የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት አስተዳደር ጉባኤ ፵፩ንው የሰበካ መንፈሳዊ አጠቃላይ ጉባኤን መሠረት ያደረገ የሥራ ግምገማ አካሄደ!!
(ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ)
የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የአስተዳደር ጉባኤ ፵፩ ው የሰበካ መንፈስዊ አጠቃላይ ጉባኤን ሂደትን የተመለከተ ግምገማ አካሂዷል።
የጉባኤው አጠቃላይ ሂደት ሙሉ ገለፃ በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መጋቤ ሐዲስ ነቅዐ ጥበብ አባቡ የተደረገ ሲሆን የውይይቱ ተሳታፊዎች ሀገረ ስብከታችን ያገኘው ድል የሁላችን መተባበር ውጤት ነው፤ በቀጣይም የበለጠ ለመሥራት ስንቅ ሆኖናል ሲሉ ገልጸዋል።
በ፵፩ንው የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም ዐቀፍ ጉባኤ ላይ የተነሱ ሐሳቦችንና የተደረጉ ውይይቶችን እንደ ግብዓት በመጠቀም ለሀገረ ስብከቱ ቀጣይ ሥራዎች የዕቅዳችን አካል አድርገን መተግበር አለብን ብለዋል በስብሰባው የነበረውን አጠቃላይ ሂደትንም አድንቀዋል።
No comments:
Post a Comment