ ። ቆላ
2 ፥ 16 ።
ጌታችን ሲጠመቅ ሦስት አበይት ክስተቶች ተከናውነዋል ማቴ 3፤13
1) ሰማያት መከፈቱ
2) መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል መታየቱ
3) እግዚአብሄር አብ በደመና ሆኖ (ስለ ጌታችን) መመስከሩ
ጌታችን ወደ
ዮሐንስ ሄዶ የተጠመቀበት ምክንያት
v ትህትና
v ሥርዓትን ሊሠራልን ነው
ዮሐንስ
እጁን ሳይጭን ጌታን ያጠመቀበት ምክንያት
v መስዋዕተ ኦሪት አለፈ መስዋዕታችን አንተ ነህ ሲል
v መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ላይ ሲያጠምቅ እጁን ጭኖበት ቢሆን ኖሮ ዮሐንስ ጌታን አከበረው የሚሉ መናፍቃን ይነሱ ነበር
v የመለኮትን አካል መንካት አይቻለንም ሲል
ጌታችን የተጠመቀበት መሠረታዊ ምክንያቶች
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ እጅ በባሕረ ዮርዳኖስ የተጠመቀው እንደ አይሁድ ሥርዓት
ለመንጻት እንደ ዮሐንስም ጥምቀት ለሥርየተ ኃጢአት አልነበረም፡፡ ዳሩ ግን ስለሚከተሉት ምክንያቶች ተጠምቋል፡፡
v የእዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ ተጠመቀ
ወሰጠጠ መጽሐፈ ዕዳሆሙ ለአዳም ወለሔዋን እንዲል ውዳሴ ማርያም
ዘሰኑይ፡፡ ዲያብሎስ በአዳምና በሔዋን የጨለማ መጋረጃ ጋርዶ ስመ ግብርናት ጽፋችሁ ብትሰጡኝ ስቃይ/አገዛዝ አቀልላችኋለሁ አላቸው፡፡
አዳም ገብሩ ለዲያብሎስ ሔዋን አመቱ ለዲያብሎስ ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ በሁለት እብነ ሩካም ቀርጾ አንዱን በዮርዳኖስ አንዱን በሲአል
ቀብሮታል፡፡ በዮርዳኖስ የጣለውን ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲጠመቅ እንደ ሰውነቱ ረግጦ እንደ አምላክነቱ አቅልጦ አጥፍቶልናል፡፡
በሲኦል የጣለውንም በእለተ እርብ በአከለ ነፍስ ውርዶ ደምስሶልናል፡፡ ቆላ. ፪፥ ፲፬ በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም
በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው። እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል።
v ምሥጢረ ሥላሴን ለመግለጥ ተጠመቀ
ወልድ
በተለየ አካሉ በማዕከላ ዮርዳኖስ ቆሞ ሲጠመቅ፣ አብ በደመና ሆኖ ሲናገር፣ መንፈስ ቅዱስም በአምሳለ ርግብ ጸዓዳ ሲወርድ ምሥጢረ
ሥላሴ ታወቀ ተገለጠ፡፡
v ትህትናን ለማስተማር ተጠመቀ
በፈጠረው በሰው እጅ ራሱን ዝቅ አድርጎ ተጠመቀ ማቴ 3፤15
v አርአያ ሊሆነን ተጠመቀ
ማንም ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ይገባ ዘንድ መጠመቅ ግዴታው ነው።
No comments:
Post a Comment