በእግዚአብሔር ማደሪያ በታቦቱ ላይ ማላገጥ ያስቀስፋል - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Tuesday, January 28, 2025

በእግዚአብሔር ማደሪያ በታቦቱ ላይ ማላገጥ ያስቀስፋል

"የእግዚአብሔርም ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በገባ ጊዜ የሳዖል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች፥ ንጉሡም ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ሲዘልና ሲዘፍን አየች፤ በልቧም ናቀችው። እስከ ሞተችበት ቀን ድረስ ልጅ አልወለደችም።" 2ኛ ሳሙ.6:16

ፕሮቴስታንቲዝም በአስተሳሰብ ደረጃ የምጸየፈው ለክርስትና ሃይማኖት አውዳሚ አመለካከትን የሚያስታጥቅ በመሆኑ ነው።

አምቦ ዩኒቨርሲቲ‼
በጣም አሳፋሪና ንቀት የተምላበት የአምቦ ዩንቨርሲቲ ሦስቱ ተማሪዎች ተግባር‼️
የሃይማኖት መቻቻል እና እኩልነት ባለባት ኢትዮጵያ ምድር ላይ እነዚህ 3 ልጆች በእግዚአብሔር ማደሪያ ታቦት ላይ እንደዚህ መቀለድ በሰማይም በምድርም ያስቀጣል።
ከኢትዮጵያዊነት ባፈነገጠ መልኩ ብዙ ሚሊዮን ተከታዬች ያለውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት የሆነውን የቅዱስ ሚካኤልን ታቦት በማሾፍ በማፌዝ መልኩ ቪዲዮ ሰርተው በቲክ ቶክ በሚባለው አፕ ለቀዋል::
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት እነዚህ ልጆች የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ሲሆኑ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት፤ የአምቦ ዩኒቨርስቲ ሃላፊዎች አጣርተው እነዚህን ልጆች ለሕግ እንዲያቀርብ ብዙ ኢትዮጵያውያን እየተማፀኑ ይገኛል::

እሳቤው በአጠቃላይ ፀረ ሃይማኖት፣ ኢምክንያታዊ፣ ፀረ ክርስትና፣ ፀረ ሥርዓት፣ ፀረ ትውፊት፣ ፀረ ባሕል፣ ፀረ ታሪክ፣ ፀረ ማንነት፣ ፀረ ግብረ ገብነት፣ ፀረ ሰውነት ነው። የመከባበር አውዳሚ እሳቤን የተሸከመ ነው። ግለሰብ ተመልክቼ አይደለም እንዲህ የምለው፤ የጴንጤ አብዛኛው አስተምህሮ እጅግ መርዘኛና የማኅበረሰብ እሴትን በጣጥሶ የሚጥል አፍራሽ በመሆኑ ነው። እንዴት እንጥፍጣፊ የሕሊና ልጓም በዚህ ደረጃ አጣን?
ግለሰቦቹን በሕግ ማን ይጠይቃቸዋል? አንድ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም ብዙ ተመሳሳይ ቪዲዮ ሠርተዋል።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages