ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ክፍል ፬ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Thursday, June 3, 2021

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ክፍል ፬

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ክፍል ፬ (ከመምህር ዘለዓለም ገጽ የተወሰደ)
በዛሬው ርዕሳችን የምንዳስስ ሁለት ነገሮችን ነው 1.ቤተ ክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሠራ የክርስቶስ ደም ከፈሰሰበት ቦታ ላይ መሆኑን 2.ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ሲሠራ ያለጳጳሱ ፈቃድ የማይፈጸም መሆኑን ፡፡ የሕንፃ ቤተ ክርስቲያን አመሠራረት በማንኛውም ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ሲሠራ ቦታውን የሚመርጠው ራሱ እግዚአብሔር ነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ በተሰቀለ ጊዜ እጁንና እግሩን በቀኖት ሲቸነክሩት የፈሰሰውን ደም መላእክት በጽውዓ ብርሃን እየተቀበሉ ዓለሙን በሙሉ ረጭተውታል እስካሁን ድረስ የተሠሩት እንግዲህም ወዲህ የሚሠሩት አብያተ ክርስቲያ ናትም እግዚአብሔር ባወቀ መሠረታቸው የተቀመጠ የክርስቶስ ደም ከነጠበበት ቦታ ላይ መሆኑን የቤተ ክርስቲያናችን የሥርዓት መጻሕፍት ያስረዳሉ ቤተ ክርስቲያን ሲሠራ በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መሠረት መጀመሪያ የሚቀድመው ፈቃድ ነው ፈቃዱንም መፍቀድ ያለበት የክፍለ ሀገሩ ጳጳስ ነው ጳጳሱ ይፍቀድ የተባለበትም ምክንያት የሕንፃው አሠራር ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እንዳይወጣና መሠረቱ ሲቀመጥም ሆነ ሕንፃው ሲያልቅ በቅብዓ ሜሮን በቡራኬ የሚያከብራት እሱ ስለሆነ ነው የክፍለ ሀገሩ ሊቀ ጳጳስ ሳይፈቅድ በማንኛውም ምክንያት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን መሥራት ግን አይቻልም ሌላው ቀርቶ ስለአሠራሩም(ስለፕላኑ) መጻሕፍት ከሚያዙት ውጪ መሥራት የተከለከለ ነው ማንኛውም ሰው በማንኛውም ጊዜ ይህን አድርጎ ቢገኝ ግን ቀኖናዊ ቅጣት አለው ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን ሲሠራ ከላይ ከጉልላቱ ጀምሮ እስከ መሠረቱ ድረስ እያንዳንዷ ሥራ በምስጢርና በምሳሌ የተከናወነች ስለሆነች ይህ ሥርዓትና ትውፊት እንዳይፋለስ ለማድረግ ነው ፡፡ ስለዚህ የቤተ ክርስቲያንን ፕላን የሚሠሩ ባለሞያዎችም ቢሆን እንዴት መሠራት እንዳለበት የሚመለከታቸውን የቤተ ክርስቲያኒቱ ሰዎች ማማከር ይኖርባቸዋል ያለዚያ ግን ሕንፃን ለማሳመር ተብሎ የሚሠራው ሥራ ሠሪውንም አሠሪውንም ከተጠያቂነት ነጻ ሊያደርግ አይችልም ቀኖናዊ ቅጣቱም ካህን ከሆነ ከክህነቱ ይሻራል ምእመን ከሆነ ከቤተ ክርስቲያንና ከምእመናን ተወግዞ ይለያል ነው የሚለው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንም ያለጳጳሱ ፈቃድ መጻሕፍት ከሚያዙት አሠራር ውጪ ከተሠራ ስሙም ቤተ ክርስቲያን አይባልም ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንም አይፈጸምባትም ሥርዓተ ቁርባን አይከናወንባትም እንዲሁ ፈት ሁና እንድትኖር በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ተወስኖባታል ፡፡ ፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ ፩ ባስልዮስ በጻፈው መጽሐፍ አንቀጽ ፺፬ ወስብሐት ለእግዚአብሔር !!

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages