በወላይታ አንድ ፓስተር ከ500 የቸርቹ አባላት ጋር ከኦርቶዶክሳዊነትን መቅደስ የተቀላቀለበት ድንቅ አገልግሎት‼ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Saturday, October 22, 2022

በወላይታ አንድ ፓስተር ከ500 የቸርቹ አባላት ጋር ከኦርቶዶክሳዊነትን መቅደስ የተቀላቀለበት ድንቅ አገልግሎት‼

 

በወላይታ አንድ ፓስተር ከ500 የቸርቹ አባላት ጋር ከኦርቶዶክሳዊነትን መቅደስ የተቀላቀለበት ድንቅ አገልግሎት‼
የወላይታ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ ብፁእ አቡነ ይስሐቅ/በአንድ የገጠር መንደር ድንገት ተገኝተው በሐዘን ቤት በወላይተኛ ቋንቋ ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ስብከት ሲሰጡ አንድ ፓስተር ድንገት ይሰማል።
በለቅሶ ቤት ውስጥ የሰማው ወንጌል ልቡን አረሰረሰው። የቆመበትን ዕምነት መጠየቅ ጀመረ። ከእራሱ ጋርም ተማከረ።
ቸርች ከፍቶ 500 የቸርች አባል አፍርቶ ለዓመታት ኖሯል። ራዕይ፣ትንቢት፣ልሳን በእዚህ አደራሽ ውስጥ በተደጋጋሚ ተነግሮበታል።
መጽሐፍትን ገልጦ ይመረምርም ጀመር።አምላኩን በየዋህነት መጠየቅ ጀመረ።
ድንገት በአንደኛ ቀን ግን ይህ ፓስተር ዕለተ ሰንበት በአደራሽ ውስጥ ለተሰበሰበው የቸርቿ አባላት ያልተለመደ ስብከት መስጠት ጀመረ።
ስለኦርቶዶክሳዊት መቅደስ መናገር ጀመረ። ትክክለኛ ሃቀኛ ቤት እንደሆነች መመስከሩን ተያያዘ። መጀመርያ ላይ የቸርቿ አባላት ማጉረምረም ጀመረ።
ነገር ግን ቀስ በቀስ የፓስተሩ ስብከት ልባቸውን ውስጥ መተከል ጀመረ። በጥሞና ሰሙት። በስተመጨረሻም ፓስተሩ አንድ የመጨረሻ ቃል ተናገረ።
በወላይተኛ ቋንቋም እንዲህም አለ.... "የሱሲ ና ቱማ ኦርቶዶክሴን ማቅደሴ ዴስ፣አዋ ናአ ፂሎ አያናአ ኢሲ ጦሳን ሥላሴቲ አማኖቴፔ ሶን ሃይቴ ኢሲፔ ባና" አለ።
የአማርኛ ግትርጓሜ "ኢየሱስ እና እውነት በኦርቶዶክስ መቅደስ አለ፣አብ ወልድ መንፈስቅዱስ አንድ አምላክ ሥላሴ ወደሚመለክበት ቤት አንድ ላይ እንሄዳለን " ሲል ስብከቱን አሰረ።
ፓስተሩ ከእነቸርቿ አባላት ወደ ኦርቶዶክሳዊት ቤት መጥተው ተጠመቁ።
የመድኃኒዓለም ቤተክርስትያን እና ታቦት ስጡን ሲሉ ሀገረ ስብከቱን ጠየቁ።
እነሆ በጥያቂያቸውም መሰረት በአከባቢው የመድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን እየታነጸላቸው ይገኛል።
ወዳጄ ይህን ድንቅ አገልግሎት ሰምተህ እግዚአብሔርን አታመሰግንም ወይይይ?
በእዚህ አገልግሎት ውስጡ እረኛ የሆኑት ብጽኡ አቡነ ይስሐቅ በረከታቸው ይደርብን
የሀገረስብከቱ ብርቱ ሥራ አስኪያጅ ቀሲስ ቦኪቻ ኢንጋ ቅድስት ቤተህርስቲያን ስለሱታፌዎ ታመሰግኖታለች።
 

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages