ከረውረና_ሚካኤል - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Wednesday, November 2, 2022

ከረውረና_ሚካኤል

 


ከረውረና ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በራያ ቆቦ ወረዳ 032 ቀበሌ ከረውረና ተብሎ በሚጠራ ቦታ ይገኛል።
ከረውረና በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በዓፄ ገላውዴዎስ ዘመነ መንግስት የተመሰረተው ይህ ቤተክርስትያን ጥንታዊ የብራና መፃህፍት እና ንዋየ ቅድሳት መገኛ ቦታ ነው፡፡
ቤተክርስትያኑ ካለው ጥንታዊነት እና ታሪካዊነት በአካባቢው ደጋግ አባቶች፣ ለአገራቸው ታሪክ የሰሩ ጀግኖች እና የብዙ የሐይማኖት አባቶች አፅም ማረፊያ ሆኖ ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ በተጨማሪም ቀደም ሲል ልክ እንደ አሁኑ በየ ቦታው ቤተክርስቲያን ባልነበረበት ግዜ ቆባ ጠጠራ ተብሎ የሚጠራው የራያ ማህበረሰብ ክፍል ህዝብ ለረዥም ዓመታት የቀብር ስነስርዓት ሲፈፅም የነበረው ረዥም የእግር ጉዞ በመጓዝ በዚሁ ታሪካዊ ቦታ በከረውረና ሚካኤል ቤተክርስቲያን ነበር።
የህወሓት ወራሪ ሃይል በዚህ ቦታ ለስምንት ወራት ያህል ትልቅ ምሽግ በቤተ ክርስቲያኑ ዙሪያ ሰርቶ ቆይቷል።
በዚህ ታሪካዊ ቦታ ለብዙ ቀናት ከባድ ውጊያ በመካሄዱ ምክንያት ቤተክርስቲያኑ ለጉዳት ተዳርጓል።
ስለሆነም ይህን ጥንታዊ እና ታሪካዊ ቤተክርስቲያን ወደነበረበት ለመመለስ ምእመናን እና የሃይማኖት አባቶች በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው። ስለዚህ የቅዱስ ሚካኤልን በረከት እናገኝ ዘንድ ካለን ላይ ቀንሰን ለቤተክርስቲያኑ እድሳት የሚሆን ገንዘብ በመለገስ እኛም የበረከቱ ተካፋይ እንሁን።
ለሁሉም ሰው እንዲዳረስ ሼር በማድረግ ተባበሩ።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages