ጊዮርጊስ ኃያል መስተጋድል - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Tuesday, November 1, 2022

ጊዮርጊስ ኃያል መስተጋድል

 



ለደካማውም ለብርቱውም ፣ለእርዳታ ፈጥነህ የምትደርስለት ጊዮርጊስ ሆይ፤ ደግነትህ በጎነትህ ከመጠን በላይ ነውናኖ። በአማላጅነትህ ለሚተማመኑትም ሁሉ ነፍስ፤ ዋስ ጠበቃ ነህ ። ከቂም በቀል ንጽሕ በመሆን እንደ ክብርት እመቤትህ እንደ ማርያም ርኅሩኅ ልብ ነህ።
ፍጡነ ረድኤት ጊዮርጊስ ሆይ፣
ከላይ ባለ በሰማይ ከታች ባለ በምድር በብዙ ወገን ለርዳታ ፈጥነህ አደራረስህ የኤፍራታ ርግብ የተባለችው እንደ እመቤትህ ማርያም ነው እኮን። በመሆኑም በእናትህ በቴዎብስትያ ስም እንደስምህ መንታነት የባለ ሟልነት ስምህን ትሰጠኝ ዘንድ ቃል ኪድን እንድትገባልኝ እማልድሃለሁ።
ፍጡነ ረድኤት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ፤ አንተን በመታመን ለጠራህ ሁሉ ፈጥነህ ስትደርስለት ከዓውሎ ነፋስ ይልቅ በተፋጠነ ሩጫ ነው እኮን።
ጊዮርጊስ ሆይ፤ የዘወትር ጸሎቴንና የቃሌንም የልመና ጩኽት ትቀበል ዘንድ ለይቅርታና ለምሕረት ፈጥነህ ወደ እኔ ቅረብ።
ፍጡነ ረድኤት ፈጥኖ ደራሹ ጊዮርጊስ ሆይ፤
ለጠላቴ መሳለቂያ አታድርገኝ ለሚተነኳኮሉኝም መሰደቢያ አታድርገኝ፤ ለክፉ ጐረቤቴም መዘባበቻ አታድርገኝ።
አባቴ ጊዮርጊስ ሆይ፤ የልቤን ኅዘን ስነግርህ ፈጥነህ ጸሎቴን ስማኝ ነገሬንም አድምጠኝ። ያዘኑትን የምታረጋጋ ሆይ፤ ወደኔ ቅረብ፤ በአጠገቤም ተገኝተህ አለሁልህ በለኝ።
ፍጡነ ረድኤት ፈጥኖ ደራሹ ጊዮርጊስ ሆይ፤ አሁንም ለጠላቴ መሣለቂያ አታድርገኝ። አባቴ ጊዮርጊስ ሆይ፤ የምነግርህን ባለመናቅ ተቀብለህ ልጄ ወዳጄ አገልጋዬ ታዛዤ ደረስኩልህ በለኝ።
ፍጡነ ረድኤት ፈጥኖ ደራሹ ጊዮርጊስ ሆይ፤ እንደ ወይን ጠጅ ልብን ደስ የምታሰኝ ነህ እኮን። ኅዘንን ታስረሳለህና።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ፤ ልመናችንን ፈጥነህ ስማ። በባሕር ላይ የምንንሳፈፈውን በየብስ የምንነጉደውን ሁሉ ፈጥነህ እርዳን እምነታችን በአንተ ላይ አድርገናል።
የእግዚአብሔር እውነተኛ ምስክሩ ፈጥኖ ደራሹ ሰማዕት ኃይሉ ጊዮርጊስ ሆይ፤ በየዕለቱ እርዳታህ አይለየኝ። የዚህ ዓለም ነጋዴ ያለትርፍ መውጣት መውረድ ከንቱ ድካም ነውና።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages