አቡነ ሐራ ድንግል ገዳም ክፍል አንድ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Wednesday, September 28, 2022

አቡነ ሐራ ድንግል ገዳም ክፍል አንድ


ከሁሉ አስቀድመን የአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንልጆች የሆን እኛ የክርስቶስ ወገኖች ሰዎች ነገርን ከማብዛት በማሳነስ ነገርን ከማስረዘም በማሳጠር ክቡርና ልኡል ትሩፋቱ ፍፁም ገድሉም ብዙ የሆነ ምስራቃዊ የክብር ኮከብ አርያማዊ የፅድቅ ጸሀይ የኦርቶዶክሳዊ ሀይማኖት ዓምድ የመንፈሳዊ ምግባርማደሪያ የሆነየአባታችን ሐራ ድንግልን ገድሉንና ትሩፋቱን የፅድቁንም ስራ እንጽፍ ዘንድ ህይወትን ሰጪ በሚሆን በባታዊ አድሮ በሚኖር ገዳማዊውን በሚጎበኝ የአለማዊውንም ሰው በደል በመለኮታዊ ስልጣኑ በሚያስተሰርይ በአምላክ ፈቃድ ለመጀመር ተግተን ተመኘን፡፡ 

ለሁላችንም የጥምቀት ልጆች ከኦሪታዊው ከሙሴና ከወንጌላዊው ከዮሀንስ ጋር አሸናፊ እግዚአብሄርን በቀናች ሀይማኖትና በመልካም ምግባር ካገለገሉት ከጻድቃንና ከመነኮሳትም ጋር ሰማያዊ የነፍስ ደስታ እድልን ያድለን ክብር ምስጋና ለእርሱ ይሁን ለዘላለሙ አሜን፡፡ አቡነ ሐራ ድንግል አስቀድመን በመጻፋችን የጠራነው የዚህ ጻድቅ አባቱና እናቱ በላጉና ምድር ይኖሩ ነበር ፡፡ እርስዋም ከደራ ምድር አንድ ክፍል ናት:: አባቱም ዮሐንስ የሚባል የሬማ ቄስ ነበር:: እናቱም ወለተ ጊዮርጊስ ትባል ነበር ሁለቱምበወገን ከከበሩ ቤተሰቦች ነበሩ እነርሱም ጻድቃንና ደጋግ ሰዎች እግዚአብሄርን የሚፈሩ ነበሩ ከክፋትም ስራም ሁሉ የራቁ ነበሩ በበጎ ምግባርም ሁሉ የጸኑ ነበሩ ሶስት ወንዶች ልጆች ነበሯቸው ከእነርሱም አንዱ የአለም መብራት የኢትዮጵያ ብርሀን ሐራ ድንግል ነበር ይህንም ገድለኛ ልጃቸውን ከመውለዳቸው አስቀድሞ ገንዘባቸውን ለድሆችና ለጦም አዳሪዎች ለባልቴቶችና ለሙት ልጆች ለካህናትና ለምእመናን ለህዝበ ክርስቲያኑ ሁሉ ይሰጡ ነበር :;ይህንም ያደርጉ ነበር ስጡ ይሰጣችኋል ዳግመኛም ለሌለው ይስጥ የሚለውን የወንጌል ቃልና ሌላውም መጽሀፍ ካለህ ስጥ ከሌለህም እዘን የሚለውን ቃል አስበው ነው:: 

በዚህም ነገር ላይ እንዲህ እያሉ ይጸልዩ ነበር አንተን ደስ የሚያሰኝ ፈቃድህንም ሁሉ የሚያደርግ በደግነቱም ለፍጥረትህም ሁሉ የሚጠቅም ሰሎሞን:-ብልህልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል ሰነፍ ልጅ ግን እናቱን ያሳዝናል ብሎ እንደተናገረ የእኛንም ልብ ደስ የሚያሰኝ ጠቃሚ ልጅ ስጠን ጸሎትም እንደሚጠቅም ከቅዱሳት መጻህፍት ምሳሌ አግኝተው ይህን ሁሉ ጸሎት ጸለዩ:: ሀና በአንደኛ መጽሀፈ ነገስት ለሚጸልይ የጸሎትን መልስ ይሰጠዋል የጻድቃኑንም እድሜ ያረዝማል ብላለች ዳዊትም:-66 መዝሙር መንገድህን ለእግዚአብሄር ግለጥ በእርሱ ታመን እርሱም ያደርግልሀል ብሏል፡፡


ከዚህም በኋላ እግዚአብሄር ጽሎታቸውን ልመናቸውንና እንደ ጣፋጭ ዕጣንና እንደ ንጹህ መሥዋዕት በተቀበላቸው ጊዜ በዚያች ዕለት በጋብቻ ስርአት ተገናኙ ሁለቱም በንጽህና ሐብል የታሰሩ ነበሩና ዝሙትንና ሀጢያትንም አያውቁም ነበርና ነገር ግን :-ወንድ ሁሉ በሚስቱ ጸንቶይኑር ሚስትም በባልዋ ጸንታ ትኑር በሚለው የመጽሀፍ ስርዓት እርስ በርሳቸው ይጠባበቁ ነበር፡፡ በዚያችም በተገናኙባት እለትም ወለተ ጊዮርጊስ መልካም ስራው እንደጸሀይ አወጣጥ የሚያበራ የኢትዮጵያ ብርሀን ሐራ ድንግልን ጸነሰችው ከጸነሰችውም በኋላ በዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በንጉስ አጽናፍ ሰገድ ወለደችው:: እርሱንም በወለደች ጊዜ እጅግ ደስ አላት አባቱና ዘመዶቹም እጅግ ደስ አላቸው ሀሴትም አደረጉ ሃጥአንን በእግዚአብሄር ዘንድ በጸሎቱ የሚያስምራቸውና ዳዊት በ111ኛው መዝሙሩ :-መልካም ዛፍ መልካም ፍሬ ያፈራል ክፉ ዛፍ ግን ክፉ ፍሬን ያፈራል ዛፍ ከፍሬው ይታወቃልና ብሎ እንደ ተናገረ ወላጆቹን በምእመናን ሁሉ አንደበት የሚያመሰግናቸው የተባረክ ልጅ ተወልዶላቸዋልና በአርባኛው ቀንም ይህን ልጃቸውን ሐዋርያት በኢየሩሳሌም አንድ ሆነ እንደ አዘዙትሥርዓት የዚያች ቤተክርስቲያን ወሰዱት ያንጊዜም በጥምቀት ፀጋ የወለደው ስሙን ሐራ ድንግል ብሎ ሰየመው:: ከዝያም በኋላ አባቱና እናቱ ተቅብለው ወደ ቤታቸው ወሰዱት በህግና በሥርዓትም አሳደጉት የሰሎሞንን ቃል አውቀው ቅዱሳት መጽሀፍትን ብሉይ እስክ ሀዲስ የዳዊትንም መዝሙር ለሚያስተምር መምህር ሰጡት ያም ህፃን ቅዱሳት መጽሀፍትን ይሚሉትን አውቆ ስላስተዋለ እስኪያድግና አቅመ አዳም እስኪደርስ ድረስ ለትምህርት የተጋ ሆነ በመምህሩ ፈቃድ የድቁና ሹመት ከጳጳሱ ይቀበል ዘንድ በዚያ ወራት ሄደ የድቁና ሹመትም ተቀብሎ በደስታና በሀሴት በሰላምና በህይወት ወደ መንደሩ ተመልሶ ገባ


የጥበባት ባህርና የቋንቋ ባለቤት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም የትምህርት ምንጭ ለሆነው ለደቀ መዝሙሩ ለጢሞቴዎስ በላከው መልእክቱ:-የዲያቆናት ንጹሓን ይሁኑ ለጸሎትም የነቁና የተጉ ይሁኑ ብሎ እንደተናገረ በንጽህናና በቅድስና በጸሎትና በጭምተኝነት በፍቅርና በትህትና እግዚአብሄርን ያገለገለው ጀመር፡፡ አባታችን ሐራ ድንግልም በእነዚህ የብሉይና የሐዲስ መጽሀፍት ቃላት ጸንቶ ሲኖር ክቡር ዳዊት 88 መዝሙር ሞትን ሳያይ በህይወት የሚኖር ማነው? ዳግመኛም 143 መዝሙር ሰውስ ከንቱ ይመስላል ዘመኑም እንደ ጥላ ያልፋል ብሎ እንደተናገረ:: በአቤልና በሴት ከተጀመረው ከዚህ ሞት የሚድን ስለሌለ አባቱና እናቱ ከዚህ ዓለም ድካም ዓረፉ ወደ ዘላለም ህይወትም ሄዱ አባታችን ሐራ ድንግልም በወላጆቹ ሞት የመረረ ልቅሶን አለቀሰ አዘነም፡፡ 

አባታችን ሐራ ድንግልም ከአባቱና እናቱ ሞት በኋላ ሬማ በምትባል ደሴት እየተመለለሰ በቤታቸው ውስጥ ለጥቂት ወራት ተቀመጠ ከሬማም ወደ ዘጌ ይሄድ ነበር ከዘጌም ወደዚያው ወደ ሬማ ይመለስ ነበር እንደዚህ አለም ሰዎችም ሚስት ሊያገባ አልወደደም ነገር ግን በድንግልና ኖረ:: ልብሰ ምንኩስናም ሳይለብስ አርባ ዓመት ሆነው ከዚህም በኋላ በጽኑዕ ደዌ ታመመ የንዳድ በሽታም ያዛው ክደዌው ጽናት የተነሳም በስጋውና በነፍሱ ከእግዚአብሄር ፈውስን ያገኝ ዘንድ ልብሰ ምንኩስናን ለመልበስ ወደደ መዓዛ ድንግል የተባለውን የሬማ መምህር ልብሰ ምንኩስናን ይሰጠው ዘንድ ለምኖ ነገረው እርሱም ልብሰ ምንኩስናን አለበሰው ለወጣንያን ለማእከላውያንና ለፍፁማንም መነክኮሳት የሚገባቸውን የምንኩስናን ህግ ሁሉ ሰጠው ከዚህም በኋላ እግዚአብሄርን ከሞት ስላዳነው ከደዌው ተፈወሰ::

ከዚህም በኋላ የቅስና ማረግን ከዚያ ጳጳስ ከተቀበለ በኋላ በዚሁ ደስ እያለውናሀሴት እያደረገ ከመንገዱ ተመልሶ ወደ ቤቱ ገባ እግዚአብሄር እርሱ የተመኘውንና የፈለገውን አድርጎለታልና በዚህ ሁኔታ እያለ ወደ አለም መመልስ አልፈለገም ተመልሶ ከዘመዶቹና ከሀገሩ ሰዎች ተሰውሮ ወደ ሸዋ ሊሄድ ወደደ ወደ አሰበበት ለምድረስ በመንገድ ላ ሲሄ ዘመዶቹ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ያገኙትና ከ እነርሱም አንዱ የወንድሙ ልጅና የልቡ ወዳጅ ስለንበር ሁሉንም ያነሳሳቸው አርከ መርዓዊ ይባላል እነርሱም ግራርያ በተባለ ሀገር ያዙትና ወዴት ትሄዳለህ አሉት እባክህ ወደ ሀገርህ ተመለስ ለሀገርና ለዘመዶችህ የሚቀርብ ገዳም እንፈልግልሃለን አንተም እንዳዘዝከን እንደርጋለን እንጂ ከፈቃድህ አንወጣም አንተ አባታችን ጽድቀህ እኛንም በጽድቅህ እንድታጸድቀን ትሉ ከማያንቀላፋ እሳቱም ከማይጠፋ ከገሀነም እሳት እንድታድነንም እንወዳለንና እንደማንሸነግልህ ም በአምላካችን በ እግዚአብሄር ስም እንምልልሀለን ይሄን ቃላቸውን ከሰማ በኋላ እሺ አላቸው::

እንሱም 7 ምሳሮች ይዘው ከቁስቋም ጀምረው ገዳም እስካደረገው ድረስ መንገዱን ይጠርጉ ዛፎችንም ይቆርጡ ጀመሩ ወደ ገዳሙ በደረሱ ጊዜ ማረፊያዬ ይህች ናት በድካሜም ጊዜ የማርፍበት ትንሽ ቤት ስሩልኝ እንጂ ከዚህ ወደ ሌላ አትሂዱ እስከሞቴ ድረስ በ እርሷ እንድኖር እግዚአብሄር አዞኛልናየስጋዬንም በድን እስከ ሙታን ትንሳኤ ድረስ በውስጧ ይኖራል አላቸው በዚያችም ቀን ዕንጨቱን ቆርጠው መሬቱን ቆፍረው አጥር አጠሩለት እርሱንም በገዳሙ ትተውት ወደ ቤታቸው ሄዱ አባታችን ሐራ ድንግልም በተራበ ጊዜ እንጀራ አይበላ ነበር ጥቂት ምስር አተርና አደንጓሬ ይበላ ነበር ብትንሽ ጽዋ መክደኛ ጽዋ ሰፍሮ በትንሽ ድስት ይቀቅለው ነበር ያም በጽዋው መክደኛ ሰባት መስፈሪያ ነበር በሶስት አንድ ቀን ይመገበው ነበር ከምድርም ፍራፍሬም በበላ ጊዜ እሼ የሚባል ፍሬ ይመገብ ነበር ከምናኔው በኋላ ግን ከውሃ በቀር ሌሎች መጠጦችን አልጠጣም ነበር::ያንጊዜም ብዙዎች አራዊት አንበሶች ነብሮች ዝሆኖች ተኩላዎችና ጅቦች የዱር እንስሳዎች ያስፈራሩት ዘን ወደ እርሱ መጡ እርሱ ግን እግዚአብሄር ከእርሱ ጋር ስለነበር ከፊቱ እንዲሸሹ አስፈራርቶ አስደነገጣቸው እንጂ አልፈራቸውም ይህም ነገር ከሆነም በኋላ የቅል ዓይነት ተክልና ወይን ሎሚና ኮክ ተከለ እነዚህንም ተክሎች ከሩቅ ወንዝ ውሃ በእጁ ቀድቶ በትከሻው ተሸክሞ ያጠጣቸው ነበር መንገዱም ሩቅ ስለነበር አባታችን ሐራ ድንግል እንዲህ ብሎ ጸለየ ከ እናቴ ማህጸን ያወጣሀኝ እስከ እዚች ሰአት ያደረስከኝ ፈጣሪዬ እግዚአብሄር ሆይ እስራኤል ከግብጽ በወጡ ጊዜ ሙሴ ከዓለት ውሃን እንዳወጣ ከዚህ ምድር ውሃን አውጣ ዘንድ ጸሎቴንና ልመናዬን ስማኝ ይህን ብሎ በሁለት ረድፎች ምድሩን ቆፈረ በመስቀልም ምልክት ባረካቸው ወዲያውኑ ከሁለቱም ረድፎች ውሃዎች ፈሰሱ በፈለቁት ውሃዎች በየጊዜው እንዲያፈሩና ሊያዩት ወደ እርሱ ለሚመጡት ሰዎች ምግብ እንዲሆኑ እንዚህን ተክሎች አጠጣቸው ለሚልውምኑትም ድሆችም ቅጠሉ ፍሬ ያፈራውን አይነት በገበያ አሽጦምጽዋት ይሰጣቸው ነበር::በዚያ ጊዜም የበጎ ነገር ጠላት ሰይጣን በሴት አምሳል በንጭ ሀር በወርቅበብር በጉትቻዎችና በቀለበቶች አጊጦ መጣና እንዲህ አለው ለምን ብቻህን ትኖራለህ ? ሁለት ሆነው መኖር ሰዎች ልማዳቸው ነውና ከ እኔ ጋር ብትኖር አይሻልህምን? አባታችንም ትቆጣ የ እግዚአብሄርን ቃል በሚጸልይበት በጠበል እቃ የነበረውን ውሃ በሰይጣ ረጨበት ሰይጣንም ድንግጦ ሸሸ በባህርም ስጠመ አባታችን እስኪሰማ ድረስ ባህሩን አወከው አባታችንን ለማሳት ሰባት ጊዜ መጣ ነገር ግን በ እግዚአብሄር ሀይል ድል ተደረገ::

አንዲት ሚዳቆ ነብር እያባረራት መጣች ወደ አባታችን ሐራ ድንግል ቤትም ገብታ በእርሱ ተመአጥና ከ እግሩ በታች ተጋደመች አባታችንም ወደ ፈጣሪው ወደ እግዚአብሄር እየጸለየና እየለመነ ተቀምጦ ነበር ያቺን ሚዳቆ የሚያባርራት ነብርም መጣ አባታችን ወዳለበት ደርሶ በደጁ ቆመ አባታችንንም ባየው ጊዜ ጊዜው ቀን ስለ ነበረ ፈርቶ ወደ ውስጥ አልገባም ያም ነብር ተቆጥቶ በዚያው ቦታ ተፍገመገመ አባታችን ነብሩን ገድለህ ትበላት ዘንድ እግዚአብሄር አልሰጠህም ነብሩም ይህን ነገር ከአባታችን ቃል ሰምቶ ሳይገድላት ሄደ በዚያች ሌሊት በእርሱ ዘንድ አደረች በማግስቱም ከቤቱ ወጥታ በደጅ ስትመላለስ አባታችን ባያት ጊዜ እንዲህ ብሎ አሰናበታት ከቦታሽ አባርሮ ያሳደደሽ ወደ እኔም ያደረሰሽ ያ ነብር ትናንት ስለሄደ ወደ ቦታሽ ሂጂ ይህንም ሰምታ ወደ ቦታዋ ተመለሰች:;
አባታችንም ሁለት ደቀመዝሙሮች ነበሩት ወንዱ እሱን ያዘዘውን የሚፈጽም ነበር ተስፋዬ እና አመተ እግዚእ አለምን ንቃወደ ገዳብ የገባች ነበረች እርሳውም ከአባታችን ቤት ትንሽ በሚርቀው ቤት ተቀምጣ ከምናኔዋ ጀሮ በሞት እስከ ተለየች ድረስ ረዳትና አገልጋይ ሆና ራሷን ለአባታችን ሰጠች እርስዋም በስጋ ዝምድና ከሚቀርቡት አንድዋ ነበረች እርሷም በአገልግሎቷና በታዛዥነቷ እንደዚህ ይሁን የሚለውን ፈቃዱን በመፈጸም እጅግ ደስ አሰኘችው በምግባርዋ ደግ በነገሯም እውነተኛ በልቡናዋም ብልህ ነበረች::

ከዚህም በሃላየአንዲት ታቅ ሴት አሽከሮች ወደ አባታችን መጡ ሊጣሉትም ወደቤቱ ገቡ አንተ ከንጉሱ ፈቃድ ወጥተህ በአመጽ የምትኖር የንጉስ ከዳተኛ አይደለህምን እያልይ ፈጽመው ሰደቡት ከገቡበትም ወጥተው የ አባታችን የወይን ዘለላም ምንም ሳያስቀሩለት ቆረጠው ወሰዱ አባታችንም ምንም አልተናገራቸውም የወሰዱትንም ወይን ለእመቤታቸው የወይኑ ዘለላ ሰጡ እመቤታቸውም ይሀ ወይን ከማን አመጣችሁ ሐራ ድንግል ከሚባለው መንኮስ ነው አላት አንዱንም የሆድ በሽታ ይዞ አንጀቱን ቆረጠው እመቤታቸውም እነዚህን አንተን ያስቀየሙ የበደሉና ማርልኝ ብላ አሽከሮችን ላከች እግዚአብሄር ይቅር የሚላቸውና በደላቸውና የሚተውላቸው ከሆነ ይቅር እላቸዋለሁ አሽከርም በተመለሰ ጊዜ ሆዱን የቆረጠው ሞተ ጻድቁ አባታችንን ስለተሳደበ እግዚአብሄር ትቆጥቶታልና ይህ የሰሙትን የተደረገውን ባዩ ጊዜ አደነቁ:: ይህ ድንቅ ነገር ከሆነ ረዥም ወራት በሃላ አመተ ወልድ የተባለች አንዲት ሴት ታመመች እርስዋም በዚሁ በሽታ ሞተች መላእክተም ሞትም ነፍስ ወሰዱ ያችንም ነፍስ እያጣደፉና እያዳፉ ወደ ፈጣሪዋ አደረሳት በዚች ሰአትም አባታችን ሐራ ድንግል ወደ ፈጣሪው ወደ እግዚአብሄር እንዲህ እያለ ጸለየ አለቀሰም ይህችን ዛሬ የሞተችውን ሥጋዋም በመሬት ተጥሎ በነፍስዋ ወደ አንተ የመጣችውን ማርልኝና አንሳልኝ ነፍሴንና ስጋዬን በአንተ ላይ ጥያለሁ ብላ በእኔ ላይ እንደ ተማጠነች አቤቱ አንተ ራስህ ታውቃለህና በህይወት ሳለችም እንዳገለገችኝ አንተ ራስህ ታውቃለህ አባታችንም ይህን ጸሎት ጸልዮ ዝም አለ እግዚአብሄርም ይህችን ነፍስ ለምን ወደ እኔ አመጣችሃት የሕራ ድንግል አደለች የ እርሱ ስለሆነች ወደ እርሱ መልሳት እርሳም በስማይ ሳለች ከፈጣሪዋ አንደበት ከሰማች በኋላ የመላእክት ቅዱስ ገብርኤልን ለወዳጄ ሐራ ድንግል ሶስት ጊዜ እንዲህ ብለህ አዋጅ ንገር ሲለ ከዚያ ከፈጣሪ አንደበት ሰማች:: 

ሐራ ድንግል ሆይ በ እጅህ የተባረከውንና በቃልህ የተጽናናውን ስምህን የጠራውንና መታሰቢያህን ያደረገውን ለተራቡትም ለተጠሙትም እህልና ውሃ በመስጠት በዓልህን ያከበረውን ሀጢአተኛና በደለኛ ሳለም በጸሎትህና በቃል ኪዳንህ የታመነውን የገድልህንም መጽሀፍ ያጻፈውን ያነበበውንና የተረጎመውን የሰማውንና ለሰዎች ያሰማውን አጽምህንም እየጠበቀ በገዳምህ የተቀመጠውን አንተን ወድዶ ከሩቅ ወይም ከቅርብ ሀገር በመምጣት ገዳምህን የጎበኘውን ወንድ ልጁንና ሴት ልጁንም በስምህ የጠራውን እነዚህ ሁሉ በየወገናቸው ከስጋና ከነፍስ ባርነት ነጻ የወጡ ይሆኑ ዘንድ እስከ ሰባት ትውልድ ምሬልሃለሁ አንተ አገልግለሃልና ከህፃንነትህም ጀምረህ እስከዚች ሰአት ፈቃዴን ፈጽመሃልና:: በሞት ከሥጋዋ የተለየች ያች ነፍስም ይህን ነገር በሰማች በኋላ ከሰማይ ተመለሰች ከሥጋዋ ጋር ተዋህዳ በአባታችን ጸሎት ተነሳች ለወዳጄ ሐራ ድንግል ሂድና አዋጅ ንገር ብሎ መላኩ ገብርኤልን ሲያዝዘውከ እግዚአብሄር የሰማችውን ቃል ኪዳን ለሰዋች ተናገርች አባታችን ሐራ ድንግልም በጸጋ አወቀ የእግዚአብሄር ምስጢር ባየችው በዚች ሴት መነሳት ደስ አለው::

እግዚአብሄርም ለአባታችን ሁለት ቃል ኪዳን ሰጠው አንደኛው ያቺ ሴት ናት ሁለተኛውም ከዚህ አለም በሞት ተለይቶ ወደ ዘላአለም ህይወት በሄደ ጊዜ እግዚአብሄር የሰጠው ነው:: የአባታችን ሐራ ድንግልም የእረፍቱ ቀን በደረሰ ጊዜ እግዚአብሄር የምህረትና የይቅርታ ቃል ኪዳንን ይሰጠው ዘንድ ከሰማይወደ እርሱ መጥቶ ወዳጄ ሐራ ድንግል ሆይ ስለ እኔ ብዙ አመታትን ደክመሃል እኔም እንዲህ ብዬ ቃልኪዳ እስትሃለሁ:: ሐራ ድንግል ሆይ በ እጅህ የተባረከውንና በቃልህ የተጽናናውን ስምህን የጠራውንና መታሰቢያህን ያደረገውን ለተራቡትም ለተጠሙትም እህልና ውሃ በመስጠት በዓልህን ያከበረውን ሀጢአተኛና በደለኛ ሳለም በጸሎትህና በቃል ኪዳንህ የታመነውን የገድልህንም መጽሀፍ ያጻፈውን ያነበበውንና የተረጎመውን የሰማውንና ለሰዎች ያሰማውን አጽምህንም እየጠበቀ በገዳምህ የተቀመጠውን አንተን ወድዶ ከሩቅ ወይም ከቅርብ ሀገር በመምጣት ገዳምህን የጎበኘውን ወንድ ልጁንና ሴት ልጁንም በስምህ የጠራውን እነዚህ ሁሉ በየወገናቸው ከስጋና ከነፍስ ባርነት ነጻ የወጡ ይሆኑ ዘንድ እስከ ሰባት ትውልድ ምሬልሃለሁ አንተ አገልግለሃልና ከህፃንነትህም ጀምረህ እስከዚች ሰአት ፈቃዴን ፈጽመሃልና::

አባታችን ሀራ ድንግል ይህን ቃል በሰማ ጊዜ እግዚአብሄርን ሲያመሰግን እንዲህ አለ አምላኬ ሆይ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ ቅዱስ ስምህንም ለዘላለም አከብራለሁ ሁልጊዜ አመሰግንሃለሁ ስምህንም ለዘላለም ዓለም አከብራለሁ ደግ ወይም ክፉ ቢሆን በእኔ የተማጠነ ሰው ሁይድን ዘንድ ይህን ቃል ኪዳን ሰጥተሀኛል እግዚአብሄርም ይህን ምስጋና ከእርሱ ከተቀበለ በኋላ ከእርሱ ዘንድ ሄደ:: ገዳሙንም እንዲህ እያለ ባረካት የአብና የወልድ የመንፈስ ቅዱስም በረከት በገዳሜና ስሜን በሚተሩ ሁሉ ላይ ይደር አምላክን በወለደች የ እመቤታችን የማርያም በረከትም በገዳሜና እኔን በሚወድዱ ሁሉ ላይ ይደር የሚካኤልና የገብርኤል በረከት የማያንቀላፉ ትጉሃን ዝም የማይሉና አመስጋኞች የሆኑ የሱራፍኤልና የኪሩቤል በረከት በገዳሜና በእኔ በሚማጸኑ ሁሉ ላይ ይደር የ እስጢፋኖስ የጊዮርጊስ የመርቆርዮስ የፋሲለደስ የቴዎድሮስና የገላውዴዎስ የድል አድራጊዎች ሰማእታት ሁሉ በረከት በገዳሜና ፈቃዴን በሚፈጽሙት ሁሉ ላይ ይደር የ አባታችን አቡነተክለሀይማኖትና የ አባታችን አዎስጣቴዎስ የ አባታችን የገብረ መንፈስ ቅዱስና በኢትዮጵያ ውስጥ በገዳማትና በአድባራት በደሴቶችም የሚኖሩት ሁሉ በረከት በገዳሜና በውስጥዋ ሆነው አስከሬኔን በሚጠብቋት ሁሉ ላይ ይደር የሀይማኖት አምድና የቸርነት መዝገብ የሆነው እንደ መላእክትም በንጽህና የተሸለመው አባታችን ሐራ ድንግል ይህን ቃለ ቡራኬ ከተናገረ በኋላ በኢያቄምና በሐና በፋሲለደስና በገላውዴዎስ በፊቅጦርም በዓል ጥር አስራ አንድ ቀን ከዚህ ከሀላፊው ዓለም ድካም አረፈ:: በአሉም ጥር 11 ቀን በታላቅ ድምቀት በባህርዳር ይከበራል፡፡

ምንጭ ገድለ አቡነ ሐራ ድንግል ጽሎቱና በረከቱ ከሁላችን ከህዝበ ክርስቲያን ጋር ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን!

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages