ስባት ፯ ቁጥር በቤተ ክርስቲያን - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Friday, April 24, 2020

ስባት ፯ ቁጥር በቤተ ክርስቲያን


ስባት ፯ ቁጥር በቤተ ክርስቲያን ፯ቁጥር በአይሁድ ሙሉ ቁጥር ነው ስባት የሚጠሉ ነገሮች ========== 1 ትዕቢተኛ አይን 2 ሀስተኛ ምላስ 3 ንፁ ህ ደም የምታፈስ እጅ 4 ክፉ ሀሳብን የምታፈልቅ ልብ 5 ወደ ክፉ የምትሮጥት እግር 6 በሀስት የሚናገር ሀሰተኛ ምስክር 7 በወንድማማቾች መካከል ጠብን የሚዘራ ሰባት አባቶች ====== 1 ልዑል እግዚያብሄር 2 የንስሀ አባት 3 ወላጅ አባት 4 የክርስትና አባት 5 የጡት አባት 6 የስልጣን አባት 7 የቀለም አባት ሰባት ስማያት ====== 1 ጽርሐ አርያም 2 መንበረ መንግስት 3 ሰማይ ወጹድ 4 ሰማያዊ ኢየሩሳሌም 5 ኢዩር 6 ራማ 7 ኤረር ስባት አጽርሐ መስቀል ========== 1 አምላኬ ሆይለምን ተወከኝ 2 አባተ ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁትምና ይቅር በላቸው 3 እውነት እልሀለሁ ዛሬ እኔ ካንተ ጋር በገነት እሆናለሁ 4 አንቺ ሴት እነሆ ልጅሽ እናትህ እንኋት 5 ተጠማሁ 6 ተፈጸመ 7 አባት ሆይ ነፍሴን በእጄ አደራ እስጣለሁ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት ========== 1 ቅዱስ ሚካኤል 2 ቅዱስ ገብርኤል 3 ቅዱስ ሩፋኤል 4 ቅዱስ ራጉኤል 5 ቅዱስ ዑራኤል 6 ቅዱስ ፋኑኤል 7 ቅዱስ ሳቁኤል ስባቱ እኔ ነኝ ብሎ ጌታ የተናገረው ቃላት ==================== 1 የእይወት እንጀራ እኔ ነኝ 2 የዓለም ብርሀን እኔ ነኝ 3 እኔ የበጎችበር እኔ ነኝ 4 መልካም እረኛ እኔ ነኝ 5 ትንሳሄ እይወት እኔ ነኝ 6 እኔ መንገድና እውነት እይወት ነኝ 7 እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ ሐ/ቅ/ ዩሐንስ መልእክት የፃፈላቸው ስባቱ አብያተ ክርስቲያናት ============================= 1 የኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን 2 የሰርምኔስ ቤተ ክርስቲያን 3 የትያጥሮን ቤተ ክርስቲያን 4 የስርዴን ቤተ ክርስቲያን 5 የሎድቅያ ቤተ ክርስቲያን 6 የጴርጋሞን ቤተ ክርስቲያን 7 የፊልዶልፊያ ቤተ ክርስቲያን ስባት ተፀሎት ግዜያት =========== 1 ነግህ /ጧት ፲፪ ስዓት 2 ሰልስቱ ፲፫ 3 ስድስት ስዓት 4 ተስዓቱ ፱ ስዓት 5 ሰርክ ምሽት ፲፪ ስዓት 6 ንዋይ ምሽት ፫ ስዓት 7 መንፈቅ ሌሊት ጌታችን በተስቀለ ግዜ የታዩ ተዓምራት ================== 1 የፀሐይ መጨለም 2 የጨረቃ ደም መምስል 3 የከዋክብት መርገፍ 4 የዓለቶች መስነጣጠቅ 5 የመቃብራት መከፈት 6 የሙታን መነሳት 7 የቤተ ክርስቲያን መጋረጃ ከሁለት መቀደድ ለመጀመርያ ግዜ በቅ/ሐዋርያት የተመረጡት ስባት ዲያቆናት =========================== 1 ቅዱስ እስጢፋኖስ 2 ቅዱስ ጵሮኮሮስ 3 ቅዱስ ኒቃሮስ 4 ቅዱስ ጢሞና 5 ቅዱስ ጳርሜና 6 ኒቆላዎስ 7 ቅዱስ ፊልጶስ ስባቱ አጽዋማት ======= 1 አብይ ፆም 2 የሐዋርያት ፆም 3 የፍልስታ ፆም 4 የነብያት ጾም 5 የነነዌ ፆም 6 ጾመ ገሃድ 7 ጾመ ድኅነት ስባት ሚስጢራተ ቤተ ክርስቲያን ================= 1 ሚስጢረ ጥምቀት 2 ሚስጢረ ሜሮን 3 ሚስጢረ ቁርባን 4 ሚስጢረ ክህነት 5 ሚስጢረ ተኪሊል 6 ሚስጢረ ንስሀ 7 ሚስጢረ ቀንዲል ወስበሀት ለእግዚአብዜር።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages