ጾመ ሐዋርያት - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Friday, June 30, 2023

ጾመ ሐዋርያት
በወርኃ ሰኔ የሚጾም በመሆኑ ይህ ጾም በተለምዶ የሰኔ ጾም በመባል ይታወቃል፡፡ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ለስብከተ ወንጌል ከመሰማራታቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው፡፡ ጾመ ሐዋርያትን ለመጀመሪያ ጊዜ የጾሙት ቅዱሳን ሐዋርያት ሲሆኑ የጾሙበትም ዋና ምክንያት በሃምሳኛው ቀን ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ስለተቀበሉና እግዚአብሔር ስላደረገላቸው መልካም ነገር ለማዘከር ነው፡፡
ጾመ ሐዋርያት በዓለ ጰራቅሊጦስ በመጀመሪያው ሰኞ ይውላል፡፡ ጌታችን አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ደቀ መዛሙርቱን ይህን ጾም እንደሚጾሙት እንዲህ ተናግሮ ነበር፡፡ ‹‹በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው። ‹‹እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ እንጾማለን፥ ደቀ መዛሙርትህስ ለምን አይጾሙም? አሉት፡፡›› (ማቴ.፱፥፲፬) ደቀ መዛሙርቱ ይህንን በጠየቁት ጊዜ ጌታችን እንዲህ ብሎ መልሶላቸው ነበር፡፡ ‹‹ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ የሙሽራው ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ አይችሉም፤ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ ያንጊዜም ይጾማሉ፡፡›› (ማቴ.፱፥፲፭)
በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ ያደረው ጸጋ መንፈስ ቅዱስና ሀብተ መንፈስ ቅዱስ በእኛም ላይ እንዲያድር፣ ከቅዱሳን ሐዋርያቱ በረከት እንድንሳተፍ፣ አገልግሎታችን በስኬት እንዲቃና እና ወርኃ ክረምቱ በሰላም ያልፍልን ዘንድ ጾመ ሐዋርያትን መጾም አስፈላጊ ነው፡፡ ከጸሎትና ምጽዋትን መንፈሳዊ እድገትን በጾም አስምረን ከራሳችን እና ከእግዚአብሔር አምላካችን ጋር የምንታረቅበት እንዲሆንልን የቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት በረከትና ጸሎትም አይለየን፡፡
የአምላካችን እግዚአብሔር ቸርነት፣ የቅድስት ድንግል ማርያም እና የቅዱሳን ሐዋርያት አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፤ አሜን!

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages