ባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ለአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ስልጠና መስጠት ጀመረ።
EOTCMK TV ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም
የባሕር ዳር እና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ስልጠናውን በአባታዊ መመሪያና ቡራኬ በከፈቱበት ወቅት ስልጠናው አዲስ እውቀት የሚማሩበት ብቻ ሳይሆን ከአሁን በፊት ያገኙትን መሠረታዊ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትምህርትና ሥርዓት መሠረት ያደረገ አስተደደራዊ ክህሎትን ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል።
ብፁዕነታቸው በተጨማሪም ለሰልጣኞች ባስተላለፉት መልእክት ቅዱስ ጳውሎስ ለቲቶ የጻፈለትን መልእክት በማስታወስ አስተዳዳሪዎች በመልካም ሥራቸው ለሌሎች አርዓያና ምሳሌ መሆን እንዳለባቸው አጽንዖት ሰጥተው አሳስበዋል።
ስልጠናው ከሐምሌ 1 ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ መሆኑን ከሀገረ ስብከቱ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል የተገኘው መረጃ ያሳያል።
Post Top Ad
Thursday, July 9, 2026
ባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ለአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ስልጠና መስጠት ጀመረ። EOTCMK TV ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Post Bottom Ad
Author Details
Templatesyard is a blogger resources site is a provider of high quality blogger template with premium looking layout and robust design. The main mission of templatesyard is to provide the best quality blogger templates which are professionally designed and perfectlly seo optimized to deliver best result for your blog.




No comments:
Post a Comment