"ዛሬ ሀገራችንን ምስቅልቅል ውስጥ እንድትገባ ያደረጓት የተለያዩ መጥፎ ሚዲያዎች ናቸው" ብፁዕ አቡነ ናትናኤል - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Saturday, October 29, 2022

"ዛሬ ሀገራችንን ምስቅልቅል ውስጥ እንድትገባ ያደረጓት የተለያዩ መጥፎ ሚዲያዎች ናቸው" ብፁዕ አቡነ ናትናኤልጥቅምት 18 ቀን 2015 ዓ.ም (ቲ.ኤም.ሲ/ አዲስ አበባ)

ዛሬ ሀገራችንን ምስቅልቅል ውስጥ እንድትገባ ያደረጓት የተለያዩ መጥፎ ሚዲያዎች ናቸው ሲሉ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የዴንቨር ኮሎራዶ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ገለጹ።

ብፁዕነታቸው ይህን ያሉት ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል በትላንትናው እለት ባዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ እና የ ኪነ ጥበብ መርሐግብር ላይ ነው።

ሚዲያ ለቤተክርስቲያናችን አስፈላጊ ነው ስለዚህ ሚዲያ ይገድላል ሚዲያ ያድናል፤ ሚዲያ ይበትናል ሚዲያ ይሰበስባል ያሉት ብፁዕነታቸው ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከልም አጀማመሩ የሚያምር ነውና ሊደገፍ የሚገባው ሚዲያ መሆኑን ጠቁመዋል።

ብፁዕነታቸው አክለውም "የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በዕድሜ ታናሽ የሆነ ሀገረ ስብከት ሲሆን ነገር ግን በሥራ እጅግ ረጅም ዕድሜ ያስቆጠሩ አህጉረ ስብከቶችን የቀደመ ሀገረ ስብከት ነው ብለዋል።

ዛሬ ሀገራችንን ምስቅልቅል ውስጥ እንድትገባ ያደረጓት የተለያዩ መጥፎ ሚዲያዎች ናቸው ያሉት ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ያንን ደግሞ ድል ማድረግ የሚቻለው እንደነዚህ ዓይነት መልካም ሚዲያዎችን እየደገፍን ስናሳድግ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ሌላ በዚሁ የገቢ ማሰባሰቢያ እና የ ኪነ ጥበብ መርሐግብር ላይ ሐሳባቸውን የሰጡት ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ዶክተር የሰሜን አሜሪካ የሰሜን አሜሪካ ሜኒሶታ እና የኢሉ አባቦራ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ "ሚዲያ የእግዚአብሔርን ቃል የምንማርበት፤ ከእግዚአብሔር በረከት የምንቀበልበት ፤ከእግዚአብሔር ጋር የምንታረቅበት ፤የጠፉ ሰዎች የሚመለሱበት" እንደሆነ ተናግረዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል እና ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስን ጨምሮ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የምዕራብ ሸዋ፣ የምስራቅ ወለጋ እና ሆሮ ጉድሩ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ አበረታተዋል።

Source:-  ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages