ሚያዝያ ፲፬ ግጻዌ (ዐቢይ ጾም/ ኒቆድሞስ ፭ኛ ቀን) - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Friday, April 23, 2021

ሚያዝያ ፲፬ ግጻዌ (ዐቢይ ጾም/ ኒቆድሞስ ፭ኛ ቀን)

ሚያዝያ ፲፬ ግጻዌ (ዐቢይ ጾም/ ኒቆድሞስ ፭ኛ ቀን)
-------------------------------------------------------------- ስንክሳር:- ሚያዝያ ፲፬ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት አባ መክሲሞስ ሊቀ ጳጳሳት ወር በገባ በ፲፬ የሚታሰቡ በዓላት አቡነ አረጋዊ ና ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ፣ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ፣ ቅዱስ ሙሴ (የእግዚአብሔር ሰው)፣ አባ ስምዖን ገዳማዊ፣ አባ ዮሐንስ ጻድቅ፣ እናታችን ቅድስት ነሣሒት ____________ አባ መክሲሞስ _____________ በዚች ዕለት ሚያዝያ ፲፬ በዚች ቀን በእስክንድርያ ለተሾሙ ሊቃነ ጳጳሳት ዐሥራ አምስተኛ የሆነ የከበረ አባት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ መክሲሞስ አረፈ። ይህም አባት መንፈሳዊና በሥራው ሁሉ እግዚአብሔርን የሚፈራ ነው። እርሱም ከእስክንድርያ ሰዎች ወገን ነው ወላጆቹም ሃይማኖታቸው የቀና ነበረ የዮናናውያንንም ጽሕፈትና መጽሐፋቸውን ጥበባቸውንም ሁሉ ተምሮ ፍጹም አዋቂና አስተዋይ ሆነ በዮናኒ ቋንቋ። ከዚህም በኋላ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ልዑል እግዚአብሔር የሠራውን ሕግና ሥርዓት ተማረ። አባት ያሮክላም ዲቁና በእስክንድርያ ሾመው ከዚያም በኋላ ዲዮናስዮስ ቅስና ሾመው በተሾመባት ሁሉ ላይ ተጠምዶ የሚአገለግልና የሚጋደል ሆነ። አባ ዲዮናስዮስም በአረፈ ጊዜ አዋቂዎች ኤጲስቆጶሳትና ካህናት ማኅበሩም ሁሉ መረጡት በእግዚአብሔርም ፈቃድ በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበር ላይ ሊቀ ጳጳሳት አድርገው ሾሙት። ዲዮናስዮስም ስለ ጳውሎስ ሳምሳጢ በአንጾኪያ ከተማ የተጀመረው የኤጲስቆጶሳት ማኅበር ጉባኤ ተጀመሮ ሳይፈጸም አረፈ። ይህም አባት መክሲሞስ በተሾመበት ወንበር በተቀመጠ ጊዜ በማኅበሩ ጉባኤ ስለ ተወሰነውና ከሀዲው ጳውሎስ ሳምሳጢን እንደአወገዙት ከጉባኤው ሹማምንት መልእክቶች ወደርሱ ደረሱ። በትምርቱ ያመኑትንም መልእክቶቹንም ካህናቱ በአንድነት በተሰበሰቡበት አነበበው። ከዚያም በኋላ ዳግመኛ ከራሱ መልአክቶችን ጽፎ የጳውሎስ ሳምሳጢን ስሕተት ያርቅ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንዲጸልዩና እንዲማልዱ እያዘዘ ወደ ግብጽ አገሮች ሁሉ ወደ ኢትዮጵያና ወደ ኖባ አገር ላካቸው። የክብር ባለቤት ጌታችን ልመናቸውን ተቀበለ ይህም ከሀዲ ከጥቂት ቀኖች በቀር አልኖረም በፍጥነት አጠፋው እንጂ የረከሰች ሃይማኖትንም ከዓለም አስወገደ አራቀ። በዚህም አባት ዘመን ከምሥራቅ አገር ማኒ የሚባል ራሱን የዕውነት መንፈስ ጰራቅሊጦስን ያደረገና ክፉ ስሕተትን የሳተ ሰው ተገለጠ። ወደ ሶርያ ምድርም ደረሰ አርኬላዎስ የሚባል ኤጲስቆጶስም ከእርሱ ጋራ ተከራከረ ስሕተቱንም ገላልጦበት አሳፍሮ ከአገሩ አሳደደው። ከዚያም ተመልሶ ወደ ፋርስ ሔደ ራሱንም ነቢይ አደረገ የፋርስ ንጉሥ ብህራምም ይዞ ከሁለት ሠነጠቀው። ተከታዮቹ የሆኑ ሁለት መቶ ሰዎችን ዘቅዝቆ እስከ ወገባቸው በምድር ውስጥ ተከላቸው እነሆ ከሰው አትክልትን ተከልሁ አለ። ይህም አባት መንጋውን በመጠበቅ ሲጋደልና በቀናች ሃይማኖትም ሲያጸናቸው ኖረ ከመናፍቃንና ከከሀድያን ችግር እስከ አረፈባት ቀን ድረስ በድርሳናትና በተግሣጻት ጠብቆ አዳናቸው። በማርቆስም ወንበር ፲፮ ዓመት ኑሮ በሰላም አረፈ። በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። ሚያዝያ፣ ፲፬ ግጻዌ ____________________ ስንክሳር:- መክሲሞስ ሊቀ ጳጳሳት ዘእስክንድሪያ፣ ዘእውኅዞ ለማኒ ዘሰማየ ርእሶ መንፈስ ቅዱስ። መልእክተ ጳውሎስ ፪ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ም. ፪ ቊ. ፩- ፲፪ _________________________________ መልእክተ ዮሐንስ ፩ኛ የዮሐንስ መልእክት ም. ፬ ቊ. ፩ - ፱ _______________________________ ግብረ ሐዋርያት የሐዋርያት ሥራ ም. ፳ ቊ. ፴፭ - ፴፰ _____________________________ ምስባክ ዘቅዳሴ ______________ ወኢዐቀቡ ስምዖ ተመይጡ ወዐለዉ ከመ አበዊሆሙ ወኮኑ ከመ ቀሥት ጠዋይ መዝሙረ ዳዊት ም. ፸፰ ቊ. ፶፮ - ፶፯ ______________________________ ፶፮ ነገር ግን ልዑል እግዚአብሔርን ፈተኑት አስቈጡትም፥ ምስክሩንም አልጠበቁም፤ ፶፯ ተመለሱም እንደ አባቶቻቸውም ከዱ፤ እንደ ጠማማ ቀስትም ተገለበጡ፤ ምስባክ ዘቅዳሴ ተለዋጭ _____________________ ወበመንፈስ እዚዝ አጽንዐኒ ከመ እምሀሮሙ ለኃጥኣን ፍኖተከ ወረሲዓን ይትመየጡ ኀቤከ መዝሙረ ዳዊት ም. ፶፩ ቊ. ፲፪ - ፲፫ ______________________________ ፲፪ የማዳንህን ደስታ ስጠኝ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ። ፲፫ ለሕግ ተላላፎች መንገድህን አስተምራለሁ፥ ኃጢአተኞችም ወደ አንተ ይመለሳሉ። ወንጌል ዘቅዳሴ የማቴዎስ ወንጌል ም. ፳፬ ቊ. ፰ - ፶፩ _______________________________ ወንጌል ዘቅዳሴ ተለዋጭ የማቴዎስ ወንጌል ም. ፲፪ ቊ. ፳፪ - ፴፰ ________________________________ የዕለቱ ቅዳሴ ___________ ዘሰለስቱ ምዕት (ግሩም) ወስብሐት ለእግዚአብሔር::

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages