ማኅበረ ቅዱሳን የመስቀል ደመራ በዓልን "መስቀልን በመስቀል አደባባይ” በሚል መሪ ቃል በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ላይ መሆኑ ተገለጸ‼ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Sunday, September 25, 2022

ማኅበረ ቅዱሳን የመስቀል ደመራ በዓልን "መስቀልን በመስቀል አደባባይ” በሚል መሪ ቃል በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ላይ መሆኑ ተገለጸ‼

ማኅበረ ቅዱሳን የመስቀል ደመራ በዓልን "መስቀልን በመስቀል አደባባይ” በሚል መሪ ቃል በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ላይ መሆኑ ተገለጸ‼ መስከረም 12 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ የማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማዕከል የ2015 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓልን “መስቀልን በመስቀል አደባባይ” በሚል መሪ ቃል በድምቀት ለማክበር ሰፊ ዝግጅቶችን በማድረግ ላይ መሆኑን የማዕከሉ መስቀል ኮሚቴ ትርኢት አስተባባሪ የሆኑት ዲ/ን ወርቁ ፈንታው ገልጸዋል፡፡ ለበዓሉም እንደ አዲስ አበባ ማዕከል 600 የሚሆኑ ዘማርያን እንዲሁም 300 የሚሆኑ በዜማ መሳሪያ የሚያጅቡ ዘማርያን ያሉ ሲሆን በአጠቃላይ ከአንድ ሺህ በላይ አባላት ዝግጅት እያደረጉ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ በመስቀል ደመራ በዓል ትርኢት ባለንበት ጊዜ የአንድ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ደም የሚፋሰሱበት ወቅት እንደመሆኑ ሁሉም ለሰላም ዋጋ እንዲሰጥ ታስቦ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ዘገባው የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ነው ።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages