ኢሬቻ ጣኦት አምልኮ ነው፡፡ በብጹዕ_አቡነ_ኄኖክ_የምዕራብ_አርሲ_ሀገረ_ስብከት_ሊቀ_ጳጳስ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Saturday, October 1, 2022

ኢሬቻ ጣኦት አምልኮ ነው፡፡ በብጹዕ_አቡነ_ኄኖክ_የምዕራብ_አርሲ_ሀገረ_ስብከት_ሊቀ_ጳጳስ



☞ኢሬቻ ‼️እና ዋቄ_ፈታ‼️

በብጹዕ_አቡነ_ኄኖክ_የምዕራብ_አርሲ_ሀገረ_ስብከት_ሊቀ_ጳጳስ ‼️‼️


☞አንድ ሺህ ዓመት ወደ ኃላ የሚመልስ ሥርዓት ነው ሲሰራ የነበረው።#ዋቄፈታን አስባችሁ ታውቃላችሁ? ሺህ ዓመት ሕዝቡን ወደ ድንቁርና ወደ ጨለማ ሕይወት የሚመልስ ነው።
☞የሐይማኖት አባት ስለሆንኩ ግልጽ ነው የምንናገረው።ሽፋኑ ባህል ነው። ወደ ውስጥ ገባ ብላችሁ ስታዩት ግን ጣኦት ነው።ያሳዝናል።
☞የክርስቶስ የማዳን ሥራ እንቅፋት የሆነ ስብስብ ነው። የኦሪቱ ሥርዓት ይመስላል ግማሹ።
☞የዐዲስ ኪዳን ልጆች ነን።የዘለዓለም ሕይወትን የሚያወርሰን አንድ ጌታ ዋጋ ከፍሎልናል።የሰው ልጆችን በፍቅሩ ያዳነን የእሱን አሰራር የእሱን የከፈለው ዋጋ በዜሮ የሚያባዛ ነው በሐገራችን ላይ እየተሰራ ያለው።
☞የኦሮሞ ሕዝብ እንደ ቤተ ሙከራ ነው የታየው።
ማነው ይኼን እውነት የሚናገረው? #ሊቀጳጳሱ ነው?#ቄሱ ነው?#ሰባኪው ነው? ሁሉም ዝም ብለዋል። ትውልዱ ግን እያለቀ ነው።ብዙ ሚስጢር አለ።#በእሬቻ ስም ነው የሚደረገው። ሽፋኑ ግን ባህል በሚል ነው።
☞ክርስቲያን ሆነው ክርስቲያን ነን ብለው ይሄ ነገር ሲነገር የሚቆጠቁጣቸው ሰዎች አሉ።ራሳቸው የሚያማቸው ሰዎች አሉ ይመማቸው።እኛ እውነት ነው የምንናገረው። ወደድንም ጠላንም ያለ ክርስቶስ የዘላለም ሕይወት የለም።
☞በአርባ ቀን በሰማኒያ ቀን ያገኘናት ልጅነት በዚህ በጣኦት አሰራር እያጣናት ነው።
☞የኛዎቹ መስቀል ይዘው ካህን ተብለው እዛ ግን በርቱ የሚሉ አሉ። ወደ ዝርዝሩ አልገባም።
✍እኔ ብቻዬን ምንም ማምጣት አልችልም። እናንተን ግን ይዤ ብዙ መስራት እችላለው።
#ብጹዕ_አቡነ_ኄኖክ_የምዕራብ_አረርጌ_ሀገረ_ስብከት #ሊቀጳጳስ
☞አሁን ባለንበት ወቅታዊ ሁኔታ ሁሉም ዝም ባለበት ጊዜ እንዲህ ያለ ድፍረትን የሚጠይቅ እውነትን አፍረጥርጦ መግለጥ ለፈሩት :ለጥቅመኞች እና ለአድር ባዮች ማንቂያ ነውና ብጹእነታቸውን ማመስገን ቃለ ህይወት ያሰማልን ልንል ይገባናል።

 

 

Source:- for more information visit {መ/ር ፍቅረማርያም ፀጋዬ} facebook

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages