የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ሁለተኛ መሠረታዊ መብቶችና ነጻነቶች ችሎት ቤተ ክርስቲያን እስከ ከመጋቢት 18 ቀን 2015 ዓ.ም በሕገ ወጡ ሹመት ላይ በተሳተፉ 26 ግለሰቦች ላይ ክስ እንድትመሠርት ውሳኔ ሰጥቷል።
በዛሬው ዕለት የቤተ ክርስቲያኗ የሕግ ክፍል በተሰጠ መግለጫ እንደተገለጸው ግለሰቦቹ ወደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት እንዳይገቡ፣ ንብረቷን እንዳይወስዱ፣ ዓርማና ስም እንዳይጠቀሙ የሚከለክለውም እግድ እስከ ተጠቀሰው ቀን ይቀጥላል ተብሏል።
ሕገ ወጡ ሹመት ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች እግድን እየተላለፉ እንደሚገኙ በመግለጽ የፍርድ ቤቱን ትእዛዝና እግድ መተላለፍ በወንጀል ተጠያቂ እንደሚያደርግ አስገንዝበዋል።
ይህንን እንዲያስፈጽሙ የታዘዙ ተቋማት በአለማስፈጸማቸው ተቋማቱንም ጭምር ተጠያቂ እንደሚያደርግ እና አፈጻጸሙ ፍርድ ቤቱ ነገ በሚሰጠው አቅጣጫ መሠረት እንደሚወሰን በመግለጫው ተጠቅሷል።
source: ©EOTC TV
ለተጨማሪ መረጃ የሀገረ ስብከቱ ማኅበራዊ ድረ-ገጾችን ይጎብኙ:-
1. ድረ-ገጽ:- www.addisababa.eotc.org.et
No comments:
Post a Comment