ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ)
በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ስር የሚገኘው የመካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን 2.1 ቢሊየን ብር የራስ- አገዝ ሁለገብ ህንፃ የግንባታ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጧል።
የመሰረት ድንጋይ ያስቀመጡት የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ በኵረ ትጉሃን ዘርዓ ዳዊት ኃይሉ እና የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ባዩህ አቡሃይ በጋራ በመሆን ነው ።
የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ በኵረ ትጉሃን ዘርዓ ዳዊት ኃይሉ እንደገለጹት የሚገነባው ህንፃ መካነ ሰብሐት ልደታ ቤተክርስቲያን ቦታ ላይ ይሁን እንጂ የሚገነባው ግን ለአጠቅላይ የጎንደር ህዝብ አገልግሎት ነው ብለዋል።
የሚገነባው ህንፃ ዓመታትን ማስቆጠር የለበትም ያሉት በኵረ ትጉሃን ዘርዓ ዳዊት በኢትዮጵያ ውሰጥና በመላው ዓለም ያሉ የማኅበረሰብ አንቂዎች እግዚአብሔር በሰጣቸው ጸጋ ተጠቅመው እንዲደግፉና እንዲያስተባብሩ በታሪካዊቷ ጎንደር ሀገረ ስብከት ስም ጥሪ አስተላፈዋል ።
No comments:
Post a Comment