ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ አስኮ ደብረ ገነት ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ለሚያሠራው አዲስ ቤተልሔም የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ!! - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Wednesday, September 21, 2022

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ አስኮ ደብረ ገነት ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ለሚያሠራው አዲስ ቤተልሔም የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ!!

(መስከረም 11 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ) የአዲስ አበባ እና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ እንዲሁም የአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ የቦርድ ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት ሥር የሚገኘው የአስኮ ደብረ ገነት ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በዘመናዊ መልኩ ለሚያሠራው አዲስ ቤተልሔም የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል። ብፁዕነታቸው ከመሠረት ድንጋይ ማስቀመጥ በኋላ ባደረጉት ንግግር የቤተክርስቲያን ዋና ተግባር መንፈሳዊ አገልግሎትን ማሳለጥ ቢሆንም ልማታዊ ሥራዎችን ማከናወንም የሚመከር ነው ብለዋል። አክለውም በዛሬው ዕለት የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጥንለት ቤተልሔም በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ሲሉ አባታዊ መመሪያ አስተላልፈዋል። በመርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅን ጨምሮ የብፁዕነታቸው ፕሮቶኮል ሊቀ ጉባኤ አባ ኃይሉ እንዳለ፣ የትምህርትና ሥልጠና ዋና ክፍል ኃላፊ መ/ም በቃሉ ወርቅነህ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ፈቃደ ፣ የደብሩ ሊቃውንት እና ሰ/ት/ቤት አባላት ተገኝተዋል።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages