ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Thursday, October 27, 2022

ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን




ምሥጢር ማለት ድብቅ ለልብ ካልሆነ ለሌላ የማይነገር ማለት ነው። አስማምቶ አራቆ የሚተረጉመው ሊቅ አዋቂ እንደሱ የሰው አእምሮ አስቦና መርምሮ የማይደርስበት የአምላክ ህልውና የአምላክ ግብሩም ምሥጢር ይባላል። ቤተክርስትያን የመንፈስ ቅዱስን ፀጋ በእምነት ለሚቀርባት ሁሉ ታድላለች። ይህንንም ፀጋ የምታድልበት መሣሪያዎች ሚስጢራት ተብለው ይጠራሉ። እንዚህም ሚስጢራት ተብለው የሚጠሩበት ምክንያት አፈጻጸማቸው በዓይን የሚታይ ቢሆንም የሚያስገኝው ጥቅም ግን በስጋዊ ጥበብ ሊደረስበት የማይቻል የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ስለሆነ ነው። ይህም ከአእምሮ በላይ ነው።እንዲህም ሰለሆነ / ምስጢር ብላ በመሰየም ለልጆቿ ታስተምራለች። ይህም በራሱ መንፈ ጥበብ፣ መንፈሳዊ ዕውቀት ነው። ምስጢር መባሉ ስለ ፫ ነገር ነው፡፡
 
1.         ለአመነ እንጂ ላላመነ አይሰጥም።
 
2.     በዓይን የሚታየው በእጅ የሚዳሰሰው ግዙፍ ነገር ሲለወጥ አይታይም።
 
3.       መዕመናን በዚህ በሚታየው የማይታየውን የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ  ሲቀበሉ የሚፈጸመው በግብረ አምላካዊ ስለሆነ ሚስጥር ይባላል።


ሰባቱ ሚሥጢራተ ቤተክርስቲያን
 
1.         ምሥጢረ ጥምቀት
2.         ምሥጢረ ሜሮን
3.         ምሥጢረ ቁርባን
4.         ምሥጢረ ንሰሐ
5.         ምሥጢረ ቀንዲል
6.         ምሥጢረ ክህነት
7.         ምሥጢረ ተክሊል
 
የሚደገሙ ምሥጢራት
 
1.         ምሥጢረ ቁርባን
2.         ምሥጢረ ንሰሐ
3.         ምሥጢረ ቀንዲል
4.         ምሥጢረ ሜሮን(አንዳንዴ)

የማይደገሙ ምሥጢራት
 
1.         ምሥጢረ ጥምቀት
2.         ምሥጢረ ክህነት
3.         ምሥጢረ ተክሊል ናቸው።
 
 
የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ በእነዚህ በሰባቱ ምሥጢራት አይወሰንም በቤተክርስትያናችን ምስጢራት የሚባሉት ከላይ እንደገለጽነው ሰባት ናቸው። ለዚህም ማስረጃ የሚሆነን ጥበብ ቤቷን ሰራች ሰባቱንም ምሰሶዎቿን አቆመች ብሎ የተናገረው ቃል ነው(ምሳ 91)

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages