"ውብ የሆኑ አብያተ ክርስቲያናት ማነጽ እንዳለ ሆኖ የእኛ ሕይወት መሠራትና ተረካቢ ትውልድም ልናዘጋጅበት ይገባናል" ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Saturday, October 29, 2022

"ውብ የሆኑ አብያተ ክርስቲያናት ማነጽ እንዳለ ሆኖ የእኛ ሕይወት መሠራትና ተረካቢ ትውልድም ልናዘጋጅበት ይገባናል" ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል

 

የዋሽንግተን ዲስና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ


(ኢኦተቤ ቴቪ ጥቅምት ፲፯ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም)

በሰሚት ኆኅተ ምሥራቅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት የአዲስ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱና የጻድቁ አቡነ አረጋዊ ዓመታዊ ክብረ በዓል በአንድ ላይ ጥቅምት ፲፬ /፳፻፲፭ ዓ/ም ሲከብር ታቦታቱ ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው ዑደት ያደረጉ ሲሆን ልብን በሚያሳርፍ ዝማሬና ሽሻቦ በማጀብ ነበር፡፡
ከዑደቱ በኋላም ሕንጼሃ አዳም ለኆኅተ ምሥራቅ የሚል ወረብ በደብሩ ሊቃውንት:
 
በመቀጠል የደብሩ ፈለገ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን ዝማሬ ቀርቧል፡፡ 
 
በበዓሉ ትምህርተ ወንጌል የሰጡት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዋሽንግተን ዲስና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብዙ ድካምና ገንዘብ ሕንጻውን መሠራቱን አመስግነው ይሁን እንጅ በሀገራችን የተከሰተው የመጠላላትና ከፍተኛ የእርስ በርስ ጦርነት ያለመሠራታች ምልክት ነው ያሉ ሲሆን በክርስትና ሕይወታችን ቅዱስ በሆነ መንገድ ልንሠራ ይገባል በማለት ገልጸዋል፡፡ 
 
ብፁዕነታቸው አክለውም የሕንጻ ቤተ ክርስቲያን መገንባታቸው እንዳለ ሆኖ ክርስትናችን ላይና ተተኪ ትውልድ ላይ መሥራት ይኖርንብናል ያ ካልሆነ እንደምዕራቡ ዓለም አብያተ ክርስቲያናቱ ተላልፍ ሌላ ዓላማ ሊውሉ ስለሚችሉ ከወዲሁ ልናስብበት ይገባናል ብለዋል፡፡ 
 
ብፁዕነታቸው ቀጥለውም እንደሀገርም ከገባንበት የሰላም እጦት ሁኔታ ልንወጣ እንደሚገባን ሲያስረዱ ጥቅምት ፲፬ የተሰወሩት ጻድቁ አቡነ አረጋዊ ትወልዳቸው ሌላ ሀገር ቢሆንም ለኢትዮጵያውያን አባት ከመሆን ያገዳቸው ነገር አልነበረም ስለሆነም ሰውን በሰውነቱ ልንወድ፣ ልናከብርና ሰላማዊ ልንሆን የገባል በማለት በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡ 
 
በመጨረሻም ብፁዕነታቸው ቡራኬ በመስጠት የቅዳሴ ቤቱ ክብረ በዓል ፍጻሜ ሆኗል፡፡
© EOTC TV

 

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages