ግንቦት_26 ልደቱ ለአቡነ ሀብተማርያም ጻድቅ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Thursday, June 3, 2021

ግንቦት_26 ልደቱ ለአቡነ ሀብተማርያም ጻድቅ

#ግንቦት_26 ልደቱ ለአቡነ ሀብተማርያም ጻድቅ
✞እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም በጤና አደረሰን አደሰችሁ ✞ ✞ ጽሩይ እምወርቅ ወእምብሩር ንጡፍ ወኅሩይ እምአእላፍ ሀብተ ማርያም መልአክ ዘውገ ኪሩብ ቀሊለ ክንፍ አማን ስሙዐ ዜና እስከ አጽናፍ፡፡ †ሰላም ለፅንሰትከ እማህፀነ ቅድስት ዮስቴና በብሥራተ ጻድቅ ባሕታዊ ሠናየ ዜና ሐብተ ማርያም ጴጥሮስ ሐዋርያ ወልደ ዮና መሐረኒ ምግባረ ጽድቅ ወጸግወኒ ልቦና አፍቅሮ ቢጽ እኃሥሥ ዘምስለ ፍጽምት ትሕትና:: (መልክአ አቡነ ሀብተ ማርያም) 💭 ✞ ታሪክ አቡነ ሀብተማርያም የተወለዱት በመንዝ አውራጃ ልዩ ስሙ የራዊ በተባለ ቦታ ሲሆን የአባታቸው ስም ፍሬ ብሩክ የእናታቸው ስም ዮስቴና ይባላል፡፡ ሁለቱም በሕግ ጋብቻ ጸንተው ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቀው ምግባር ቱሩፋት ሰርተው በንጽህና በቅድስና ይኖሩ ነበር፡፡ ሆኖም ልጅ አለነበራቸውም፡፡ በዚህ ሁኔታ ያዘኑ ቅድስት ዮስቴና ማለት እናታቸው መንነው በአከባቢያቸው ከሚገኝ ጫካ ውስጥ ዋሻ ፈልገው ገብተው ዘጉ፡፡ በዚያም አንድ መናኝ መነኩሴ አግኝተዋቸው እግዚአብሔር በቅድስቲቱ ያለው ድብቅ ነገር ስለገለጠላቸው አንቺ ለምንኩስና የተፈቀደልሽ አይደለሽም ወደ ቤትሽ ግቢ ጸሎቱ ለዓለም ሁሉ የሚጠቅም ሰው ሁሉ የሚማጸነው ስሙ፣ ገድሉ ትሩፋቱ በዓለም ሁሉ የሚነገርለት ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ አሏቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ድንቅ ተዓምር የሰሙ ቅድስት ዮስቴናም እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ወደ ቤቸው ተመለሱ፡፡ የተናገረውን የማያስቀር አምላክ በቸርነቱ ጎበኛቸውና ነሐሴ 26 ቀን ጸነሱ፡፡ ግንቦት 26 ቀንም ደም ግባታቸው እንደ ንጋት ኮከብ ያማሩ ሃብተማርያም ተወለዱ፡፡ እግዚአብሔር ለቅድስና ሥራ ስለመረጣቸው በእናተቸው ጀርባ ታዝለው ወደ ቤተክርስቲያን ሄደው በሕጻን አንደበታቸው ከቀዳሹ ካህን ጋር “እግዚኦ ማሐረነ ክርስቶስ” በማለት ይጸልዩ ነበር፡፡ ባደጉም ጊዜ ይህን ጸሎት ደጋግመው ይጸልዩ ነበር፡፡ ላባቸውም እስኪንጠባጠብ ድረስ በመስገድ ይጋደሉ ነበር፡፡ አንድ ቀንም ከአባታቸው ጎን እንደ ተኙ በድንገት እግዚአብሔር በድምጽ “ሀብተማርያም ሆይ! አንተን የተመረጠ ዕቃ አድርጌሃለሁና ቃሌን ለተመረጡ ሰዎች ተናገር” አላቸው፡፡ ይህን ግን የተበሰረላቸው የቤተሰቦቻቸውን ከብቶች በሚጠብቁበት ጊዜ ነበር፡፡ እድሜያቸው እየገፋ ሲሄድ አባታቸው ትምህርት ቤት አስገቡአቸው፡፡ ለአቅመ አዳም በደረሱ ጊዜ ሚስት አጩላቸው፤ እርሳቸው ግን የድንግልናን ህይወት በመምረጥ ከወላጃቸው ቤት ኮብልለው ገዳም ገቡ፡፡ “ልጄ ሆይ እራስህን ለእግዚአብሔር ታስገዛ ዘንድ ወደ ገዳም ብትሄድ ሰውነትህ ለመከራ አዘጋጅ፡፡” መጽሐፈ ሲራክ 2፡1. በዚያን አባ ሳሙኤል ለሚባሉ በረዳትነት ሲያገለግሉብዙ ገቢረ ተዓምራት ተደርጎላቸዋል፡፡ ዛሬ ይሰበይ ገዳም ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ ለሦስት ወራት ጽሙድ እንደበሬ ትጉህ እንደ ገበሬ እንዲሉ በጾም በጸሎት ተጠምደው ሳለ መታሰቢያህን በዚህ ዋሻ አደርግልሃለሁ በማለት እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ጊዜ እረፍታቸው በደረሰ ጊዜ ጌታ ተገልጦላቸው ስለ ተጋድሎአቸውና ስለንጽህናቸው ሳባት አክሊል እንደሚቀበሉ ነግሯቸዋል፡፡ በ490 ዓ.ም ህዳር 26 ቀን ዐርፈው በደብረሊባኖስ ገዳም መካነ ቅዱሳን ቀበሯቸው፡፡ የአባታችን የጻድቁ አቡነ ሀብተማርያም ረድኤት፣ በረከት፣ ምልጃና ቃል ኪዳናቸው አይለየን፡፡ 🤍✞#አቡነ #ተክለሃይማኖት እና #አቡነ #ሀብተማርያም #ያን ጊዜ ክቡር የሆነ #አቡነ_ተክለሃይማኖት ጠርቶኝ ልጄ #ሀብተ_ማርያም ሆይ ፈጣሪየ እግዚአብሔር ስለ ወደደህ ብዙ ምህርኮ እንደአገኝህ በአንተ ፈጽሞ ደስ ይለኛል አለኝ ፤ #ነገር ግን የሞለምንክ አንድ ነገር አለና እሽ በለኝ ቢለኝ አቤቱ ጌታዩ ምንድን ነው ነገሩ አልሁት ፣ #ክቡር አባታችን አባ ተክለሃይማኖትም ከተቀበርኩበት ቦታ እንድትቀብር ቃል ኪዳን ግባልኝ አለኝ፤ ይንን አደርግ ዘንድ ስለምን ትለምነኛለህ ብየ ብመልስለት፣ እነሆ በሀገሬ ላይ የታዘዙ አምስት መቅሰፍቶች አሉና ስለዚህ ነው ፤ እሊሁም አንዱ መብረቅ ነው ፣ ሁለተኛው ቸነፈር ነው ፤ ሦስተኛው የረኃብ ጦር ነው ፣ አራተኛ ወረርሽኝ ነው ፡፡ አምስተኛ የእሳት ቃጠሎ ነው ፤ የአንተ አጽም በውስጡ የተቀበረ እንደ ሆነ አጥንቴ የተቀበረባት ሀገር ከእንዚህ መቅስፍታት ትድናለች፣#……ልጄ ሀብተማርያም ሆይ አንተ የማታውቀው ከፈጣሪያችን ከእግዚአብሄር የተሰጠህ እኔ የማውቀው ክብር አለህና ስለዚህ ነው አለኝ ፣ ይልቁንስ እንዳልኩክ በተቀበርኩበት ቦታ እንተቀበርልኝ ቃል ኪዳን ግባልኝ ብሎ መላልሶ ማለደኝ:: ይህንንም ሲባባሉ እንዲህ የሚል ቃል መጣላቸው፡- ‹‹ከወዳጄ ከሀብተ ማርያም አንደበት ይህ ቃልኪዳን አይወጣም፣ ዳግመኛም ወዳጄ ተክለ ሃይማኖት ሆይ! እርሱ በወደደው የሚቀበር አይደለምና እኔ ከተቀበርኩበት እንድትቀበር ብለህ የምታስገድደው ለምንድን ነው? እኔ በወደድሁት ቦታ ይቀበራል እንጂ›› የሚል ቃል ተነገረ፡፡ አቡነ ተክለሃይማኖትም እየለመኑናና እየሰገዱ ከሥላሴ ዙፋን ፊት ተንበረከኩ፡፡ በሦስተኛውም ‹‹ይሁን እንዳልከው ይቀበርልህ›› የሚል ቃል ተሰማ፡፡ ዳግመኛም ‹‹በአንተም አጽም በሀብተ ማርያምም አጽም ቦታህ ከመቅሰፍታት ትዳንልህ፤ ልጆችህ ግን በቸነፈር ደዌ ቢሞቱ ከሰማዕትነት ተቆጥሮላቸው ወደ መንግሥተ ሰማያት እንዲገቡ በራሴ ምዬ ቃልኪዳን ገብቼልሃለሁ›› አላቸው፡፡ በዚህም ጊዜ አቡነ ተክለሃይማኖት እጅግ ደስ ተሰኝተው ሦስት ጊዜ ሰገዱ፡፡ 🕊✞ #ከገድላቸው አቡነ ሀብተ ማርያምም ምንኩስናን ከተቀበሉ በኋላ ገድላቸውንና ትሩፋታቸውን በማብዛት በሳምንተ አንድ ጊዜ ቅጠልን ብቻ የሚመገቡ ሆኑ፡፡ አርባ አርባ ቀን ሰማንያ ሰማንያ ቀንም የሚጾሙበት ጊዜ ነበር፡፡ በሌሊትም ወደ ጥልቅ ባሕር እየገቡ መዝሙረ ዳዊት፣ አራቱን ወንጌላትና ሌሎች የጸሎት መጽሐፍትን ይደግሙ ነበር፡፡ ፊታቸውም እንደ ንጋት ምሥራቅ ኮከብ ያበራ ጀመር::… 🕊✞ # ተአምር ከዕለታት በአንድ ቀን በሌሊት መብራት ለአባ ሳሙኤል እያበሩ ሳለ መብራቱ ከእጃቸው ላይ ወድቆ ጠፋ፡፡ መምህሩም አባ ሳሙኤል ቁጡ ነበረና ስለ መምህራቸው ቁጣ በጣም ደንግጠው ወድቆ የጠፋውነ መብራት ፈጥነው ባነሱት ጊዜ መብራቱ በእግዚአብሔር ተዓምር ራሱ በርቶ ታየ፡፡ አባ ሳሙኤልም ይህን ተዓምራት አይቶ እጹብ እጹብ በማለት ‹‹የዚህ ቅዱስ ልጅ መጨረሻ ምን ይሆን?›› ብሎ ካደነቀ በኋላ ‹‹የዓለም ሁሉ የጥበብ መብራት ይሆናል›› ሲል ትንቢት ተናገረላቸው፡፡ እመቤታችን ለአባ ሳሙኤል ተገልጣላቸው የአቡነ ሀብተ ማርያምን ክብር ነግራዋለች፡፡ አባታችንም አባ ሳሙኤልን 12 ዓመት ከትሕትና ጋር እየታዘዙ ቤተ ክርስቲያንን እያገለገሉ ኖረው ከዚህ በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ ወጥተው ሄደው እለ አድባር በተባለ ገዳም መኖር ጀመሩ፡፡ ከቦታውም ደርሰው ጥቂት ከቆዩ በኋላ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ከአባ መልኬጼዴቅ እጅ የምንኩስናን ስርዓት ተቀበሉ፡፡ ይኸውም የሚዳው አቡነ መልኬጼዴቅ በደጃቸው የተቀበረውን ሰው አፈር የማያስበሉት ጻዲቅ ናቸው፡፡ ይህንንም የጻድቃኑን አባትና ልጅነታቸውን መሠረት በማድረግ የይሰበይ አቡነ ሀብተ ማርያም ገዳም ካህናት፣ መሪጌቶችና ዲያቆናት ግንቦት 4 ቀን ወደ ሚዳ መራቤቴ በመሄድ የአቡነ መልኬጼዴቅን በዓል እጅግ በደማቅ ሁኔታ ያከብራሉ፡፡ 🕊✞ # ቃልኪዳን አቡነ ሀብተ ማርያምም ምንኩስናን ከተቀበሉ በኋላ ገድላቸውንና ትሩፋታቸውን በማብዛት በሳምንተ አንድ ጊዜ ቅጠልን ብቻ የሚመገቡ ሆኑ፡፡ አርባ አርባ ቀን ሰማንያ ሰማንያ ቀንም የሚጾሙበት ጊዜ ነበር፡፡ በሌሊትም ወደ ጥልቅ ባሕር እየገቡ መዝሙረ ዳዊት፣ አራቱን ወንጌላትና ሌሎች የጸሎት መጽሐፍትን ይደግሙ ነበር፡፡ ፊታቸውም እንደ ንጋት ምሥራቅ ኮከብ ያበራ ጀመር፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ ምሥራቅ ሄደው ጎሐርብ ወደምትባል ሀገር ደረሱ፡፡ በዚያም በዓት አጽንተው ሲጸልዩ ጌታችን ቅዱስ ገብርኤልንና ቅዱስ ሚካኤልን በቀኝና በግራ አስከትሎ ተገለጠላቸውና ‹‹ወዳጄ ሀብተ ማርያም ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን›› አላቸው፡፡ ያን ጊዜ አባታችን ከፈጣሪአቸው ግርማ የተነሳ ደንግጠው ከመሬት ወድቀው እንደ በድን ሆኑ፡፡ ጌታችንም አንስቶ ክቡራን በሆኑ እጆቹ አጸናቸውና ‹‹የመጣሁት ለጸናህ ነው ሰውነትህንም እንደ ንስር ላድሳት ነው እንጂ ላጠፋህ አይደለም፡፡ ድካምህና ገድልህ ሁሉ ለዘለዓለም መታሰቢያ ሊሆን በኢየሩሳሌም ሰማያዊት ተጽፎልሃል ብዬ በእውነት እነግርሃለሁ፡፡ ለአንተ ለወደድኩህና ለመረጥኩህና ወዳጄ የማቴዎስንና የማርቆስን ወንጌል ባነበብክ ጊዜ ተጭነህ ወደምትሄድበት ቦታ የሚያደርስህ የብርሃን ሰረገላ ሰጥቼሃለሁ፡፡ እንደ አንተም ካሉ በዋሻ በመሬት ፍርኩታ ከሚኖሩ ከመረጥኳቸው ቅዱሳን ጋር ትገናኝ ዘንድ ወደ አራቱም አቅጣጫ ትበር ዘንድ የብርሃን ሠረገላ ሰጥቼሃልሁ፡፡ ዳግመኛም የሉቃስንና የዮሐንስን ወንጌል ባነበብክ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ትሄድ ዘንድ የእሳት ሠረገላ ሰጥቼሃለሁ›› አላቸው፡፡ ዳግመኛም ‹‹በጸሎትህ አምኖ በጎ ሥራ ለሚሠራ ሁሉ፣ ስምህን የጠራውን ዝክርህን ያዘከረውን ሁሉ የሀብተ ማርያም አምላክ ሆይ ከጠላት እጅ አድነኝ ያለኝን በኅሊና ያሰበውን በልቡናው የወሰነውን እፈጽምለታለሁ፡፡ አንተን ገድልህንና ቃል ኪዳንህን የናቀውን ያቃለለውን ሁሉ ፍጹም መበቀልን እበቀለዋለሁ፡፡ እንደ ወዳጄ እንደ ፊቅጦርም በእናቴ በማርያም ድንግል አተምኩህ›› ካላቸው በኋላ ቅዱስ ሚካኤል ከእርሳቸው እንዳይለይ የዘወትር ጠባቂ አድርጎ ሰጣቸውና በታላቅ ግርማ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ ቅዱስ አባታችን ፅንሰታቸው ነሐሴ 26፣ ልደታቸው ግንቦት 26፣ ዕረፍታቸው ኅዳር 26 ነው፡፡ ኦ አምላከ አቡነ ሀብተ ማርያም ዕቀቦ ወአድኅኖ ወባልሆ እመከራ ሥጋ ወነፍስ ወእምኩሉ ተቃራኒ ወእምኩልነ ክቡር ሀብተ ማርያም ለዓለም ዓለም አሜን ለይኩን ለይኩን:: ወስብሐት ለእግዚአብሔር !

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages