መጋቤ ካህናት ቆሞስ አባ ሃብተ ጊዮርጊስ አስራት - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Tuesday, February 27, 2024

መጋቤ ካህናት ቆሞስ አባ ሃብተ ጊዮርጊስ አስራት



 "መሞታቸው ብቻ ሳይሆን አሟሟታቸውም ዘግናኝ ነበረ አስከሬናቸው እንኳ ተለቃቅሞ እንዲቀበር ነው የሆነው።"

መጋቤ ካህናት ቆሞስ አባ ሃብተ ጊዮርጊስ አስራት
የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ አዲስ አበባ)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የገዳማት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ በግፍ በተገደሉት የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አባቶች ዙሪያ ከተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ጋር ቆይታ አድርገዋል።
የመምሪያው ዋና ኃላፊ የሆኑት መጋቤ ካህናት ቆሞስ አባ ሃብተ ጊዮርጊስ ዓሥራት እንደተናገሩት ከጥቃቱ በፊትም በተደጋጋሚ የማስፈራሪያ ዛቻና ገዳሙን ለቃችሁ ውጡ የሚባሉ መልእክቶች ይደርሱ እንደነበር ገልጸዋል።
ከዚህ ክስተት ቀደም ብሎ የገዳሙ መጠበቂያ መሣሪያና የመናንያኑ እህል በኃይል ተወስዷል ያሉ ሲሆን የሚመለከተው አካል ለጉዳዩ ትኩረት ካልሰጠ ወደ ፊትም ከዚህ ያልተናነሰ ወንጀል በገዳሙ ሊፈጸም የማይችልበት ምክንያት አይኖርም ብለዋል።
ምንም እንኳ ለቤተክርስቲያን አባቶች መደብደብ መሰደድና መገደል የነበረ ቢሆንም የአሁኑ ግን መሞታቸው ብቻ ሳይሆን አሟሟታቸውም ዘግናኝ ነበረ አስከሬናቸው እንኳ ተለቃቅሞ እንዲቀበር ነው የሆነው ሲሉ ተናግረዋል።
ገዳማትን መጠበቅ የቤተክርስቲያኗ ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የመንግሥትም ኃላፊነት ነው መንግሥት ከፌደራል እስከ ክልል ባሉት የጸጥታ መዋቅሮቹ ገዳማትን እንደማንኛውም ተቋም ሊጠብቅ ይገባል በማለት አክለዋል።
በመጨረሻም በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ያሉ ምእመናን በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙት የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም መናንያን በገዳሙ ሕጋዊ አካውንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000011282222 (የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም) ድጋፍ እናድርግ በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል።
ምንጭ፤ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages