በዝቋላ ገዳም በታጣቂዎቹ የተገደሉት አባቶች - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Friday, February 23, 2024

በዝቋላ ገዳም በታጣቂዎቹ የተገደሉት አባቶች

 "4 ተገድለው 1 ጠፍተዋል፤ ገዳሙን እና እኛን ለማዳን እነሱ ተሰው፤ የእኛንም በደል እነሱ ከፈሉ"



የደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አባቶች
++++++++++++++++++++++++++++++
የገዳሙን መጋቤ እና ዋና ጸሐፊ ጨምሮ የደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም 4 መነኮሳት በታጣቂ ኃይሎች መገደላቸውን ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን የደረሰው መረጃ ያመላክታል።
ከገዳሙ በስልክ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው የካቲት 12/2016 ዓ.ም የታጠቁ ሰዎች ወደ ገዳሙ በመግባት ሁለት መነኮሳት መውሰዳቸውን እነሱ ይመለሳሉ ብለው ሲጠብቁ በማግስቱ የካቲት 13/2016 ዓ.ም ታጣቂዎቹ ድጋሚ መጥተው ለውይይት እንፈልጋችኋለን በማለት 3 መነኮሳትን ወደ "ጂዳ ተክለ ሃይማኖት" ወስደዋል ብለዋል።
መነኮሳቱ "ለውይይት" ሲባሉም "ችግር የለውም እናንተ አባቶች እዚህ ቆዩ እኛ አነጋግረናቸው እንመጣለን፤ ተረጋጉ" ብለው ታጣቂዎቹን ተከትለው ከገዳሙ ሂደዋል።
ቀኑን ሙሉ ስልካቸው ክፍት እንደነበረ አመሻሽ ማግኘት ባለመቻላቸው ተጨንቀው የአካባቢውን ምእመናን ሲያጠያይቁ 4ቱ መገደላቸውን እንደነገሯቸው አንደኛው አባት ግን ተለቀዋል ቢባልም እስካሁን ያሉበት እንዳልታወቀ አባቶቹ ለጣቢያችን በእንባ ተናግረዋል።
በታጣቂዎቹ የተገደሉት አባቶች
፩ አባ ተክለ ማርያም አሥራት (የገዳሙ መጋቤ)
፪ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን (የገዳሙ ዋና ጸሐፊ)
፫ አባ ገብረ ማርያም አበበ (ቀዳሽ ካህን፣የመጽሐፍ መምህርና የገዳሙ አስተዳደር አባል)
፬ ባህታዊ ኃ/ማርያም ስሜ (የገዳሙ የአስተዳደር አባል)
ሲሆኑ
እስካሁን ያሉበት ያልታወቀው ደግሞ አባ ኪዳነ ማርያም ገ/ሰንበት ናቸው።
ገዳሙ በተደጋጋሚ በታጠቁ ሰዎች ዐይነተ ብዙ ጥቃት እንደሚደርስበት ነገር ግን መፍትሔ እንዳላገኙ በመግለጽ የአሁኑ ጥቃት ግን በቃላት የማይገለጽ ነው ብለዋል።
"ገዳሙን እና እኛን ለማዳን እነሱ ተሰው፤ የእኛንም በደል እነሱ ከፈሉ፤ ጻድቁን አገልግዬ እዚሁ አርፋለሁ ሲሉ ደመ ከልብ ሆነው ዐፈራቸውንም ሳይቀምሱ ቀርተዋል" ሲሉም መረጃ የሰጡን አባቶች በከፍተኛ ሐዘን ገልጸዋል።
ምንጭ፤ ማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages