በሰው ቂም አትያዝ በሰው ላይ ያለውን ቂም በልቦናው የሚያሳድር ሰው ጸሎቱ
ቅድመ እግዚአብሔር አትደርስምና ከአርዮሳውያን ጋር አትጸልይ እሊህም መናፍቃን ናቸው፡፡ ከአህዛብም ጋር ቢሆን፡፡(መዝ 4÷4-36(37) ፣ ማቴ 5 ÷ 5-14 ፣ ሮሜ 4 ÷ 4-19-2)
አንተ ሰውነትህን ለማድከም በምትጾምባቸው ዕለታት ወንድምህ ሊጠይቅህ ቢመጣ
እግዚአብሔርን ደስ በምታሰኝ በበጎ ሕሊና በፍቅር ሆነህ ከእርሱ ጋር ተመገብ ይህንንም የምነግርህ የጌታ ጾም በሆነበት ዕለታት ትበላ ዘንድ አይደለም፡፡ እሊህም ረቡዕ እና
አርብ አርባውም (ዓብይ ጾም) ቀን ናቸው፡፡ አንተ ብቻ በራስህ ፈቃድ
በምትጾምበት ቀን ነው እንጂ ይኸውም ሰኞ ማክሰኞ ሐሙስ ነው፡፡
(ዳን 10 ÷ 2-3፣ማቴ 6÷16-18)
በቅዳሜ ቀን ግን መጾም አይገባም ፡፡በቅዳሜ ቀን ፀሐይ እስኪጠልቅ መጾም የሚገባ ስራ አይደለም፡፡ እሁድ ግን በጠዋት እጅግ ማልደህ ወደ ቤተክርስቲያን ሂድ ስትሄድም ልቦናህን በማባከን ወዲያ
እና ወዲህ አትይ በንጹሕ ቅዳሴም ጊዜ ሕማማቱን ፣ ሞቱን እና ትንሳኤውን እያሰብክ በፍጹም ፍርሃት ቁም፡፡(መዝ 62(63) ÷1-4፣ ሉቃ 24 ÷ 1-40፣ ራዕ 1÷9 -10)
በከበረች እሁድ ቀን መቼም መች ትጾም ዘንድ ማንም አያስትህ አትስገድባት በዋዜማው( በቅዳሜም) ቢሆን ዳግመኛም በከበረች በፋሲካ ቀኖች (በበዓለ አምሳ)
አትስገድ ቅዳሴ በሚቀደስበትም ጊዜ ሁሉ ስጋው ደሙን ከተቀበልክ በኋላ አትስገድ ይህ ከስርዓተ ቤተክርስቲያን የተገኘ አይደለምና፡፡
በሰንበት ቀኖችም አትጹም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስኩብ በመቃብር ሆኖ ከነበረባት፣ ድኅነት በተደረገባት ከፋሲካ ዋዜማ ካለች ከአንዲት ቅዳሜ ቀን (ቀዳም ሥዑር) በቀር፡፡
የረቡዕ እና ዓርብ ጾም እስከ ቀኑ 9 ይሁን ከዚህ አብልጠህ ብትጾም ግን
ለነፍስህ ጥቅም ይሆንሃል፡፡ የማሰናበቻ ጸሎት (እትው በሰላም) እስኪፈፀም
ድረስ ከቤተ ክርስቲያን አትውጣ ሕማም ቢያገኝህ ነው እንጂ ድንተኛ
መንገድ ቢሆን ነው እንጂ፡፡(መዝ 69(68)÷ 10-11፣109(108)÷24፣ ዳን 1 ÷ 10-15)
ጌታ ያዘዘውን ጾም አትሻር እነዚህም ረቡዕ፣ዓርብ ናቸው፡፡ ደዌ ካላገኘህ
በቀር በበዓለ አምሳ ፣ልደት፣ጥምቀት ፣ በዋሉባቸው ዕለታት (ረቡዕ
ዓርብ) በቀር ይኽውም ኤጵፋንያ ጥምቀት ነው፡፡
ምንጭ ( ሃይማኖተ አበው
ዘሠለስቱ ምዕት ምዕ 20÷17-29)

No comments:
Post a Comment