#መንበረ_ጸባኦት_ቅድስት_ሥላሴ_ካቴድራል! - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Monday, May 18, 2020

#መንበረ_ጸባኦት_ቅድስት_ሥላሴ_ካቴድራል!


መቼና በማን ተመሰረተ?
#ከወሎ ወደ በአዲስ አበባ የሄደው ታቦት ረዘም ያለ የአመሰራረት እድሜ ካላቸው አድባራት መሀከል አንዱ ነው። ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በሸዋ ንጉስ ከሆኑ በ25ኛ ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ ተብለው ዘውድ ከደፉ በ2ኛ አመታቸው በእለተ ሰንበት ታህሳስ ሰባት ቀን 1883ዓ·ም በዓል አድርገው አሁን ካቴድራሉ ካለበት ቦታ አነስተኛ የሳር ጎጆ መቃኞን በማሰራት ታቦተ ሥላሴን አስገቡ።
ታቦቱ የመጣው ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት ከመናገሻ አውራጃ ከአዲስ አለም ፎየታ ሥላሴ ነው ነገር ግን አስቀድሞ #በወሎ/ቤተ አማራ/ መካነ ሥላሴ ነበር ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ‘ኢትዮጵያ፡- ነጠላ እና ጋቢ’ በሚል ጽሑፉ ላይ የቅድስት ሥላሴ ታቦት የመጣው በግራኝ ጊዜ ከፈረሰው ከወሎው #መካነ_ሥላሴ እንደሆነና ከዚያ ተወስዶ ወግዳ መኖሩን፣ ከወግዳ ራስ ጎበና አምጥተው ሸዋ አዲስ ዓለም ፍየታ እንዳኖሩት ከዚያም ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክደግሞ አዲስ አበባ አራት ኪሎ እንዳመጡት ይዘግባል፡፡
በእልቅና የአንኮበሩ ሚካኤል አስተዳዳሪ የነበሩት አለቃ ገብረ ክርስቶስ እንዲጠብቁት ተደረገ የደብሩ የማእረግ ስሙ ደብረ ፅጌ ነበር በ1885 መካነ ሥላሴ ተባለና አነስተኛ የሆነው ከስር የምታዯት ቤተክርስቲያን ተሰራች ስዕሉንም የተለያዩ ባለሙያወች ሳሉት
ለመተዳደሪያም አፄ ምኒልክ 100 ጋሻ መሬት ሰጡት።
ለረጅም አመታት በሳር ጎጆ በተሰራ ቤተ መቅደስ ሲገለገል ከቆየ በኋላ በ1924 ዓ·ም በቀዳማዊ አፄ ሐይለስላሴ አማካኝነት አዲስ ቤተ መቅደስ መሰራት ተጀመረ የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሕንፃ የመሠረት ድንጋይ ታኅሣሥ 15 ቀን 1924 ዓ/ም ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሲያስቀምጡ የእስክንድርያ ኮፕት ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ዮሐንስ እና የሀገር ጳጳሳትም በተገኙበት ልዩ ጸሎት
እና ቡራኬ ተሠጥቶ ተመረቀ። ቤተ ክርስቲያኑ ሲታነጽ ቀዳሚ ዓላማው ለአገራቸው ነፃነት ሲታገሉ ለተሰው አርበኞች #መካነ_መቃብር እንዲሆን ታቅዶ ነው። የደብሩም ስም
የሚያመላክተው ይኼንኑ እንደሆነ ነው። ታላቁ ምሁር ዓለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ
መንበር የሚለውን ቃል በቁሙ ወንበር፣ መኖሪያ፣ ማረፊያ፣ መቀመጫ፣
ዙፋን፣ አትሮንስ፣ ለመቀመጫ የተለየ ከፍ ያለ ቦታ እንደሆነ ሲገልጹ፤ ጸባኦት ደግሞ ሰራዊት፣ ጭፍራ፤ የጦር ሕዝብ፤ ብዙ ወታደር፤ ያርበኛ ጉባኤ፤ የዠግና ማኅበር እንደሆነ ያብራራሉ።
ስራው ብዙም ሳይቆይ ጣሊያን ሀገራችንን በመውረሩ ለአምስት አመታት ተቋርጦ ቆይቶ ንጉሱ ወደ ሀገርቤት ከተመለሱ ከሁለት አመታት በኋላ በ1935 ዓ·ም ከእንደገና መሰራት ተጀምሮ ከአንድ አመት በሗላ ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ ምዕመኑ እየበረከተ ቤተ መቅደሱ አልበቃ ሲል በ1939 ዓ·ም የቅጥያ ስረሳ ተጀምሮ ተጠናቀቀ።
አሁንም ግን የመንበረ ጸባኦት ምዕመን እጅግ በመብዛቱ ከ1957—1960 ባለው ጊዜ ውስጥ አሁን የምናየው ግዙፉ ካቴድራል ታነጸና (ጥር 7) ቀን በደማቅ ሁኔት ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ።እነሆ
ይህ ከሆነ ዛሬ 52 አመት ሞላው።
በካቴድራሉ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ንጉሠ ነገሥቱቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ
የሚከተለውን ዐዋጅ አስነገሩ።
“እጅግ ከፍ ያለው የዓለም ሁሉ ገዥ እግዚአብሔር ለኢትዮጵያና ለሕዝባችን ለእናና ለአርበኞቻችን በየጊዜው ካደረገልን ፣ ወደፊትም ከሚያደርግልን ከታላላቅ ችሮታ ከሚቆጠሩት ሥራዎች አንደኛውን ዛሬ ስለፈጸመልን ልናመሰግነው ይገባናል።
ለንጉሠ ነገሥት ቤተ ዘመዳችን ደንበና የዕረፍት ሥፍራ እንዲሆን በመሠረትነው
የክብር ቦታ በሥራቸውና
በመሥዋዕትነታቸው ውለታቸውን ልንመልስላቸው የተገባቸው አገልጋዮች ደንበኛ የርስት ተካፋይ እንዲሆኑ ፈቀድን። የሚገባቸውን ፈጽመው ማረፋቸውን ስንመሰክርላቸው በዐጽማቸው ፊት የክብር ሰላምታ እንሰጣለን።”
በዚሁም ሥነ ሥርዓት ላይ ለልዩ ልዩ የጦር ሠራዊት መለዮ የሚሆነው ሰንደቅ
ዓላማ በዚህ ካቴድራል እንዲውለበለብ ፈቀዱ። ይህም በጦር ሜዳ ለወደቁት
አርበኞች፣ ለሕያዋኑ ጦር ሠራዊት መታሰቢያ እና የጦሩ መለያ የሚሆን ነው።
1ኛ/ ከ1927 ዓ/ም እስከ 1933 ዓ/ም የጦር ሠራዊታችን ሰንደቅ ዓላማ
2ኛ/ ለክብር ዘበኛ ሰንደቅ ዓላማ
3ኛ/ ለቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የጦር ተማሪ ቤት ሰንደቅ ዓላማ
4ኛ/ ከ1927 ዓ/ም ጀምሮ እስከ1933 ዓ/ም ድረስ በጦር ሜዳ ለወደቁ ጀግኖች
ሰንደቅ ዓላማ።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages