ለመስቀል ደመራ ቦታ ፍቃድ የሰጡ በህግ እንዲጠየቁ⁉ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Sunday, September 25, 2022

ለመስቀል ደመራ ቦታ ፍቃድ የሰጡ በህግ እንዲጠየቁ⁉

ለመስቀል ደመራ ቦታ ፍቃድ የሰጡ በህግ እንዲጠየቁ⁉ ለመስቀል ደመራ ቦታ ፍቃድ መስጠት "ሆን ብሎ በአንድ አካባቢ ሠላም ለማሳጣት የተደረገ በመሆኑ ይህንን የፈፀሙ አካላት በህግ አሰራር እንዲጠየቁ" ሀገር የሰራች፣ ሀገር ያቆየች፣ ሀገር የጠበቀች የምላት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በዘመነ ብልፅግና እንዲህ ናት። ጭራሽ ለመስቀል ደመራ ቦታ ፍቃድ የሰጡ ሰዎች በህግ እንዲጠየቁ ተብሏል። ለመስቀል ደመራ ቦታም በሀገር አቀፍ ደረጃ ማረጋገጫ አይሰጥም ይህንን ያደረጉ አካላትም ርምጃ ይወሰድባቸዋል። እኛ አፍዝዘው የሚያፈዝዙን የቤተክርስቲያን አካላት አሉን ሌሎች ደግሞ ጠንክረው እየሰሩ ነው። የቤተክርስቲያን አባቶች፣ የሀገረስብከትና ሌሎች የወረዳ ቤተክህነት ኃላፊዎች ዕዳ አለባችሁ። ታሪካችሁን አታበላሹ የዛሬ ዝምታችሁ የነገ ውድቀታችሁ ነው። መንግስት መዋቅሩን ተጠቅሞ ስራውን እየሰራ ነው። የአዲስ አበባው የመስቀል አደባባይ ጉዳይ ከመላው ሀገሪቱ የመስቀል አደባባይ ጋራ በቀጥታ የሚገናኝ ነው። ስለዚህ ለመፍትሄው እናንተ ቆርጣችሁ እስካልተነካችሁ ድረስ ነገ መንግስት ቤተክርስቲያን ይዘጋልኝ ወይም ከዚህ ቦታ ይነሳልኝ ማለቱ አይቀርም። ዝምታው እስከመቼ???? የደብዳቤው ሙሉ ቃል ጉዳዩ፦ በጎርቃ ቀበሌ በሁለቱ ቤተእምነቶች መሐል የተፈጠረ አለመግባባትን ይመለከታል፤ ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው የጎርታ ቀበሌ ሁለቱም ቤተ እምነቶች ከብዙ ዘመናት ታቻችሎና ተከባብረው የቆዩ ናቸው፡፡ ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ያለመግባባት በመፈጠሩ ምክንያት መንግስት የተለያዩ መድረኮችን አመቻችቶ ወደ መግባባት ለማምጣት ብዙ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ቢሆንም አሁን እየተስተዋለ ያለው ካለመግባባትም አለፎ ወደ ግጭት የሚመራ መሆኑን ከዞን እስከ ክልል ድረስ ያለው የመንግስት መዋቅር ቡድን ተዋቅሮ ማጣራት ተችሏል። በዚሁ ረገድ ለተገለፀው አለመግባባት መነሻ የሆነው ዘጎር ዳማ ቀበሌ ውስጥ ያለው የመስቀል ዳመራ ቦታ ለአንድ ኃይማኖት ዕውቅና መስጠቱ መሆኑን ቡድኑ አረጋግጧል። በዚህ መነሻ የዳውሮ ዞን ፀጥታ ም/ቤት በቀን 12/2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ፦ 1. ለመለያየት መንስኤ የሆነውን ይዞታ በመንግስት እጅ ሆኖ ቀበሌ ማዘጋጃ እንድያስተዳደረው እና የተለያዩ መንግስታዊና ህዝባዊ አገልግሎቶች በቦታው እንዲካሄድ፣ 2. በተለያዩ ጊዜ የተሰጡ ውሳኔዎችና ደብዳቤዎች ይህን አሰራርን ተከትለው እንዲታረሙ፤ 3. በመስከረም 16/1/2015 ዓ.ም የሚከበረው መስቀል ዳመራ በዓል ሀገራዊና አለምአቀፋዊ ይዘት ያለው በመሆኑ በቦታው እንዲከበር 4. የመስቀል ዳመራ ቦታ በሀገር አቀፍ ደረጃ የግሪን ካርድ የማይሰጥ ሆኖ ሳለ ሆን ብሎ በአንድ አካባቢ ሠላም ለማሳጣት የተደረገ በመሆኑ ይህንን የፈፀሙ አካላት በህግ አሰራር እንዲጠየቁ 5 የታርጫ ዙሪያ መንግስትም ይህንን ውሳኔ ተቀብሎ እንዲያስፈጽም በመወሰን ግልባጭ የተመዘገበላቸው አካላት እንዲያውቁ ጭምር እንገልፃለን፡፡ መስቀል ኃይላችን ነው

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages