አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ከሰባ ሁለቱ አርድእትም የተቆጠረ ሆነ የመንፈስ ቅዱስንም ሀብት ከሐዋርያት ጋራ ተቀበለ ከእርሳቸውም ጋራ ታላቅ መከራ ደርሶበታል።
ከዚህ በኋላ ሐዋርያት በአንብሮተ እድ ኤጲስቆጶስነት ሹመው ከእንድራኒቆስ ጋራ በአገሮች ውስጥ እንዲሰብክ ላኩት።
እንድራኒቆስም በአለፈው ዕለት በአረፈ ጊዜ ይህ ቅዱስ ዮልዮስ ገንዞ ቀበረው ። ከዚህ በኋላ ከርሱ እንዳይለይ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ በማግሥቱ ዛሬ አረፈ።
እነሆ የከበረ ሐዋርያ ጳውሎስም እሊህን ሐዋርያት በሮሜ ክታቡ ዕንድራኒቆስንና ዮልዮስን ሰላም በሏቸው ሲል አስታውሷቸዋል።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
በዚህችም ዕለት ሰማዕታት የሆኑ የአንስያ ከሰባ ሁለቱ አርድዕት የአንዱ የአፍሮዲጡ የዮልያና የቀሲስ ታኦድራጦስ የጳጳስ ታድሮስ የዮልያኖስን የእናቱ የእስክንድርያ የሆኑ ደግሞ የኤስድሮስ የሚስቱና የሁለት ወር ልጅዋ እኔ ከእናቴ ጋራ ክርስቲያን ነኝ ብሎ የተናገረና ዲዮቅልጥያኖስ የገደላቸው ለእነርሱም ማኅበር መታሰቢያቸው ሆነ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባቶቻችን ሐዋርያት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ምንጭ፤ ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት
No comments:
Post a Comment