ጩጌ ማርያም ገዳም - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Wednesday, June 28, 2023

ጩጌ ማርያም ገዳም


አጽማቸው የማይፈርስ ፍየሎች የሚገኙባት ገዳም።
ጩጌ ማርያም ከጎንደር ከተማ በስተሰሜን በኩል 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ተጉዘን በወገራ ወረዳ አካባቢ የኮሶየ አምባ ራስ ቀበሌን አልፈን ወደ ገዳማቱ ለማምራት የዘጎል አምባን፡የጅብ ዋሻን ጥቅጥቅ ያሉ ደኖችን አልፈን ወደ ምስራቅ ስንታጠፍ በተፈጥሮ ክብ ቅርፅ ያለውን ቤተ ክርስቲያን መስሎ የሚታየውን ተራራ እናገኛለን።
በዚህ ተራራ ላይ አባ ምዕመን ድንግል የገዳም ህይወታቸውን እንዳሳለፉ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ።
በተራራው ማየ ዮርዳኖስ ፀበልና ዋሻ ቅዱስ ሩፋኤል ክርስቲያን እናገኛለን ቤተ ክርስቲያኑ ቅድስትና መቅደስ ያለው ሲሆን በቅድስቱ ማየ ዮርዳኖስን ያለ ሲሆን ይህን በመጠጣታቸው ስጋቸው ያልፈረሰ የፍየል አፅሞች ይገኛሉ። በዚህም በአመት አንድ ጊዜ ብቻ ጳጉሜ 3 ይቀደሳል።
የጩጌ ማርያም ገዳም በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተመሰረተ ጥንታዊ ገዳም ሲሆን የመሰረቱትም አባ ምእመነ ድንግል የተባሉ ጻድቅ ናቸው፡፡ ገዳሙም ጻድቁ የጸለዩበት እና ከጌታችን ከመድኀኒታች ከኢየሱስ ክርስቶስ ቃልኪዳን የተቀበሉበት ቅዱስ ቦታ ሲሆን የጻድቁ በዓት መጸለያ ዋሻም በስማቸው “ምእመነ ድንግል” እንደተባለ አለ፡፡
ጻድቁም በሕይወት እንደነ ሄኖክ፣ ኤልያስ፣ ቅዱስ ያሬድ እና አባ ዮሃኒ በህቡእ አሉ ተብሎ ይታሰባል ፡፡የጻድቁ መጸለያ ቦታ በተፈጥሮው የተሸነቆረ መስኮት አለው፡፡ በዚህ ቦታ ላይ መኻን የሆኑ ሁሉ በመስኮቱ ወጥተው ሲመለሱ ማየ ዮርዳኖሱን ጠጥተው ሲሳሉ ልጅ ለማግኘት ይበቃሉ፡፡ ይህን ቃል ኪዳን የሚያውቁ ጳጉሜን በሙሉ በማየ ዮርዳኖሱ በመጠመቅ ትልቅ ሐብተ ፈውስ ያገኛሉ፡፡
የዮርዳኖሱን ጸበል የጠጣ ሲሞት ሥጋው አይፈርስም፣ አይበሰብስም፡፡ እንኳን በአርአያ ሥላሴ የተፈጠረው ሰው እንስሳቱ እንኳን አካላቸው ሳይፈርስ ይቆያል፡፡ ለማስረጃ ያህል እንኳን 16 የሚሆኑ ፍየሎች አካላቸው ሳይፈርስ 400 ዘመን ያስቆጠሩ አሉ፡፡
ገዳሙ የወንዶችና የሴቶች ተብሎ በሁለት የተከፈለ ሲሆን ቤተ ክርስቲያኑ በወንዶች ገዳም በኩል ሲገኝ ወደ ሴቶቹ ገዳም ስናመራ ደግሞ አንድ ትልቅ የችብሀ ዛፍ ወድቆ እንደተነሳ ይኸውም ከሰው ልጅ ሞቶ መነሳት ጋር የተያያዘ እግዚአብሔር ተአምራትን አሳይቶበታል። ዛፉ ከ15ዓመት በሗላም እንደገና እንደወደቀና በስሩ የፈለቀው ፀበልም ህመምተኞችን እየፈወሰ እንደሚገኝ አባቶች ያስረዳሉ።
የገዳሙን ተራራ የወጣ ሰው እስከ 3000 እንደሰገደ ይቆጠርለታል የሚል ቃልኪዳን አላቸው።
✥ከጩጊ ማርያም ገዳም ረድኤት በረከት ያሳትፈን። ደጇን ተሳልመን በረከት እንድናገኝ የአምላካችን ቅዱስ ፍቃድ ይሁንልን።
ዓመታዊ ክብረ በዓሏም በነገው እለት ሰኔ 21 በደማቅ ይከበራል።







No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages