መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ማን ነው? - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Saturday, September 17, 2022

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ማን ነው?

 

መስከረም-

awude%2Bamet%2Bmetmike%2Bmelekot

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ማን ነው?
ቅዱስ ዮሐንስ በእናቱ ወገን ከነገደ ይሁዳ ነው። ቅዱስ ዮሐንስ በተለያየ ስሞች ይጠራል። እነርሱም፤
v  ፍቁረ እግዚእ /ከጌታ ዘንድ የተወደደ/፦ ይህ ስም የተሰየመበት ምክንያት በሕይወቱም በኑሮውም ጌታችንን ለመምሰል ይጥር ስለነበር ጌታችንም ይህን ጥረቱን ስለሚያውቅ ይወደው ነበር።  አንድ ቀን ጌታችን መታጠቂያውን ፈትቶ ባስቀመጠበት ወቅት አንስቶ በመታጠቁ ፍትወት ሥጋዊ ወደማዊ/የሥጋ ፈቃድ ጠፍቶለት ኑሮው እንደ መላእክቱ ሆኖለታል።
v ወልደ ዘብዴዎስ /የዘብዴዎስ ልጅ/፦ የታላቁ የቅዱስ ያዕቆብ ወንድም ስለሆነና አባቱ ዘብዴዎስ ስለሚባል ዮሐንስ ወልደ ዘብዴዎስ/ዮሐንስ የዘብዴዎስ ልጅ ይባላል።
v ወልደ ነጎድጓድ/የነጎድጓድ ልጅ/፦ ለጌታችን ባለው ሃይልና ቅንአት ከወንድሙ ከያዕቆብ ጋር ሆነው ባሳዩት የሃይል ሥራ ጌታችን ሁሉንም/ዮሐንስንና ያዕቆብን/ ውሉዳነ ነጎድጓድ በኤኔርጌስ / የነጎድጓድ ልጆች ብሏቸዋል።  ማር 3፤7 ሉቃ 9፤49። እንዲሁም ቅዱስ ዮሐንስ የጻፈው ወንጌል በጣም ጥልቅ የሆነውን የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነትን በመግለጥ ወልደ ነጎድጓድ የነጎድጓድ ልጅ ተብሏል።
v ነባቤ መለኮት /ታዖሎጎስ/፦ ነገረ መለኮትን ከሌሎች በበለጠ አምልቶ አስፍቶ አልቆ አጥልቆ በማስተማሩ ነባቤ መለኮት የመለኮትን ነገር የሚናገር ተባለ።
v አቡቀለምሲስ፦ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ባለ ራዕይ ማለት ነው። ሃላፊያትንና መጻእያትን በራዕይ ስለገለጠ ዮሐንስ አቡቀለምሲስ ተብሎ ለመጠራት በቅቷል።
v ፊቱ በሐዘን የጠቆረ፦ በዕለተ አርብ በእግረ መስቀሉ ተገኝቶ የጌታችንን መከራና ስቃይ በመስቀል ተሰቅሎ በማየቱ ከዚያች ዕለት ጀምሮ ፊቱ በሐዘን ተቋጥሮ ይኖር ስለነበር ይህ ስም ተሰጥቶታል።
ቅዱስ ዮሐንስ በገሊላ አውራጃ ይኖር ነበር። ከወንድሙ ከቅዱስ ያዕቆብና ከአባቱ ከዘብዴዎስ ጋር ዓሳ በማጥመድ ይተዳደር  ነበር።  እናቱ ማርያም እንደምትባል እና ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት እንደ ነበረች የቅድስት ቤተክርስቲያን ታሪክ ይነግረናል።  የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መከራው፤ ስቃዩ፤እንግልቱ በበዛበት ሰዓት ሳይሸሽ እስከ እግረ መስቀል የተከተለ ሐዋርያ ቅዱስ ዮሐንስ ነው።  በዚያች መከራ ቀን፤ በዚያች በዕለተ አርብ ያየው የጌታችንን መከራና ስቃይ እያስታወሰ ቀሪ ዕድሜውን በሙሉ የኖረው በዕንባ ነው።  ቅዱስ ዮሐንስ ጌታችን ተከተለኝ ብሎ የተጠራ ገና በወጣትነት ዕድሜው ሲሆን በዚህ ምድር ላይ የኖረው ደግሞ ለ99 ዓመታት ያህል ነው።  ቅዱስ ዮሐንስ ዋና መንበሩን በኤፌሶን አድርጎ ከአውሮፓ ወደ መካከለኛው ምስራቅ በሚወስደው መንገድና በተቆረቆሩት ከተሞች እየተዘዋወረ ወንጌልን በማስተማርና ለምዕመናን አብያተ ክርስቲያናትን እንዲተከል ታላቅ አስተዋጽኦ አድርጓል። በተጨማሪም ጳጳሳትን በመሾም አገልግሏል።  