በግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በናቃዳ ሀገረ ስብከት የቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን የእሳት አደጋ መከሰቱ ተገለጸ ! - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Saturday, June 17, 2023

በግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በናቃዳ ሀገረ ስብከት የቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን የእሳት አደጋ መከሰቱ ተገለጸ !

ሰኔ 9 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

በናቃዳ ሀገረ ስብከት በቁስ "አዋል አል-ሹሃዳ" ካቴድራል ላይ የእሳት አደጋ መከሰቱን ሀገረ ስብከቱ አስታውቋል።
ሀገረ ስብከቱን ጠቅሶ ኮፕቲክ ሚዲያ ሴንተር እንደዘገበው ከሆነ የደረሰውን የእሳት አደጋ የሰው ሕይወት ሳይጠፋ መቆጣጠር መቻሉ ተገልጿል።
እንደ ዘገባው የቁስ ከተማ የሲቪል ጥበቃ ቅርንጫፍ ኃላፊ ካፒቴን ኦሳማ ሃምዲ በተገኙበት እና ክትትል በማድረግ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በሲቪል ጥበቃ ሃይሎች እና የእሳት አደጋ ሠራተኞች እሳቱን መቆጣጠር ተችሏል የተባለ ሲሆን ወደ ስፍራው በፍጥነት የሄዱትን የጸጥታ ሃይሎች እና የእሳት አደጋ ሠራተኞችን አመስግኗል።
በግብፅ ኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተደጋጋሚ የእሳት አደጋዎች እየደረሱ እንደሚገኙ ለመታዘብ የሚቻል ሲሆን ቤተ ክርስቲያኒቱም ሆነች የሀገሪቱ መንግስት በጉዳዩ ላይ የመፍትሔ እርምጃ ለመውሰድ እየሰሩ እንደሆነ ማረጋገጥ አልተቻለም።


No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages