የዶንኪ ቲዩብ ለአብዛኛው ኢትዮጵያውያን አንድነትን፤ ፍቅርን፤ መረዳዳትን ከማስተማርም በላይ ሃይማኖት ሳይለይ ለሁሉም ይረዳ እንደነበር ሁላችንም እናውቃለን። እኔ የዶንኪ ቲዩብ ዋና ተከታታይ ከመሆኔም በላይ ብዙ የተማርኩበት፤ የእሸቱን ቅንነትና በሃይማኖቱ ጠንካራ መሆኑን የተረዳሁበት ሰው ነው። ስለዚህ የእሸቱን መልካም ምግባር የሚቃወሙና በቅናት መንፈስ የእሱን ስራ ለማፈራረስ የሚጥሩ ከመብዛታቸው የተነሳ አይዞህ ብለን ልንደግፈው ይገባል። እንቅልፍ አጥቶ ለቤተ ክርስቲያን ብዙ ሥራ የሰራ መሆኑን ማስታወስ ይገባል። እናግዘው። ወንድማችን እሸቱ እንወድሃለን በርታልን።
No comments:
Post a Comment