በሕማማት የሚጸለዩ ፀሎቶች ምን ምን ናቸው? - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Friday, April 14, 2023

በሕማማት የሚጸለዩ ፀሎቶች ምን ምን ናቸው?

 


1️⃣
በሕማማት የሚጸለዩ ፀሎቶች ምን ምን ናቸው?
2️⃣
በሕማማት ወቅት የሚሰሙ የምንላቸው ከሌላ ቋንቋ የተወሰዱ ቃላት ትርጉም
3️⃣
የ41 ስግደት ምን እየተባለ ነው የሚሰገድ? ና የመሳሰሉ ጥያቄ መልሶች፦። #ይነበብ
፨ +የሕማማት ጸሎት
በሕማማት የሚጸለየው በአብዛኛው ውዳሴ ማርያም እና መዝሙረ ዳዊት፤ የነቢያት ጸሎት ሲሆን የጌታን መከራ መስቀል የሚያነሱ መጻሕፍት ይጸለያሉ፡ ሕማማተ መስቀል፣ ድርሳነ ማሕየዊ የመሳሰሉ። መልክአ መልኮች፣ ድርሳናትና ገድላት የማይጸለዩት ዋናውን ጸሎት በጌታ ሕማማና መከራ መስቀል ለመስጠት ስለሆነ ነው። በአጠቃላይ በቤተክርስቲያን የሚነበበው ንባብ (ግብረ ሕማም) ዋናው የጸሎት ክፍል በመሆኑ ያንንም መሳተፍ ትልቁ ጸሎት ነው።
+ጥብጠባ፡-
በሰሙነ ሕማማት እለተ ዓርብ ስቅለቱ መታሰቢያ ነው፡ ምእመናኑ በሰሙነ ሕማማት የሰሩትን ይናዘዛሉ ካህናቱን በወይራ ቅጠል ትከሻቸውን እየጠበጠቡ ስግደት ያዟቸዋል፡፡ ጥብጠባው የተግሳፅ ምሳሌ ነው፡፡
ይህ በስቅለተ ቀን የሚፈጸም ስነ ስርዓት ሲሆን ጥብጣቤ ማለት ቸብ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ይህም የጌታን ግርፋት ያሳያል።፡ሕዝብ ክርስቲያኑ በእለተ ስቅለት ሲሰግድ ሲጸልይ ሲያነብ ከዋለ በኋላ ሰርሆተ ሕዝብ ይሆናል። አርብ ከ 11 ሰአት በኋላ ስግደት እንደሌለ ግብረ ሕማሙ "አልቦ ስግደት "ይላል።
፨ + በሕማማት ወቅት የሚሰሙ የምንላቸው ከሌላ ቋንቋ የተወሰዱ ቃላት ትርጉም:-
በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡
"ኪርያላይሶን"
ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ “ኪርዬ ኤሌይሶን” ነው፡፡ “ኪርያ” ማለት “እግዝእትነ” ማለት ሲሆን “ኪርዬ” ማለት ደግሞ “እግዚኦ”ማለት ነው፡፡ ሲጠራም “ኪርዬ ኤሌይሶን” መባል አለበት፡፡ ትርጉሙም “አቤቱ ማረን” ማለት ነው፡፡ “ኪርያላይሶን” የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው “ዬ”ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ “ኤ” በመሳሳባቸው በአማርኛ "ያ"ን ፈጥረው ነው፡፡
"ናይናን"
የቅብጥ(ጥንታዊው የግብጻውያን ) ቃል ሲሆን ትርጉሙ “መሐረነ፣ ማረን” ማለት ነው፡፡
"እብኖዲ"
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ “አምላክ” ማለት ነው፡፡ “እብኖዲ ናይናን” ሲልም “አምላክ ሆይ ማረን” ማለቱ ነው
"ታኦስ"
የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ “ጌታ፣ አምላክማለት ነው፡፡ “ታኦስ ናይናንማለትም “ጌታ ሆይ ማረን” ማለት ነው፡፡
"ማስያስ"
የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ “መሲሕ” ማለት ነው፡፡ “ማስያስ ናይናን” ሲልም “መሲሕ ሆይ ማረን” ማለት ነው
"ትስቡጣ"
ደግ (ቸር) ገዥ ማለት ሲሆን "ትስቡጣ ናይናን" ማለት ቸር ገዥ ማረን ማለት ነው።
"አምንስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ"
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ” ማለት ነው፡፡
"አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ"
የቅብጥ ቃል ሲሆን “ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን” ማለት ነው
"አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ"
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ፤የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን” ማለት ነው፡፡
፨ የ41 ስግደት ምን እየተባለ ነው የሚሰገድ?
አንድ ክርስቲያን #በፆም ጊዜ ከፀሎት በኋላ የጌታን መከራና
ለእኛ ያሳየውን ፍቅር እያሰበ ከሐጢያቱ ብዛት ከአምላኩ
ይቅርታ ያገኝ ዘንድ 41 ጊዜ እንዲህ እያለ ይስገድ፡-
12 ጊዜ ---- #እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
12 ጊዜ ---- #በእንተ እግዝዕትነ ማርያም መሐረነ
ክርስቶስ
12 ጊዜ ---- #ኪራላይሶን (አቤቱ ማረን)
5 ጊዜ ---- #ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት፣ አዴራ፣ ሮዳስ (አምስቱ
የጌታ ችንካሮች)

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages