ቅዱስ ሲኖዶስ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የቀጣይ ዓመት መደበኛ በጀት 7.1 ቢሊዮን ብር አጸደቀ።
ኢኦተቤ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
ግንቦት ፬ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
የ፳፻፲፰ ዓ.ም ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዛሬው አምስተኛ ቀን ስብሰባ በአራት አጅንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ማሳለፉን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በዕለታዊ መግለጫው አሳውቋል።
ከነዚህ መካከልም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የቀጣይ ዓመት የበጀት ዕቅድ አንዱ ነው።
በመሆኑም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይቤተ ክህነት ጽ/ቤት ለ2019 ዓ·ም በጀት ዓመት ገቢና ወጪ ሒሳብ አስመልክቶ ከበጀትና ሒሳብ መምሪያ የተዘጋጀ ዓመታዊ መደበኛ የበጀት ዕቅድ 46 ገጽ የተመለከተ ሲሆን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከበጀትና ሒሳብ መምሪያ የተዘጋጀውን ዓመታዊ የበጀት ዕቅድ በንባብ አዳምጦና ከጉባኤው በቀረቡት ጥያቄዎች የባለሙያዎችን ምላሽ ከሰማ በኋላ በጉዳዩ ላይ በስፋት ተነጋግሮ የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፏል፡፡
በውሳኔውም መሠረት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ያቀረበው የ2019 ዓ·ም በጀት ዓመት ከነመጠባበቂያው ብር7,101,018,660.16 (ሰባት ቢሊየን አንድ መቶ አንድ ሚሊየን አሥራ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ብር ከአሥራ ስድስት ሣንቲም) በበጀት ዓመቱ የበጀት አርዕስቱን ጠብቆ በሥራ ላይ እንዲውል የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መወሰኑን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል (ረ/ፕ) ለ EOTCTV በሰጡት ዕለታዊ ማብራሪያ አስታውቀዋል ።
ምንጭ፡ © EOTC t.v.
Post Top Ad
Thursday, July 9, 2026
Home
ዜና ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ሲኖዶስ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የቀጣይ ዓመት መደበኛ በጀት 7.1 ቢሊዮን ብር አጸደቀ። ኢኦተቤ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
ቅዱስ ሲኖዶስ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የቀጣይ ዓመት መደበኛ በጀት 7.1 ቢሊዮን ብር አጸደቀ። ኢኦተቤ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Post Bottom Ad
Author Details
Templatesyard is a blogger resources site is a provider of high quality blogger template with premium looking layout and robust design. The main mission of templatesyard is to provide the best quality blogger templates which are professionally designed and perfectlly seo optimized to deliver best result for your blog.

No comments:
Post a Comment