በምሥራቅ አርሲ አሰኮ ወረዳ 3 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸው ተገለጸ። - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Wednesday, July 15, 2026

በምሥራቅ አርሲ አሰኮ ወረዳ 3 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸው ተገለጸ።

 


በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት አሰኮ ወረዳ ባሕሩ አሊ በተባለ ቦታ ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም 2 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገልጸዋል።
በዕለቱ ከምሽቱ 5ሰዓት እስከ 6ሰዓት በተከፈተባቸው የተኩስ እሩምታ ምክንያት የአካባቢው ነዋሪዎች ሕይወታቸውን ለማዳን ከቦታው የሸሹ ሲሆን ወ/ሮ አልማዝ የሻነህ እና ወንድ ልጃቸው በግፍ መገደላቸውንና በአሰኮ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መቀበራቸውን ገልጸዋል።
ሐምሌ 5ም ዳኛም የለው በሚባል አካባቢ የ90 ዓመት አዛውንት በግፍ መገደላቸውን የገለጹት ምንጫችን አካባቢው አሁንም ሥጋት ውስጥ እንደሚገኝና ነዋሪዎቹም ቦታውን ለቅቀው እየሸሹ መሆናቸውን አሳውቀዋል።
Source: EOTCMK TV ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም

ይህን ዜና ተከትሎ ከቤተ ክርስቲያን መምህራን አንዱ ዶክተር አረጋ አባተ የሰጠውን አስተያየት ከዚህ በታች አቅርቤዋለሁ፤
እነ አባ ቤዛ፣ የከተማ መነኮሳት ይኸንን የቤተ ክርስቲያን ግፍና ጭፍጨፋ ማስቀጠል ነው የሚፈልጉት፡፡
እንዲህ የሞቱ ኦርቶዶክሳውያንን እየቆጠርን ልንቀጥል አንችልም፡፡ በከተማ መነኮሳት ሥር የወደቀውንና ሽባ የሆነውን የቤተ ክርስቲያን መዋቅር እውነተኞቹ መነኮሳት፣ ለማንም ሳይሆን ለእውነት የሚኖሩ መነኮሳት ጳጳሳት ሲሆኑ ይኸንን መከራ በራሳችን ኃይል ማስቆም እንችላለን፡፡
ከዚያ ውጭ ይኸንን ሥርዓት በመለመን የሚመጣ ለውጥ፣ የሚቆም የቤተ ክርስቲያን ስደት የለም፡፡ ራሳችንን አጽድተን ራሳችንን እንከላከላለን፡፡ ይኸ የራስ ወደድ የደለቡ ጥጋበኛ የከተማ መነኮሳት ስብስብ ከጠላት እንደማያስጥለን ተፈትኖ ታይቷል፡፡
የሰማዕታቱ በረከት ይደርብን!


No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages