የእመቤታችን ስደት [ክፍል ሁለት] - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Saturday, October 8, 2022

የእመቤታችን ስደት [ክፍል ሁለት]

 ፈቀደ እግዚእ ያግእዞ ለአዳም ሕዙነ ወትኩዘ ልብ ወያግብኦ ኅበ ዘትካት

 መንበሩ ሰአሊ ለነ ቅድስት።

ጌታ ልቡ ያዘነና የተከዘ አዳምን ነጻ ያወጣውና ወደ ቀድሞ ቦታው
 
 ይመልሰው ዘንድ ወደደ ቅድስት ሆይ ለምኝልን።(ውዳሴ ማርያም ዘሰኑይ)

መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል፤ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፤ ሲላት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መልአኩን ባየችው ጊዜ ከንግግሩ የተነሳ እጅጉን ደነገጠችና ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው? ብላ አሰበች፤ መልአኩም እንዲህ አላት፤ ማርያም ሆይ በፈጣሪሽ ፊት ታላቅ ጸጋን አግኝተሻልና አትፍሪ፤ እነሆም ትጸንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ስሙንም ኢየሱስ ብለሽ ትጠሪዋለሽ፤ እርሱም ታላቅ ይሆናል፤ የልዑል ልጅ ይባላል፤ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤ በያዕቆብ ቤትም ለዘለዓለም ይነግሣል፤
ለመንግስቱም መጨረሻ የለውም። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል? አለችው፤ መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት መንፈስ ቅዱስ በአንቹ ላይ ይመጣል፤ ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።

መልአኩም ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ካበሰራት በኋላ
 
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ
 
ነስቶ ወደዚህ ዓለም በመምጣት የአምላኩን ትዕዛዝ የተላለፈውን
 
አዳምን፤ ከገነት የተሰደደውን አዳምን፤ ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ
 
ከ5500 ዘመ ኩነኔ በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ ብሎ
 
በገባለት ቃል ኪዳን መሰረት ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ 
 
ተወለደ።  ከተወለደበት ከሕጻንነቱ ጀምሮ ታላቅ መከራና እንግልት
 
ደርሶበታል፤ ከእናቱም ጋር ወደ ግብጽ ሃገር ለመሰደድም በቅቷል።
 
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንደ ኦሪቱ መስዋእት ለማቅረብ
 
ወደ ኢየሩሳሌም በሄደችበት ወቅት አስቀድሞ ትንቢት የተነገረለትና
 
በጌታም የተቀባውን ሳያይ ሞትን እንዳያይ በመንፈስ ቅዱስ ተረድቶ
 
የነበረው ስምዖን ጌታን ታቅፎ ባረካቸው እናቱን ማርያምንም እንዲህ አላት እነሆ፥ የብዙዎች ልብ አሳብ ይገለጥ ዘንድ፥ ይህ በእስራኤል ላሉት ለብዙዎቹ ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው ለሚቃወሙትም ምልክት ተሾሞአል፥ በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል  ሉቃ 34፤35 በማለት እንደተናገረው ቃል ሔሮድስ ሰማያዊውን ንጉስ፤ ዓለማትን የፈጠረውን ጌታ፤ ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር ያስገኘውን አምላክ፤ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የምድራዊ ንጉስ በማድረግና፤ ንግስናውን የሚቀማው መስሎት ወይም ስልጣኔን ይወስድብኛል ብሎ በማሰብ እና በመፍራት እድሜያቸው ከሁለት አመት በታች የሆኑትን ሕጻናት በሙሉ እንዲገደሉ አዋጅ አስተላለፈ።  ወዲያውኑ አዋጁ ተግባራዊ ሆነ፤ አስቀድሞም በነቢያት የተነገረው ትንቢት ፍጻሜ ሆነ።  ነቢዩ ኤርምያስ 31፤15 ላይ እንዲህ ብሎ ጽፎ ነበር፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች የሉምና፤ ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች።  ንጉስ ሔሮድስም ብዙ ሕጻናትን በሚያስገድልበት ጊዜ የጌታ መልአክ በህልም ለዮሴፍ እንዲህ ብሎ አዘዘው፤ 

“ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑንና እናቱንም 
 
ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፥ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ አለው።
 
እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና ከጌታ ዘንድ በነቢይ
 
ልጄን ከግብፅ ጠራሁት የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብፅ ሄደ፥
 
ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ።” ማቴዎስ ወንጌል 2፤7-15

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሆና ሳለ፤
 
ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ ወደ ግብጽ በተሰደደች ጊዜ ስደቷ እጅግ መሪር
 
ነበር፤ እነሱም በከፊል

          *    ረሃቧ
 
          *     በጥም መንከራተቷ
 
          *     ልጄን ይገሉብኛል ብላ መፍራቷ፤ ድንጋጤዋ እና ስጋቷ
 
          *     የበረሃው ጉዞ (ሐሩሩ)
 
          *    ብርዱ የመሳሰሉት ብዙ ችግሮችን በመንገዷ ወይም በጉዞዋ 
 
               ወቅት       አሳልፋለች

እስራኤል ከግብጽ ምድር በሙሴ አማካኝነት ወጥተው ወደ ተስፋዋ 
 
ምድር በሚጓዙበት ጊዜ፤ ፈርኦን በብዙ ሰራዊት ታጅቦ ህዝበ 
 
እስራኤልን ተከትሏቸው ነበር ነገር ግን በእግዚአብሔር ቸርነት እና
 
ጠባቂነት እስራኤልን፤ የቀይ ባህርን ውሃ ከፍሎ ካሻገራቸው በኋላ
 
ፈርኦንን በማስጠም ከጠላት አድኖቸው እንደነበር ሔሮድስም
 
ጭፍሮቹን በመላክ ጌታችንን ይከታተለው ነበር። ሰይጣን በእባብ ላይ
 
አድሮ ከሔዋን ጋር በመነጋገር፤ ለአዳምና ለሔዋን ያዘነ በመምሰል፤
 
የፈጣሪያቸውን ትእዛዝ እንዲሽሩ ማለትም ከዛፏ ፍሬ እንዳይበላ
 
ከታዘዘው እንዲበላና ፍሬዋንም በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ
 
እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ 
 
እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ ብሎ በመዋሸትና ተሰናክለው
 
እንዲወድቁና የፈጣሪያቸውን ትእዛዝ እንዲተላለፉ በማድረግ 
 
ከአምላካቸው ጋር አለያይቶ ገነትን ያህል ቦታ እንዲዘጋባቸው እና 
 
ክብራቸውን ያጎደለባቸውን አዳምን አና ሔዋንን፤ ጌታችን ኢየሱስ 
 
ክርስቶስ ወደ ቀደመ ክብራቸው ገነት መንግስተ ሰማያትን 
 
እንዳይወርሱ የጥፋት አጀንዳውን እና ሴራውን በመቀየር የጥፋት 
 
ጥበብን በመጠቀም አሁንም በሔሮድስ ላይ አድሮ በጌታ መወለድ 
 
 ዓለም እንደሚድን አና የተዘጋው ገነት እንደሚከፈት ስለሚያውቅ 
 
ሕጻናትን ሁሉ በየአሉበት እንዲገደሉ አስደረገ።  የዚህ አይነት መራራ 
 
ጽዋ እጣ በልጇ ላይ እንዳይደርስባት እመቤታችን በከባድ ሃዘን እና 
 
ጭንቀት በረሃውን አቋርጣ ከእስራኤል ወደ ግብጽ ለመሰደድ በቃች። 
 የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስደት፤ ጉዞዋ መሪር የሆነ 
 
በጣም አስቸጋሪና የተወሳሰበ፤ ለመናገርም ሆነ ለመግለጽ ቃላት 
 
አይገኝለትም። የልጇ የወዳጇ የኢየሱስ ክርስቶስ እድሜው ሔሮድስ 
 
ለመግደል ባወጀው አዋጅ የእድሜ ክልል ውስጥ በመሆኑ እመቤታችን 
 
በስደት ጉዞዋ ወቅት ልጄን አሁን ገደሉብኝ እያለች በመስጋት እና 
 
በመጨነቅ፤ ሐዘኗ መሪር እና ከባድ እንደነበር አባቶቻችን መከራዋንና 
 
ስቃይዋን በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት ተረድተው በድርሰቶቻቸው 
 
ጽፈውልናል።  በተለይ በተአምረ ማርያም መጽሐፍ ላይ እመቤታችን 
 
በልጇ ምክንያት ያገኟትን ሐዘናት ሲገልጽ “አምስቱ ሐዘናት” ይለዋል። 
 
እነርሱም 
  1)    አረጋዊውስምኦን በቤተ መቅደስትንቢት በተናገረ ጊዜ ሉቃ 2፤34-35
   2)  በቤተመቅደስ ፈልጋ ባጣችው ጊዜ ሉቃ2፤41-48
  3)  በጲላጦስ አደባባይ በተገረፈ ጊዜ ዮሐ19፤1
  4)   በእለተ አርብ በሰቀሉት ጊዜ ዮሐ19፤17-22
  5)   ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ገንዘው ወደአዲስ መቃብር ባወረዱት 
 
        ጊዜ ዮሐ 19፤38-42

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages