በታሪካዊቷ እመ ምዑዝ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንድነት ገዳም በጎርፍ አደጋ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ። - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Wednesday, September 21, 2022

በታሪካዊቷ እመ ምዑዝ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንድነት ገዳም በጎርፍ አደጋ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ።

ከ400 ዓመት በላይ ያስቆጠረችው እመምዑዝ ፍቅርተ ክርስቶስ አንድነት ገዳም በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት መቄት ወረዳ የምትገኝ ሲሆን ሐምሌ 16 እና ነሐሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም በተከሰተው ከፍተኛ የጎርፍ አደጋና የመሬት መንሸራተት ጉዳቱ እንደደረሰ ተገልጿል። ከ8 ዓመት በፊት ገዳሟን ከመሬት መንሸራተት እና ከጎርፍ አደጋ ለመከላከል በወረዳው ተስርቶ የነበረ እርከን እና አካባቢውን ሸፍነውት የነበሩ ዛፎች በጎርፍ በመወሰዳቸው ምክንያት በገዳሙ ዙሪያ በሚገኙ ብዙሃ ህይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። በተከሰተው ጎርፍ አደጋና የመሬት መንሸራተት የገዳሙ ወንድ መነኮሳት የሚኖሩበት ቤትና እንግዳ የሚቀበሉበት አዳራሽ ሙሉ በሙሉ መውደሙ ተገልጿል። በተጨማሪም ለገዳሟ የገቢ ምንጭ ሆኖ ሲያገለግል የነበረው የአገዳ እርሻ መሬቱ በመንሸራተቱ ጥቅም እንዳይሰጥ አድርጎታል። በወረዳው አስተዳደር አደጋውን የሚከላከል እርከን እየተሰራ የነበረ ቢሆንም በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ምክንያት በመቋረጡ አደጋ ለመከላከል ከፍተኛ ጥረት ካልተደረገ በገዳሟ ሙዚየምና ቅርስ ላይ የሚደርሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages