ሦስት ኦሬንታል በሚል እውቅና በሌለው....... - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Sunday, October 23, 2022

ሦስት ኦሬንታል በሚል እውቅና በሌለው.......

 

"ሦስት ኦሬንታል በሚል እውቅና በሌለው የመካከለኛ ምሥራቅ የኦሬንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት የሚባል ጉባኤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ጥንታዊ ይዞታ ላይ ያቀረቡት የጋራ መግለጫ ተቀባይነት የሌለው ነው"
በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የውጭ ጉዳይ መምሪያ
(ኢኦተቤ ቴቪ ጥቅምት ፲፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም )
 
ከአኀት ኦርቶዶክስ አብያተ ክርሰቲያናት ውስጥ በመካከለኛ ምሥራቅ የሚገኙት የሶርያ፣ አንፆኪያ ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን የግብፅ አሌክሳንደርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶከስ ቤተ ክርስያን፣ እና በአርመን ቤተ ክርስያን የቂልቅያ - ሊባኖስ መንበር ይገኝበታል፤ እነዚህ ሦስት አብያተ ክርስቲያን በመካከለኛ ምሥራቅ ካለው የፖለቲካና የጸጥታ ሁኔታ ጋር በማያያዝ የራሳቸው የሆነ ሌሎቹን የኦሬንታል አኀት አብያተ ክርስቲያናት ያገለለ የጋራ መድረክ ከፈጠሩ ከዐሥር ዓመት በላይ ሆኗቸዋል፤
ስለጉባኤው ቀደም ሲል በአምስተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና በወቅቱ የነበሩትን የሦስቱንም አብያተ ክርስቲያናት ፓትርያርኮች የጠየቁ ሲሆን በወቅቱ ተመለሱላቸው ምልሶች አንደኛው ጉዳዩ የሚመለከተው መንበረ ፓትርያኮቻቸው እና ዋና ማዕከላቸው በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ የግብጽ እስክንድርያ፣ የሶርያ አንፆኪያ እና የአርመን ቂልቅያ መንበሮችን መሆኑን እንዲሁም የምክክሩ ዓላማም በወቅቱ በመካከለኛው መሥራቅ የነበረውን የአክራሪዎች እንቅስቃሴ በተመለከተ፣ በተጨማሪም ሦስቱ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ሌሎቹን ለማግለል ሳይሆን የመካከለኛው ምሥራቅ ችግር ከሌሎቹ ስለሚለይ ያንን የተመለከተ ጉባኤ መሆኑን ገልጸው ነበር፡፡
ይሁን እንጅ በቅርቡ በአውሮፓውን አቆጣጠር ከኦክቶበር 18-20 (ከጥቅምት 8-10) ድረስ ዐሥራ ሦስተኛው የመካከለኛው ምሥራቅ ኦሬንታል አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ጉባኤ በሚል 13th Meeting of the Heads of the Oriental Orthodox Churches in the Middle East፣ ምንም ዕውቅና የሌለው ጉባኤ በማድረግ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ የጉባኤው የጋራ መግለጫ ነው የተባለው ሰነድ በዛሬው ዕለት በሶርያ ቤተ ክርስቲያን ይፋዊ ድረ-ገጽ እና ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ወጥቷል፤ በመግለጫው ላይ ከመካከለኛው ምሥራቅ አልፎ ሌሎቹ የኦሬንታል አብያተ ክርስቲያናትን የሚመለከት መግለጫን ያካተተ ተቀባይነት የሌላቸውን አንቀጾች ያካተተ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
በዚህ መግለጫ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊ፣ ታሪካዊ፣ ሉዓላዊ የሆኑ ይዞታዎችን ያለምንም የታሪክ፣
ከእምነት፣ የቅርስ አጠባበቅ፣ የሕግና የሥርዓት መነሻ፣ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው የመግለጫ አንቀጽ በማካተት ከጥንት ጀምሮ በአንድነት የኖሩ የኦሬንታል አብያተ ክርስቲያናትን ለልዩነት በሚዳርግ መልኩ መግለጫ አውጥተዋል፡፡
በዋናነት በጋራ መግለጫቸው በሰባተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ያላትን ታሪካዊ ድርሻና እና ጥንታዊ ይዞታዎች ላይ ያስቀመጠው ከእውነት የራቀና በአብያተ ክርስቲያናቱም መካከል ያለውን ታሪካዊና እምነታዊ ትሥሥራቸውን የማይመጥን ሆኖ ተገኝቷል።
"Seventhly: The Case of El- Sultan Monastery in Jerusalem that is owned by the Coptic Orthodox Church
We are saddened by the recent developments in the case of El-Sultan Monastery that was captured by the Ethiopian monks, and their methods in trying to display their flag during Easter celebrations as proof of their ownership.
We stand and support the Coptic Orthodox Church in its ownership of this Historic Coptic Monastery."
ስለ ጉዳዩ የመንበረ ፓትርያርክ የውጭ ጉዳይ መምሪያ ክትትል በማድረግ እና ውሳኔ እንዲሰጥበት እንደሚያቀርብ ለዚህም አስፈላጊውን ጥረት እንደሚደርግ ገልጧል።
 
Source:  
 በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የውጭ ጉዳይ መምሪያ

 

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages