የመላእክት ተራዳኢነት - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Saturday, October 8, 2022

የመላእክት ተራዳኢነት

 

የመላእክት ተራዳኢነት

“እነሆም ከዋነኞቹ አለቆች አንዱሚካኤል ሊረዳኝ መጣ “(ዳን 10 ፡ 21) 
 
ከዓለማት  በፊት  የነበረ፣  ያለና  የሚኖር፣  የጌቶች  ጌታ፣  የነገሥታት  ንጉሥ ...  እግዚአብሔርዓለማትን  ፈጥሮ  በውስጣቸው  ያሉትን  ፍጥረታት  ለአንክሮ  ለተዘክሮ  ከመፍጠሩ  አስቀድሞ  መላእክትን  ፈጠረ፡፡  ቅዱሳን  መላእክትም  መቼ፣  ለምንና  እንዴት  እንደተፈጠሩ  ብዙ  ሊቃውንት  ብዙ  ጽፈዋል  አስተምረዋል፡፡ " ቅዱሳን  መላእክት  በዕለተ  እሑድ  በወርኃ  መጋቢት  በመጀመሪያው ሰዓት "" እምኃበ  አልቦ  ኃበ  ቦ "  ፈጥሮአቸዋል፡፡  ተፈጥሮአቸውም  በነቢብ ( በመናገር )  አይደለም፤  በአርምሞ ( በዝምታ )  ነው  እንጂ  የተፈጠሩበትም  ዓላማ  ሰውንና  እግዚአብሔርን ለማገልገል  ነው፡፡ ( ኃይለ  ጊዮርጊስ . 1993 ፡ 3)  በማለት  አስቀምጠውታል፡፡

የመላእክት  ህልውና  ወይም  የአኗኗር  ሁኔታም  እስከ  ዓለም  ፍጻሜ  በትጋትና  በቅድስና  ሰውንና  እግዚአብሔርን  ሲያገለግሉ  የሚኖሩ  ኢመዋትያን ( የማይሞቱ )  ሲሆኑ  ተፈጥሮአቸውምእንደነፋስና  እንደ  እሳት  ነው  ፈጣንና  እረቂቅ  ናቸው፡፡  የመላእክት  ግብራቸው  ምንድን  ነው  ቢሉ  እንደነፋስ  የሚፈጥኑ  እንደ  እሳት  የሚረቁ  ስለሆነ  ከእሳትና  ከንፋስ  ተፈጥረዋል  እንላለን  እንጂ  የመላእክት  ባሕርያቸው  አይታወቅም ( አክሲማሮስ፤  ገጽ . 94) ፡፡  እሳት  ኃያልና  ብሩህ  ነው፡፡  መላእክትም  ኃያላንና  ብሩሃነ  አዕምሮ  መሆናቸዉን  ለማጠየቅ፤  ንፋስ  ፈጣን  ነው  መላእክትም  ፈጣን  መሆናቸውን  ለማጠየቅ፤  ቅዱሳን  መላእክት 10  ከተማና 7  ሊቃነ  መላእክት  ሲኖሩአቸው  ለእግዚአብሔር ቅርብ  ከመሆናቸዉየተነሳ  ልዩ  ልዩ  ሰማያዊ  ሥልጣንከእግዚአብሔር  ተሰጥቷቸዋል፡፡
የመጀመሪያው  የመላእክት  አለቃ  ቅዱስ  ሚካኤል  ሲሆን  ስም  ትርጊሜዉም " መኑ  ከመ  አምላክ " ( ማን  እንደ  አምለክ )  ማለት  ነው፡፡  የመላእክት  አለቃ  ቅዱስ  ሚካኤል  ሹመቱ  ከእግዚአብሔር  ሆኖ  ዕለተ  ሢመቱም  ህዳር 12  ቀን ነው፡፡ " አመ 10  ወ 2 ቱ  ለኅዳር  ሲመቱ  ለቅዱስ  ሚኮኤል " ( መጽሐፈ  ድጓ 1981 ፡ 84 ፡ 1 ኛ  ዓምድ )  " ለጠቢብ  አሐቲ  ቃል  ትበቁዖ "  ነው እንጂ  ሌሎችም  መጻሕፍትና  ጸሐፍት  ብዙ  ብለዋል፡፡
  " አንድ  አምለክ  በሚሆን  በአብ  በወልድ  በመንፈስ  ቅዱስ  ስም  ህዳር 12  በዚህች  ቀን  ለሰው  ወገን  የሚያዝንና  የሚራራ  በእግዚአብሔር ጌትነት  ፊት  ሁል  ጊዜ  በመቆም  ለፍጥረቱ  ሁሉ  የሚማልድ  የመላእክት  አለቃቸው  ለሆነ  ለቅዱስ  ሚካኤል  በዓለ  ሢመቱ  መታሰቢያ  ነው፡፡ ( መጽሐፈ ስንክሳር፡  ከመስከረም  እስከ  የካቲት፡ 1994 ፡ 297) ያለ እረፍት  ሰውንና  እግዚአብሔርን የሚያገለግለዉ  ቅዱስ  ሚካኤል  እኛ  የአዳም  ልጆች በአለመታዘዝ  ምክንያት  በሚያጋጥመን  መሰናክል  እንዳንሰናከል  ምሕረትን  ከእግዚአብሔር  ይለምንልናል፡፡ " ተውህቦ  ምሕረት  ለሚካኤል "  እንዲል፡፡  ሕዝበ  እሥራኤል  ከዘመቱና  ባርነታቸዉ  ወደ  ነጻነት  ከምድረ  ግብጽ  ማርና  ወተት  ወደምታስገኘው ሀገረ  ርስት  በእግዚአብሔር እርዳታ  በሚሄዱበት  ጊዜ  ባለመታዘዛቸው  ምክንያት  እንዳይጠፉ  ምሕረት  እየለመነ  ለሀገራቸው  ያበቃቸዉምይኸው  መልአከ  ነበር፡፡ " እግዚአብሔርም  ሙሴን  እንዲህ  ብሎ  ተናገረው።  ሂድ፥  ለአብርሃምና  ለይስሐቅ  ለያዕቆብም።  ለዘርህ  እሰጣታለሁ ብዬ  ወደ  ማልሁባት  ምድር፥  ወተትና  ማርም  ወደምታፈስሰው  ምድር  አንተ  ከግብፅ  ምድር  ካወጣኸው  ሕዝብ  ጋር  ከዚህም  ውጣ።  አንገተ  ደንዳና  ሕዝብ  ስለሆንህ  በመንገድ  ላይ  እንዳላጠፋህ  እኔ  በአንተ  መካከል  አልወጣምና  በፊትህ  መልአክ  እሰድዳለሁ  ከነዓናዊውንአሞራዊውንም  ኬጢያዊውንም ፌርዛዊውንም  ኤዊያዊውንም  ኢያቡሳዊውንም አወጣልሃለሁ። "  ዘፀ 33 ፡ 3  ተብሎ  እንደተጻፈ፡፡

በገመድነው  በኃጢአት  ገመድ  ተተብትበን  መውጫ  አጥተን  ለምንፈራገጠው ለእኛ  ለአዳም  ልጆች  እድፋችን  በዝቶ  እግዚአብሔር  ፊቱን  እንዳይመልስብን  በንስሐ  ለመታጠብ  እንችል  ዘንድ  ጽድቅን  የሚመክረን  መልአክም  ይኸው  ሊቀ  መልአኩ  ሚካኤል  ነው፡፡  ነገር  ግን  በእዉነት  ጽሑፍ  የተጻፈውን  እነግራለሁ  በዚህም  ነገር  ከአለቃችሁ  ከሚካኤል  በቀር  ማንም  የረዳኝ  የለም " ( ትንቢተ  ዳንኤል 10 ፡ 22)  ብሎ  መስክሮአል፡፡ ክብርና  ምሥጋና  የባሕርዩ  የሆነ  የእዉቀት  ባለቤት  እግዚአብሔር አማካሪ  የማያስፈልገው  ቢሆንም  ለመለኮቱ  ለቸርነቱ  እና  ለትሕትናው  አድማስ  ስለሌለው  ለመላእክት  ለጻድቃንና  ሰማእታትያለውን  ክብርና  ፍቅር  ሲገለጽ  የነርሱን  ልመና  ይቀበላቸዋል፡፡ " እግዚአብሔርን  በሰማይ  የሚተካከለው  ማነው  ከአማልክትስ እግዚአብሔርን  ማን  ይመስለዋል  በቅዱሳን  ምክር  እግዚአብሔር ክቡር  ነው " ( መዝሙር 86 ፡ 6-7) ፡፡

እናስተውል  እራሳችንን  አዋቂ  አደርገን  የሰውን  ምክር  ይቅርና  የእግዚአብሔርን  ምክር  አንቀበልም  ለምንል  ከበሮዎች  ምንያክል  ባዶ  መሆናችንን  ከመረዳታችንም  በተጨማሪ  ቅዱስ  ሚካኤል  የእግዚአብሔር  የቅርብ  አማካሪ  ነው፡፡ በጊዜአቸው፣  በሥልጣናቸው፣  በጉልበታቸው፣ እንዲሁም  በገንዘባቸው  ተመክተው  ለአንዴናለመጨረሻ  ሊረጋግጡን  ፕላን  አውጥተው  በተጠንቀቅ  ለሚያስደነግጡን ኃያላንም  እምነታችንን  ተስፋችንንና አለኝታችንን  ለእግዚአብሔር  ሰጥተን  ለምንጠራው  ለእኛ  ለድሆቹ  ከጐናችን  ደረስ  ብሎ  ጠላቶቻችን  እሶት  የገባ  ቅቤ  የሚያደርግልን  ይኸው  መልአክ  ሚካኤል  ነው፡፡ " የእግዚአብሔር  መልአክ  በሚፈሩት  ሰዎች  ዙሪያ  ይሰፍራል  ያድናቸውማል " ( መዝሙር 33 ፡ 7)  ተብሎ  እንደተጻፈ፡፡
በሠራዊቱ  ብዛት  እና  ጥራት  ተመክቶ  አንገተ  ሠባራውን  እና  የኢየሩሳሌም ንጉሥ  የነበረውን  ንጉሥ  ሕዝቅያስን  ከዓለማት  ሕይወት  አሠናብተዋለሁ ብሎ  ሲያናፋ  በማሰው  ጉድጓድ  የተመረገው  ንጉሥ  ሰናክሬም  በቅዱስ  ሚካኤል  ተራዳኢነት  ነበር፡፡ " ኢይድኅን  ንጉሥ  በብዝኃ  ሠራዊቱ፡ -  ንጉሥ  በሠራዊቱ  ብዛት አይደንም "  ተብሎ  ተጽፏልና።    መዝሙር 32 ፡ 16
ዛሬስ  ቢሆን  በዙሪያችን  ከቦ  የቅርጫ  ሥጋ  ሊያደርገን  እየፈለገ  ያለዉ  ረሀብ  እርዛት  ጥላቻ  እንዲሁም  በአጠቃላይ  ዲያብሎስንና ሴፈዣግሬውን  እሳትየገባ  ጭድ  አድርጐ  ወደ  ቀደመ  ሰላማቸን  እንድንመለስ  የሚያደርገን መልአክም  ይኸው  ሚካኤል  ነው፡፡ ከፈርዖን  ማዕሠረ  አገዛዝ  በፈቃደ  እግዚአብሔር ወጥተው  ወደምድረ  ርስት  ለመግባት  እንደ  ነደ - እሳት  በተንቀለቀለው  የሲና  በረሀ  አቋርጠው  ለማለፍ  ደፋ  ቀናሲሉ  የነበሩትን  የእግዚአብሔር  ድሆች  ደቂቀ  እሥራኤልን  በላዔ - ነዳያን  ረሀብ  ወጽምእ  እቋደሣቸዋለሁ  ብሎ  አፉን  ባፏሸከ  ጊዜ  ፈጣሬ  ወመጋቢ  ዓለማት  እግዚአብሔር  የከፈተውንጉሮሮ ለመዝጋት  መና  ሲያዘንብላቸውና ማየ  ሕይወትን  ሲያፈልቅላቸው የአስተናጋጅነቱን  ኃላፊነት  የፈረመው  ይኸው  ሊቀ  መላእክት  ነበር፡፡ " ይበሉም  ዘንድ  መና  አዘነመላቸው፤ ከሰማይ  እንጀራምሰጣቸው  የመላእክትንም እንጀራ  ሰው  በላ " ( መዝ 77 ፡ 24 – 25)  ተብሎ  እንደተጻፈ፡፡ በ 4 ቱም  መዓዘን  ቀለበት  ውስጥ  አስገብቶ  ከመንገድ  አስቀራቸዋለሁ  በማለት  ሲያገሣ  የነበረው  አንበሳ  ረሀብና  ጽም  ብቻዉን  መች  ነበር  በምድያማዊያንና  በአማሌቃዊያን ሾተል  ላይ  እንዲሁም  በፈርዖንና  በሠራዊቱ  ልቡና  ተሰግስጐ  የነበረው  በለዔ - አዳም  ዲያብሎስ  ሁሉ  ነበር  እንጂ፡፡  በመሆኑም  ተመዝዞ  የነበረውን  የአማሌቃዊያንን  እና  የምድያማዊያንን  ሰይፍ  ወደሰገባው  መልሶ  ፈርዖንና  ሠራዊቱንም  በባሕረ - ኤርትራ  ውሃ  የገባ  ጨው  አደርጐ  ያስቀረውም  መልአክ  እኮ  ይኸው  ቅዱስ  ሚካኤልነው፡፡ የሐዋርያት  ተከታዮች  ሊቃውንትም  በመጽሐፋቸዉ  እንዳስተላለፉት፡ - " ይህም  በንጉሥ  ጭፍራ  አምሳል  በታላቅ  ክብር  ሆኖ  የነዌ  ልጅ  ኢያሱ  ያየው  የእግዚአብሔር ሠራዊት  አለቃ  ነኝ፡፡  አሁንም  ወደ  አንተ  መጥቼአለሁ፤ ኢያሱም  በግንባሩ  ከመሬት  ተደፍቶ  ሰገደለትና  በእኔ  በባርያህ  ዘንድ  ምን  አቁመሃል  አለው  ሚካኤልም  ኢያሱን  የቆምክባት  ምደር  የተከበረች  ነችና  ጫማህን  አለው፡፡  ኢያሪኮንና  በውስጧ  ያለውን  ንጉሡን  ከኃያላኑና  ከአርበኞቹ  ጋር  እንሆ  በእጃችሁ  እሰጣችኋለሁ " ( መጽሐፈ  ስንክሳር ከመስከረም - መጋቢት 1994 ፡ 296)
መላእክት  የሰውን  ልመና  ወደ  እግዚአብሔር፣ የእግዚአብሔርን  በረከትና  ረድኤት  ወደሰው  የሚያመላልሱ መሆናቸውን  በሁለተኛው  አንቀጽ  ኃይለ  ቃል  ላይ  ያስቀመጥነው በመሆኑም  ጸሎታችንን  ጾማችንን  እንዲሁም  ለእግዚአብሔር የምናቀርበውን  መሥዋዕት  በእግዚአብሔር ዘንድ  የሚያሳርግልን  መልአከ  ይኸው  ሚካኤል  ነው፡፡  ደቂቀ  እሥራኤል  ሕጉን  እግዚአብሔርን  እየተዉ  አምልኮተ  ጣዖታትን  ከመከተላቸ  የተነሣ  ለጠላት  እየአሳለፈ  እየሰጣቸው  በአማሌቃዊያንና በምድያማዊን  እጅ  ሲወድቁ  እየተመለሱ  ወደ  እግዚአብሔር  ሲያዝኑ  እግዚአብሔር  ፊቱን  እየመለሰ  ይመራቸው  የነበረው  በመልአኩ  በሚካኤል  አማካኝነት  ነበር ፡፡  መስዋዕታቸውንም  እግዚአብሔር ተቀብሎአቸዋል፡፡
የቅዱስ ሚካኤል ረድኤት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡    

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages