አንዳንዱ ክህነቱ ተይዞ ምዕመን ሆኖ መኖር (ለእሱም ከበቃ) ሲኖርበት የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ሆኖ ሲመጣ ስመለከት አዝናለሁ። የሚገርመው ደግሞ ሰውየው ያሰማራው ዲጂታል ሰራዊት የውዳሴ ዶፍ እያወረዱለት ነው። የገጽታ ግንባታ መሆኑ ነው።
አየር ጤና መካነ ስብሐት ቅዱስ ሩፋኤልና ቅድስት ልደታ ቤተክርስቲያን አጥቢያዬ ነው። የማስቀድስበት፣ኪዳን ማደርስበት፣በየለቱ የምሳለመው ደብሬ። ፍልሰታን ተረጋግቼ እዚሁ ላሳልፍ አስቤ ነበር። ይህን ሰውዬ እያየሁ ግን የምችል አይመስለኝም። ሌላ ደብር ሔደን እናሳልፋለን። ለእኛ ለምዕመናን ይህ ትልቅ ፈተና ነው። ትልቅ የመሰናክል ድንጋይ ነው። የከተማ መነኩሴ ቤተክርስቲያንን ሊያጠፋት ነው። ከገንዘብና ከፖለቲካ ንክኪ በቀር ቤተክርስቲያንን ማያውቁ ወሮበላዎች እጅ ወደቀች። ይህን መታገል የልጅነት ግዴታችን ነው።
ምንጭ፤ ወልደ ሥላሴ ኪዳኔ (ፌስ ቡክ)
No comments:
Post a Comment