ወንጌልን በመስበኩ ምክንያት ንጉስ ድምጥያኖስ ክ81-96 ዓ.ም በጣዖት አምላኪዎች ተከሶ ለፍርድ ከቀረበ በኋላ በፍል ውሃ ተሰቃይቶ በፍጥሞ ደሴት ግዞት እንዲታሰር ተፈረደበት።  ራዕዩን ያየውና የጻፈውም በዚያ ቦታ ሆኖ ነው።  ቅዱስ ዮሐንስ ድምጥያኖስ በ96 ዓ.ም ሲገደል ከግዞት ተመልሶ ሶስቱን መልእክታትና ወንጌልን እንደጻፈ ይናገራል። አስቀድሞ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚወደው ደቀ መዝሙሩ ለቅዱስ ዮሐንስ  ቃል ኪዳን በገባለት መሠረት ሞትን ሳይቀምስ ተሰውሮ እነ ነቢዩ ኤልያስ፤ ቅዱስ ሔኖክ ባሉበት በብሔረ ሕያዋን በሕይወት ይኖራል።
ü የስሙ ትርጉም ፍስሐ ወሐሴት ማለት ሲሆን አባቱ ካህኑ ዘካርያስና እናቱ ኤልሳቤጥ ልጅ አጥተው ሲያዝኑ በነበሩበት ጊዜ በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት የተገኘ በመሆኑ ፍስሐ ወሐሴት ብለው ደስታቸውን አጣጥመውበታል። ሉቃ 1፤13 
ü መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ሁለት ዓመት ከመንፈቅ ሲሆነው ሄሮድስ በጌታ ምክንያት ወአዘዘ ሐራሁ ወፈነወ ይቅትሉ ኩሉ ሕጻናተ ዘቤተልሔም ወዘኩሉ አድያሚሃ ብሎ 14 እልፍ 4 የቤተልሔም ሕፃናት ሲያስገድል እናቱ ኤልሳቤጥ  ወደ በርሃ ይዛው ሸሽታ እመቤታችን ከስደት እስክትመለስ ድረስ ስታሳድገው ከቆየች በኋላ አረፈች። ከዚያም ቶራ የምትባል እንስሳ እያጠባችው አደገ፡፡ በኋላም የግመል ጸጉር ለብሶ የበርሃ ማርና አንበጣ እየተመገበ ኖረ ፡፡
ü  30 ዘመን ሲሞላው ቃለ ዓዋዲ ዘይሰብክ በገዳም ወይብል ጺሑአ ፍኖቶ ለእግዚአብሔር ኢሳ 403-5 ተብሎ በኢሳይያስ እንደተነገረ ከጌታ መንፈቅ ያህል ቀድሞ ወጥቶ ‹‹ ነሥሑ እስመ ቀርበት መንግስተ ሰማያት ›› እያለ ማስተማር ጀመረ።
ü ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሲያጠምቅ የሥላሴ ምሥጢር ተገለጠለት፤ አንድነት ሦስትነት ተገለጠለት ፡፡
ü  ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ 40 ቀንና 40 ሌሊት ጾሞ ሲመለስ ተመልክቶ በዚያ ሲያጠምቅ በነበረበት ሥፍራ ብዙ ሰዎች ተሰብስበው ነበርና ‹‹ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘየአትት ኃጢአተ ዓለም ‹‹ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ›› ብሎ አምላክ ወልደ አምላክነቱን መስክሯል፡፡ ዮሐ 1፤29
መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስና ሄሮድስ
ü በዚያን ዘመን ንጉስ ሄሮድስ  የወንድሙን ሚስት ሄሮድያዳን አግብቶ ነበር።  በዚህም ምክንያት የወንድሙን ሚስት ማግባት እንደሌለበት ገሰጸው።
ü  ሄሮድስም እኔን ንጉሱን እንዴት ይገስጸኛል በማለት አሰረው።
ü የሄሮድስ ልደትን ለማክበር ሰው ተሰብስቦ ሳለ የወንድሙን ሚስት የሄሮድያዳ ልጅ የሄሮድስን ልደት ለማክበር ስትል ዘፍና አስደሰተችው።
ü  የመንግሱትን እኩሌታ እስከ መስጠት ድረስ ቃል ገብቶላት ስለነበር፤ ከእናቷ ጋር በመመካከር የቅዱስ ዮሐንስን አንገት ቆርጦ እንዲሰጣት በህዝቡ ፊት ጠየቀችው። እርሱም ቃል በገባላት መሰረት ቆርጦ ሰጣት።

እናቷ ጥልፍ እየጠለፈች ነበር ንጉሥን ሳታፍሪ ስትዘልፊ የነበርሽ አንደበት ዛሬ ተዘጋሽ እያለች በመስሪያዋ ምላሱን ስትጠቀጥቀው ራሱ ክንፍ አውጥቶ ሄሮድስን የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም ብላ ሦስት ጊዜ በራሱ ላይ ዞራ ወጥታ ሄዳለች 15 ዓመት አስተምራ ሚያዝያ 15 ቀን አርፋለች ፡፡
ከዚህ በኋላ ሄሮድያዳ ምን ሆነች ቢሉ?
ü ሄሮድያዳም ምድር ውጣታለች
ü ብላቴናይቱም እንደእብድ ሁና ሄሮድስን ስትዘልፈው አስገድሏታል ፡፡

አዲስ ዓመት በመጥምቁ ዮሐንስ ስም የተሰየመበት ምክንያት?
ü ሰማዕት የሆነው ጳጉሜ 1 ቀን ታስሮ መስከረም 2 ቀን አንገቱን በሰይፍ ተቀልቶ ስለሆነ የሰማዕትነት ቀኑ ከአዲስ ዓመት ጋር አንድ በመሆኑ፡፡
በማቴ 1111
ü እውነት እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል መጥምቁ ዮሐንስን የሚበልጥ አልተነሳም ተብሎ የተነገረለት የጻድቃንና የሰማዕታት ርዕስ እንደመሆኑ
ü አዲስ ዓመት በዓልም የበዓላት ሁሉ በኩር ርእስ ነውና በስሙ ተጠርቷል፡፡
ü መጥምቁ ዮሐንስ ከነቢያት መጨረሻ ከሐዋርያት መጀመሪያ ተገኝቶ ዘመነ ሐዲስን ስለሰበከ
ü የሁለቱ የዘመነ ሐዲስና የዘመነ ብሉይ መሸጋገሪያ ጊዜ ላይ እንደነበረ የሁለቱ ዘመናት የአሮጌውና የአዲሱ የምንሸጋገርበት የዘመን መለወጫ ቀን መታሰቢያ የአዲስ ዘመን መግቢያ ተደርጎ እንዲቆጠር
ü ጌታ ባረገ 180 . በእስክንድርያ ሊቀጳጳስ የተሾመው ቅዱስ ዲሜጥሮስ ተገልጾለት ባሕረ ሐሳብን ሲደርስ በዮሐንስ ጀምሮ ደርሶታል፡፡
ü በእስክንድርያ/በግብፅ/ አና በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በዓላት የሚከበሩትና አጽዋማት የሚገቡት ከዚህ ዕለት ተነስቶ ስለሆነ ‹‹ ርዕሰ ዐውደ ዓመት ዮሐንስ ወላዴ መጥቅዕ ወአበቅቴ›› ትርጉሙም ‹‹ የዓመት በዓላት ራስ ዮሐንስ ጊዜ መቀመሪያ መጥቅዕና አበቅቴን የምትወልድ አንተ ነህ›› እየተባለ ይዘመርለታል ቀኑም በስሙ ይጠራል ዘመኑም በዚህ ዕለት ይታደሳል ይለወጣል፡፡

ከመጥምቀ መለኮት ከቅዱስ ዮሐንስ ረድኤት በረከት ይክፈለን!!!

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages