ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ 18 - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Friday, February 23, 2024

ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ 18

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ነሐሴ 18 በዚህች ቀን እለእስክንድሮስ አረፈ፤ታሪኩ እንዲህ ነው ተፍጻሜ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ 3 ደቀመዛሙርት ነበሩት “ወልድ ፍጡር” ብሎ የተነሳው አርዮስ፤አኪላስና ዛሬ መታሰቢይውን የምናደርግለት እለእስክንድሮስ ናቸው። አርዮስ ትውልዱ ዛሬ በጦርነት ከምትታመሰው ከጋዳፊ አገር ከሊቢያ ነው። ዲቁናውን የተቀበለው ከመምህሩ ከጴጥሮስ ነበር፤በኃላ አርዮስ ኑፋቄውን ሲያመጣ ቅዱስ ጴጥሮስ አወገዘው፤ቅዱስ ጴጥሮስ ሊሞት አኪላዎስ ሊቀጳጳስ ሆነ አርዮስንም ከግዝቱ ይፈታዋል ቅስናም ይሾመዋል፤ ነገር ግን በወንበሩ 6 ወር ብቻ ነው የቆየው እርሱ ይሞትና እለእስክንድሮስ ሊቀጳጳስ ይሆናል አርዮስንም ድጋሚ ያወግዘዋል፤ አርዮስም

“ ክህደቴን ትቼ ወደአባቶቼ ሀይማኖት ተመልሼ ነበር እለእስክንድሮስ ያለአግባብ አወገዘኝ ” ብሎ ክስ ይጀምራል፤ ንጉሱም ለምን አወገዝከው ይለዋል፤እኔ ብቻ ሳልሆን 318ቱ ሊቃውንት አባቶቼ ናቸው ያወገዙት ነግር ግን በትክክል ከተመለሰ ወረቀት ላይ ይጻፍሊኝ ይላል፤ አርዮስም ይጽፍለታል ከልቡ ግን አልነበረም፤ንጉሱም አሁን ምንም ምክንያት የለህም ከግዝቱ ፍታው ይለዋል፤በዚህ ጊዜ እለእክንድሮስ በጣም ይጨነቃል፤አንድ ሳምንት ብቻ ስጠኝ ይለዋል፤ ንጉሱም እሺ ሌላ ምክንያት ግን አልቀበልም ይለዋል፤ እለእስክንድሮስ በዚህ ጊዜ አባቶችን ሰብስቦ በጉዳይ ላይ ይወያያሉ፤በትክክልም ከተመለሰ ቀድሶ ያቁርብ ብለው ይወስናሉ፤ አርዮስ ሊቀድስ ገባ አሐዱ አብ ቅዱስ ብሎ አሐዱ ወልድ ቅዱስ ሊል ሲል ሆዱን ያመዋል ወደ ውጪም ይወጣል አንጀቱ ተዘርግፎም ይሞታል፤ታሪክ እጅግ በጥቂቱ እስከዚህ ድረስ ነው፤ አባታችን እለእስክንድሮስ የእስክንድርያ ሊቀጳጳስ ሆኖ ለ 22 ዓመት ከ 10 ወር መንጋውን በፍቅር ሲመራ ቆይቶ በዛሬዋ ቀን አረፈ።
ነሐሴ 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ተዝካረ ፍልሠታ ለማርያም ድንግል (3ኛ ቀን)
2.ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ
3.ቅዱስ እንድራኒቆስ ዲያቆን
4.አባ ዘክርስቶስ ዘወሎ (ኢትዮዽያዊ ጻድቅ)
ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን)
3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
4.ማር ያዕቆብ ግብፃዊ
5.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኩአችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ:: (ይሁዳ. 1:3)

የአባቶቻችን በረከት ይደርብን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages