ቪዲዮውን ተመልከቱ!!! ዓለምን ንቀው በገዳም ተወስነው የሚኖሩት መነኮሳት ተጨፈጨፉ። አረጋ አባተ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Thursday, July 23, 2026

ቪዲዮውን ተመልከቱ!!! ዓለምን ንቀው በገዳም ተወስነው የሚኖሩት መነኮሳት ተጨፈጨፉ። አረጋ አባተ

 በአረጋ አባተ የተጻፈ 

ምንጭ፤ አረጋ አባተ ፌስቡክ 


አሁን ያለው የቤተ ክርስቲያን መዋቅር፣ ታላላቅ ለገዳማት ጭፍጨፋ፣ ለአብነት ትምህርት ቤቶች ጭፍጨፋ፣ መነኮሳትን እልቂት፣ ለኦርቶዶክሳውያን ሞትና መፈናቀል ግድ የማይሰጠው ለምን ይመስልሃል? ጳጳሳቱ፣ የከተማ መነኮሳቱ፣ ሊቃውንቱና መላው አገልጋይ ጭምር ለሕዝቡ እልቂት ትንፍሽ የማይለው ለምን ይምስልሃል?
ቁልፉ ያለው ጠቅላላው መዋቅር በጨካኝ የከተማ መነኮሳት የሚዘወር በመሆኑ ነው፡፡ መዋቅሩ የአመራር ብቃት ባላቸው፣ በተማሩና ለቦታው በሚመጥኑ ሰዎች እንዳይያዝ ጨምድደው የያዙት ደና*ቁርት፣ ያልተማሩ፣ የማያምኑ እና ራስ ወዳዶች ያለቦታቸው ስለተቀመጡ ነው፡፡
እነዚህ ወንጀለኞች ችግራቸው ቃል ኪዳን ማፍረሳቸውና የማይገኛቸው ቦታ ላይ መገኘታቸው ብቻ አይደለም፡፡ ያለቦታቸው የተገኙ ከመሆናቸው አንጻር አብዛኞቹ እምነትም፣ ፈሪሃ እግዚአብሔርም የላቸውም፡፡ ቀሚሱን የሚለብሱት፣ ቆቡን የሚያጠልቁት ሳይገባቸው በውምብድና ነው፡፡ እነዚህ ውምበዴዎች ሕዝቡ ቢያልቅ አንድ ሰው እስከሚቀር ድረስ ሥልጣኑን ጨምድደው በመጨረሻም ቤተ ክርስቲያንን በሐራጅ ሽጠው መሞት የሚፈልጉ አጥፍቶ ጠፊዎች ናቸው፡፡
እነሱ መዋቅሩ ላይ እስካሉ ድረስ ቤተ ክርስቲያን አትታፈሩም፣ አትፈራም፣ አትሰማም፣ ድምጽም የላት፡፡ እንዲያውም ከገዳዮች፣ ከጨፍጫፊዎች እና ከአሳዳጆች ወገን ሆነው ጭፍጨፋውንና ማሳደዱን ያጠናክራሉ ካልሆነም ይክዳሉ፡፡ በታሪክም የሆነው አሁን እየሂነ ያለው ይኸ ነው፡፡ እነሱ እስካሉ ድረስ እስከዛሬ ከሆነው አሁን እየሆነ ካለው የተለየ ነገር መጠበቅ ሲበዛ ሞኝነት ነው፡፡
ዳሩ ግን ቁርጠኝነት ይጠይቃል እንጂ መፍትሔው በእጃችን ነው፡፡ ሥርዓተ ምንኩስናን ማስከበር፣ መዋቅሩን በሚገባቸው ሰዎች ማስያዝ፡፡ አለቀ፡፡ ያኔ አቅማችን በሕዝባችን ልክ፣ በአስተዋጽአችን ልክ፣ በታሪካችን ልክ ይሰፋል፡፡ ማንም መንገደኛ መቀለጃ አያደርገንም፡፡ የሚፈራ፣ ጥርስ ያለው፣ ራሱን የሚያስከብር መዋቅር ሊኖረን የሚችለው ወንጀል በሌላቸው፣ ታሪካቸው ባልተበላሸ ገዳማውያን አባቶች የሚመራ ሲኖዶስ ሲኖረን ብቻ ነው፡፡ ያንን ለማድረግ ደግሞ ምንጩን ገዳምንና ገዳማውያንን እንዲሁም ምንኩስናቸውን መጠበቅ አለብን፡፡ ይከ ትግል ዐላማው ይኸ ነው፡፡
ይኸ ትግል የተበላሸውን ጥንታዊ ሥርዓት ወደ ቀድሞ ማንነቱ መመለስ ነው፡፡ ካድሬዎችን ከመቅደስ የመንቀል ነው፡፡ ሥጋውያንን ወደ ሥጋ ሥራቸው ማስገባትና መንፈሳውያንን ለመንፈሳዊ አገልግሎት ማብቃት ነው፡፡ የተደበላለቀው የሚጠራው በቀኖና በሥርዓትና በትውፊት መሠረት ስንመራ ብቻ ነው፡፡
ስለሆነም ትግላችን የከተማ መንኮሳት መንቀልና ማጭበርበራቸውን ማስቆም መሆን አለበት፡፡
ይኸው ነው፡፡

ምንጭ፤ አረጋ አባተ ፌስቡክ 



No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages