በሕማማት የሚጸለዩ ፀሎቶች ምን ምን ናቸው?
በሕማማት ወቅት የሚሰሙ የምንላቸው ከሌላ ቋንቋ የተወሰዱ ቃላት ትርጉም
የ41 ስግደት ምን እየተባለ ነው የሚሰገድ? ና የመሳሰሉ ጥያቄ መልሶች፦። #ይነበብ
፨ +የሕማማት ጸሎት
+ጥብጠባ፡-
በሰሙነ ሕማማት እለተ ዓርብ ስቅለቱ መታሰቢያ ነው፡ ምእመናኑ በሰሙነ ሕማማት የሰሩትን ይናዘዛሉ ካህናቱን በወይራ ቅጠል ትከሻቸውን እየጠበጠቡ ስግደት ያዟቸዋል፡፡ ጥብጠባው የተግሳፅ ምሳሌ ነው፡፡
ይህ በስቅለተ ቀን የሚፈጸም ስነ ስርዓት ሲሆን ጥብጣቤ ማለት ቸብ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ይህም የጌታን ግርፋት ያሳያል።፡ሕዝብ ክርስቲያኑ በእለተ ስቅለት ሲሰግድ ሲጸልይ ሲያነብ ከዋለ በኋላ ሰርሆተ ሕዝብ ይሆናል። አርብ ከ 11 ሰአት በኋላ ስግደት እንደሌለ ግብረ ሕማሙ "አልቦ ስግደት "ይላል።
፨ + በሕማማት ወቅት የሚሰሙ የምንላቸው ከሌላ ቋንቋ የተወሰዱ ቃላት ትርጉም:-
በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡
"ኪርያላይሶን"
ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ “ኪርዬ ኤሌይሶን” ነው፡፡ “ኪርያ” ማለት “እግዝእትነ” ማለት ሲሆን “ኪርዬ” ማለት ደግሞ “እግዚኦ”ማለት ነው፡፡ ሲጠራም “ኪርዬ ኤሌይሶን” መባል አለበት፡፡ ትርጉሙም “አቤቱ ማረን” ማለት ነው፡፡ “ኪርያላይሶን” የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው “ዬ”ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ “ኤ” በመሳሳባቸው በአማርኛ "ያ"ን ፈጥረው ነው፡፡
"ናይናን"
የቅብጥ(ጥንታዊው የግብጻውያን ) ቃል ሲሆን ትርጉሙ “መሐረነ፣ ማረን” ማለት ነው፡፡
"እብኖዲ"
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ “አምላክ” ማለት ነው፡፡ “እብኖዲ ናይናን” ሲልም “አምላክ ሆይ ማረን” ማለቱ ነው
"ታኦስ"
የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ “ጌታ፣ አምላክማለት ነው፡፡ “ታኦስ ናይናንማለትም “ጌታ ሆይ ማረን” ማለት ነው፡፡
"ማስያስ"
የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ “መሲሕ” ማለት ነው፡፡ “ማስያስ ናይናን” ሲልም “መሲሕ ሆይ ማረን” ማለት ነው
"ትስቡጣ"
ደግ (ቸር) ገዥ ማለት ሲሆን "ትስቡጣ ናይናን" ማለት ቸር ገዥ ማረን ማለት ነው።
"አምንስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ"
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ” ማለት ነው፡፡
"አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ"
የቅብጥ ቃል ሲሆን “ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን” ማለት ነው
"አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ"
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ፤የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን” ማለት ነው፡፡
No comments:
Post a Comment