መካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ውሉደ ኤስድሮስ ሰንበት ት/ቤት ጎንደር - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Tuesday, June 2, 2020

መካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ውሉደ ኤስድሮስ ሰንበት ት/ቤት ጎንደር





🌱ሰንበት ት/ቤት ዘጎንደር🌱
እናስተዋውቃችሁ- ፫
🍂የሰ/ት/ቤቱ ሥም :- መካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ውሉደ ኤስድሮስ ሰንበት ት/ቤት
🍂ቤተ ክርስቲያኑ የታነጸበት ጊዜ :- በ1703ዓ/ም በአፄ ዮስጦስ ሲሆን ከጎንደር አርባ አራቱ ታቦታት አንዱ ነው፡፡
🍂ዓመታዊ ክብረ በዓል፦ ግንቦት 1 ልደታ ለማርያም፣ ኅዳር 12 ቅዱስ ሚካኤል እንዲሆም ጥር 10 የጥምቀት ዋዜማ ታቦቱ ሕጉ ወደ መጠመቂያ ቦታ ይወርዳል፡፡
🍂ሰ/ት/ቤቱ የምሥረታ ጊዜ :- ሐምሌ 21/1984 ዓ/ም
🍂መገኛ ሀገረ ስብከት:-በማ/ጎንደር ሀገረ ስብከት በጎንደር ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተ ክህነት
🍂የቤተ ክርስቲያኑ አድራሻ፤ ጎንደር ዞብል ክፍለ ከተማ ልደታ ቀበሌ 16
🍂የሰ/ት/ቤቱ የጉባዔ አከፋፈል፤ የህጻናት፣ማዕከላውያን እና የአዋቂዎች
፩/የህፃናት ጉባኤ መርሐ ግብሮች-
➡️ሀ/የፀሎት መርሃ ግብር ረቡዕ ከ11:00-11:30
➡️ለ/መደበኛ ጉባዔ መርሐ ግብር ቅዳሜ እና እሁድ 8:30-9:30
፪/ የማዕከላዊ መርሐ ግብር
➡️ሀ/የፀሎት መርሃ ግብር ረቡዕ ከ11:00-11:30 ከሕፃናት ጋር
➡️ለ/መደበኛ ጉባዔ መርሐ ግብር ቅዳሜ እና እሁድ 9:30-10:30
3/ የአዋቂዎችጉባኤ መርሐ ግብሮች-
➡️ሀ/የመሐረነ አብ ፀሎት ዘወትር አርብ ከ11 :00 - 12:00
➡️ለ/ማክሰኞ እና አሙስ ከ11:30-12:30 መዝሙር ጥናት
➡️ሐ/መደበኛ ጉባዔ መርሐ ግብር ቅዳሜ እና እሁድ 10:30-12:30
🍂በደብሩ የሚገኙ የአብነት ት/ቤቶች
➡️፩/ቅዳሴ ትምህርት ቤት፣
➡️፪/የአራቱሞ ጉባዔያት ትምህርት ቤት
➡️፫/አቋቋም ትምህርት ቤት
🍂ደብሩ አዋሳኞች
➡️በስተምስራቅ ጎንደር ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል
➡️በምዕራብ ጎንደር ዩኒቨርስቲ ቴዎድሮስ ግቢ/ጎንደር ማዕከል ማኅበረ ቅዱሳን
➡️በሰሜን ቀራንዮ መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን
➡️በደቡብ ቀበሌ 18 አበራ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን
🍂ከሰ/ት/ቤቱ አርያአነት ያለው ተሞክሮ ፤
፩/ በመንፈሳዊ ህይወታቸው አርአያነት ያለቸው እስከ ምንኩስና የደረሱና በሥጋዊ እውቀታቸው ከፍተኛ ደረጃ የደረሱ በተለያዩ የመንግሥት መስሪያ ቤቶችና የትምህርት ተቋማት የሚሰሩ አባላትን ማፍራቱ፡፡
፪/ከደብር ሰበካ ጉባዔ ጋር ጠንካራ ግንኙነት መኖር
፫/ህንጻ ቤተ ክርስቲያኑን የተዋጣለት አደረጃጀት በመሥራት በአጭር ጊዜ አሁን እስከ ደረሰበት ድረስ በጋራ ሥራዎችን መሥራታቸው ፡፡
፬/መጽሐፍትን በህትመት መንገድ አዘጋጅተው የሚያቀርቡና በጎንደር በተለያዩ ቦታዎች እየተጋበዙ ትምህርት አገልግሎት የሚሰጡ በርካታ መምህራን ማፍራቱ
፭/ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እየተጋበዙ በተለያዩ ርዕሱ ጉዳዮች ትምህርት የሚሰጡበት፣ምዕመናን የሚሰማቸውን ጥያቄ የሚጠየቁበትና ምላሽ/ማብራሪያ የሚያገኙበት ‹‹ ቤተ ልሔም›› የሚል መርሐ ግብር በቋሚነት የሚከናወንበት መሆኑ፡፡
፮/ ሰንበት ት/ቤቱ የራሱን ንዋየ ቅድሳን መሻጫ ሱቅ ያለው መሆኑ
ስለ ሰንበት ት/ቤቱ አድራሻ
የቀድሞዋ ልደታ ቤተ ክርስቲያን ገጽታ
Image may contain: one or more people, basketball court, sky and outdoor

መዘምራን በአገልግሎት ላይ
Image may contain: 9 people, people standing


Image may contain: 10 people, people standing

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages