"የመስቀል በዓልን ስናከብር በመስቀሉ የተከፈለልንን ዋጋ እያሰብንና ክርስቶስ በመንግስቱ እንዲያስበን በፀሎት እና በትሕትና ሊሆን ይገባል።" ብፁዕ አቡነ አብርሃም‼ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Sunday, September 25, 2022

"የመስቀል በዓልን ስናከብር በመስቀሉ የተከፈለልንን ዋጋ እያሰብንና ክርስቶስ በመንግስቱ እንዲያስበን በፀሎት እና በትሕትና ሊሆን ይገባል።" ብፁዕ አቡነ አብርሃም‼

"የመስቀል በዓልን ስናከብር በመስቀሉ የተከፈለልንን ዋጋ እያሰብንና ክርስቶስ በመንግስቱ እንዲያስበን በፀሎት እና በትሕትና ሊሆን ይገባል።" ብፁዕ አቡነ አብርሃም‼ መስከረም 13 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዛሬ መስከረም 13 ቀን 2015 ዓ.ም መጪውን የመስቀል ደመራ በዓል አከባበርን በማስመልከት ከጠቅላይ ቤተክህነት መልእክት አስተላልፈዋል። መልዕክታቸውን "ከጌታዬ ከእየሱስ ክርስቶስ መስቀል ውጭ ሌላ ትምህክት ከእኔ ይራቅ" በሚል አምላካዊ ቃል የጀመሩት ብፁዕነታቸው ሀይማኖታዊ ብሎም ሀገራዊ ሀብት የሆነውን ታላቁን የመስቀል በዓል ሀይማኖታዊና ባሕላዊ ዕሴቱን ጠብቆ ፍጹም ሰላማዊና ከስጋት ነፃ በሆነ መልኩ ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎቻችንን በሚገባ አጠናቀናል ብለዋል። መስቀል አደባባይና ደብረ ዕንቁ ልደታ ለማርያምን በተመለከተ የሚነሱ ችግሮችን ጠቅሰው ቤተ ክርስቲያን ጥያቄወቿን ከምዕመኗ ፊት ሆና መቼ ፣ለማን እና የት መጠየቅ እንዳለባት በሚገባ ታውቃለችና ምዕመኑ በበዓሉ ወቅት ሁከት ቀስቃሽ መልዕክቶችን የሚያስተላልፉ ጽሑፎችን በቲሸርቶች ላይም ሆነ በባነሮች ላይ ይዞ ከመገኘት እንዲቆጠቡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ከሰንደቅ ዓላማ ጋር በተያያዘ በየጊዜው የሚፈጠሩ ችግሮች እንዳይነሱ በዓሉን ለማክበር የሚሰባሰብ ማንኛውም ግለሰብ የቤተ ክርስቲያኗን ሰንደቅ አላማ እና በሕገ መንግሥቱ የተደነገገውን የፌደራሉን ሰንደቅ ዓላማ ብቻ በመያዝ የመንግሥት ሕጎችና መመሪያዎች ማክበርና በማስከበር ቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት አክባሪነቷን በተግባር ማሳየት ይገባል ብለዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ በአንዳንድ ግለሰቦች ስሕተቶች ቢፈጠሩ እንኳን የመንግስት የፀጥታ አካላትም የኃይል እርምጃ ከመውሰድ ሊቆጠቡ እንደሚገባ አሳስበዋል። ከመስቀል አደባባይ ውጪ በአድባራትና ገዳማት የሚከበሩ የመስቀል ደመራ በዓላትም በሰላማዊ መንገድ ተከብረው ማለፍ ይችሉ ዘንድ ሁሉም ህዝበ ክርስቲያን ፀጥታን በማክበርና በማስከበር ሀይማኖታዊ ግዴታውን መወጣት እንደሚገባ የገለጹት ብፁዕነታቸው የዓሉን ድባብ የሚያበላሹ እንቅስቃሴወችን መፍጠር ከቤተክርስቲያንና ከመንግሥት ጋር ብቻ ሳይሆን ጠቡ ከፈጣሪ ጋር መሆኑን በመገንዘብ እንዲህ ዓይነት እኩይ ተግባራትን ከመፈፀም በመታቀብ በዓሉን የሚያውኩ ሰርጎገቦችን መቆጣጠር ይገባል ብለዋል።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages