ብጹዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በፈለገ አእምሮ መንፈሳዊ ት/ቤት ጉብኝት አደረጉ። - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Saturday, June 17, 2023

ብጹዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በፈለገ አእምሮ መንፈሳዊ ት/ቤት ጉብኝት አደረጉ።

 ሰኔ 10 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ)

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የከምባታ ፣ ሀድያ፣ ስልጤ እና የደቡብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ዶ/ር ኢንጂነር መሰለ ኃይሌ በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ስር የሚገኘውን የመቄት ወረዳ ቤተ ክህነት የአስፋ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈለገ አእምሮ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ጎብኝተዋል።
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቄት ወረዳ ቤተ ክህነት ስር የሚገኙትን ጉባኤ ቤቶችንና በግንባታ ላይ የሚገኘውን ባለ 9 ወለል (B+G+7) ሁለገብ ሕንፃ የጎበኙ ሲሆን ለጉባኤ መምህራን፣ ደቀ መዛሙርትና አስተዳደር ሠራተኞች ቃለ ምእዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል።
አስፋ ገነተ ጽጌ ፈለገ አእምሮ አዳሪ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት በአምስት ጉባኤ ቤቶች ከ80 በላይ ደቀ መዛሙርትን ተቀብሎ እያስተማረ እንደሚገኝ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ዘግቧል።










ምንጭ፤ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል


No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages