መንፈሳዊ አገልግሎት - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Saturday, September 17, 2022

መንፈሳዊ አገልግሎት

ee

Ø  ቅዱስ ጳውሎስ “ ለትምህርትህ” ከማለቱ በፊት “ለራስህ” ማለቱን አስተውሉ ። እርሱ ይህንንያለው ይህ ጉዳይ ለድኅነቱና የሚናገረውን ቃል ለሚሰሙት ሰወች ድኅነት አስፈላጊ ስለሆነ ነው።

Ø   እነዚህ ሰወች የ አገልግሎት ገጽታ አላቸው እንጂ ውስጣቸው ጠፍቷል ።  ከእነዚህ ሰወች አንዳንዶቹ ስለራሳቸው የሚያስቡ ነበሩ ። ይሁን እንጂ አገልግሎትን ሲጀምሩ ቸልተኝነት በልቦናቸው ውስጥ ዘልቆ ይገባል ።
Ø  ሰወች ራቸውን በመርሳት በአገልግሎት ውስጥ ቢታገሉ መንግስተ ሰማያትን ከማጣት በስተቀር የሚጠቀሙት ጥቅም ምንድን ነው ?
Ø  እንዲህ አይነቱ ሰው ግን ሊያውቀው የሚገባ ትልቁ ጠቃሚ እውነት ቢኖር ፦ ወደ እግዚአብሔር የ ሚመራው አገልግሎት ሳይሆን ንጹህ ልብ መሆኑን ነው ።

 “ለራህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ በእነዚህም ጽና ይህንን ብታደርግ ራስህንም የሚሰሙትንም ታድናለህ. . .” 1ኛ ጢሞ 4፡16
    ታላቁ ሰባኪ ቅዱስ ጳውሎስ አገልግሎትን በጥልቀት ተግባራዊ አድርጓል ፣ መንፈሳዊ ሕይወትን በሚገባ ተለማምዷል ፤ከሌሎች ሐዋርያት ይበልጥም እጅግ ደክሟል (1ኛ ቆሮ 15፤10)
   ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን ቃል የጻፈው በኤፌሶን ጳጳስ ለነበረው ለደቀ መዝሙሩ ጢሞቲወስ ነው። ጢሞቲወስ  ትክክለኛውን ዕምነት መጀመርያ የተማረው ከአያቱ ፣ ከዚያም ከእናቱ ኋላም ከቤተሰቦቹ ስለነበር ከሕጻንነቱ አንስቶ ቅዱሳት መጻህፍትን ያውቅ ነበር ።
  መምህሩ ቅዱስ ጳውሎስ “ ለራህ ተጠንቀቅ . . . ” በማለት የተናገረው ቃል ልብ በሉ ። እርሱ ይህን የተናገረው አገልግሎት መስጠት ቀላል ባልሆነበት በኤፌሶን ከተማ ውስጥ የ ጵጵስናን ታላላቅ ሸክሞች ኀላፊነቶች መወጣት ከባድ ስለነበረ ነው ። እራሱ ቅዱስ ጳውሎስም “ እንደ ሰው በኤፌሶን ከአውሬ ጋር ከታገልኩ . . . ” (1ኛ ቆሮ 15፥32) በማለት ተናግፘል።
   ቅዱስ ጳውሎስ “ ለትምህርትህ” ከማለቱ በፊት “ለራስህ” ማለቱን አስተውሉ ። እርሱ ይህንን ያለው ይህ ጉዳይ ለድኅነቱና የሚናገረውን ቃል ለሚሰሙት ሰወች ድኅነት አስፈላጊ ስለሆነ ነው።
   አንድ ሐዋርያ ከአገልጋዮችም ሆነ ከምዕመናን ጋር መተዋወቁ መሰረታዊ መመርያ ነው ። አገልጋዮች ማንነታቸው ይበልጥ የሚታወቀው በዚህ ነውና ። ግን ለምን ?
ለራስህም ተጠንቀቅ..ለምን ?
     የ ዚህ ምክንያት ከፍተኛ የዝና እንቅስቃሴ እንዲሁም ለሌሎች ሰወች የማሰብ ደረጃ ላይ የደረሱና ስሞቻቸው ታዋቂ የሆኑላቸው ሰወች ራሳቸውን በመዘንጋታቸው ስለጠፉ ነው ።
    እነዚህ ሰወች የ አገልግሎት ገጽታ አላቸው እንጂ ውስጣቸው ጠፍቷል ።
  ከእነዚህ ሰወች አንዳንዶቹ ስለራሳቸው የሚያስቡ ነበሩ ። ይሁን እንጂ አገልግሎትን ሲጀምሩ ቸልተኝነት በልቦናቸው ውስጥ ዘልቆ ይገባል ። እነዚህ ሰወች ስለሌላ ሰወች በማሰባቸው እንጂ ስለራሳቸው ባለማሰባቸው ተልዕኮአቸውን እንዳጠናቀቁ አድርገው እንዲያስቡ ያደርጋቸዋል ። አንዳንዶቹ ደግሞ ከሚያስተምፘቸው ህጻናት ወይም ደቀ መዛሙርት እጅግ ዝቅ ባለ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ሐዋርያው ለእነዚህ ለእያንዳንዳቸው “ ለራስህ ለትምሕርት ተጠንቀቅ ይላቸዋል. . .”   ለምን ?
    “ ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጎድል ምን ይተርፈዋል . . . ?” (ማቴ 16፡26)
    ሰወች ራቸውን በመርሳት በአገልግሎት ውስጥ ቢታገሉ መንግስተ ሰማያትን ከማጣት በስተቀር የሚጠቀሙት ጥቅም ምንድን ነው ? እያንዳንዳቸው ራሄልን እንደወሰዱ ቢያስቡም የወሰዱት ግን ልያን ነው ። ብዙ አገልጋዮች በአገልግት ውስጥ ሳሉ ከዚህ ቀደም ያልተቸገሩባቸው የተለያዩ ችግሮች ፣ ጠቦች ውግዘቶች ወደ ሕይወታቸው መግባቱን ይደርሱበታል ።
   እውነቱን ለመናገር ግን አገልግሎት የእነዚህ ችግሮችና ጠቦች መገኛ ምክንያት አይደለም ። ይሁን እንጂ ለራሱ የማይጠነቀቅ ሰው በእነዚህ ጉዳዮች ጉዳት ሊደርስበት ይችላል ። እርሱ በአገልግሎት ውስጥ ብዙ ስህተት ላይ ሊወድቅ ይችላል ፤ እርሱ ፈጽሞ ያልተገነዘባቸው አዳዲስ ኃጢአቶች ይከሰታሉ ፤ ወይም ተሸሽገው ከቆዩ በኋላ አሁን ይገለጣሉ ።
   እርሱ አውቆትም ይሁን ሳያውቀው አገልግሎት ከፍ አድርጎ ያሳደገው ቢመስለውም እርግጡ እውነት ግን ቁልቁል መውረዱ ወይም መውደቁ ነው ።
    እርሱ በአገልግሎት እያደገ ሲሄድ ተካፋይ ሚሆንባቸው ነገሮች እያደጉ ስለሚሄዱ ስህተቶቹም እያደጉ ይሄዳሉ ። ኃላፊነቶቹ እየጨመሩ ሲሄዱም ሙሉ ጊዜው ይዋጣል ፤ ራሱን እስከመርሳትም ይደርሳል ። እርሱ ለነፍሱ የሚያስፈልጋትን ምግብ ስለማያቀርብላት ቁልቁል ይወድቃል ። አገልግሎቱን በማቆም ለራሱ እንዲጠነቀቅ ምክር ብትሰጡትም እጅግ ያዝናል ።አልግሎት ለእርሱ ሁሉ ነገሩ ስለሆነ ያለ እርሱ ሊኖር አያችልም ። እንዲህ አይነቱ ሰው ግን ሊያውቀው የሚገባ ትልቁ ጠቃሚ እውነት ቢኖር ፦
    ወደ እግዚአብሔር የ ሚመራው አገልግሎት ሳይሆን ንጹህ ልብ መሆኑን ነው ።
እውነተኛ አገልግሎት የ አንድን ሰው መንፈሳዊነት ቀንሶ እስከሚጠፋ ድረስ ሊገኝ አይችልም ፤ ሰውየው ለራሱ የሚገባውን እንክብካቤ ሊያደርግ አልቻለምና ። እርሱ  “ . . . የ እግዚአብሄ መንግስት በመካከላችሁ ናትና . . .” ( ሉቃ 17፥21) የ ሚለውን ቃል ስለሚዘነጋና ሙሉ ትኩረቱን በውጪያዊው ጉዳይ ላይ ብቻ ስለሚያደርግ የ እግዚአብሔር መንግስት ከውጪ በህዝቡ መካከል እንዳለች አድርጎ ያስባል !
   አንድ አንድ አገልጋዮች በፒራሚድ የ ሚመሰል መንፈሳዊ ሕይወት ስላላቸው ለራህ ተጠንቀቅ ፤ እነርሱ በመጀመርያ እስከ ጫፍ ድረስ ወጥተው በኋላ ቁልቁል ይወርዳሉና ።
   እንደዚህ አይነቶቹ አገልጋዮች ጊዜ ቢኖራቸውም ያ ጊዜ የእነርሱ አይደለም ከዚህ በተጨማሪ ትኩረታቸውምስሜቶቻቸውም የእነርሱ አይደሉም። ሁሉም ጊዜ ፣ እንክብካቤ ና ስሜቶቻቸው የተሰጡት እነርሱ “ አገልግሎት” ብለው ለሚጠሩት ጉዳያቸው ነው። የ እነርሱን መንፈሳዊነት በተመለከተ ግን ምንም አይነት ጊዜ ሊያገኙ አይችሉም ፤ በልባቸውም ውስጥ ለዚህ ጉዳይ ምንም አይነት ፍላጎት የላቸውም ! አንዳንዶች ይህንን የሚቆጥሩት ለሌሎች መስዋዕት እንደሞህን አድርገው ነው!!
     የራስ መስዋዕትነት የቅድስና ስራ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። ይሁንና የራስን መንፈሳዊነት መስዋዕት ማድረግ ግን ኃጢአትም ጥፋትም ነው ። በአንድ ወቅት መጥምቁ ዩሀንስ “እርሱ ሲልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል ”(ዮሀ 3፡30) በማለት ተናግሯል ። እርሱ ይህንን ሲናገር በመንፈሳዊነት ወይም በእግዚአብሔር ፍቅር ፈጽሞ ለማነስ አይደለም ። ይህንን ለማለት ፈልጎ አይደለም !!  እርሱ ለማነስ የፈለገው በክብር ፤ በአገልግሎትና በዝና ነው ከዚህ በተቃራኒ የእርሱ መንፈሳዊነት የሚጨምረው በቦታው ላይ ክርስቶስ ራሱ ቤተክርስትያንን እንዲመራና ሙሽራይቱን እንዲቀበል ቦታን ሲለቅ ነው ። በእርግጥም መጥምቁ ዩሀንስ ያነሰ ይምሰል እንጂ ጨምሯል አርሱ የጨመረው በትሕትና ፣ በእግዚአብሔር ፍቅር ፣ በክርስቶስ ላይ ባለው ዕምነትና በጌታ ስራ ላይ ነው።
     ለራችሁ ተጠንቀቁ ! በአገልግሎት ውስጥ እያላችሁ መንሳዊነታችሁ ከቀነሰም ራችሁን ለማደን አንድ ርምጃ ተራመዱ ።
     አገልግሎትን ለመስጠት ከመንፈሳዊነታችሁ አትቀንሱ ፤ ስለመንፈሳዊነታችሁም ስትሉ አገልግሎታችሁን አታቁሙ ። ይልቁንም ከባከነ ጊዜአችሁ በመቆጠብ ለመንፈሳዊነታችሁ ለግሱ ። ዓለማዊ  ተከፋይነታችሁን በመቁረጥ መንፈሳዊነታችሁን ተንከባከቡ። ከቸልተኝነታችሁ በመንቃት የአገልግሎትን እውነተኛ አሰራር ተረዱ ። አገልግሎት የት እንዳላችሁ ሳታውቁ የምትሽከረከሩበት አዙሪት አይደለም።

 

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages