ዶግማ ፣ ሥርዓት ፣ ቀኖና (ከመምህር ዘለዓለም ገጽ የተወሰደ)
ብዙ ጊዜ ስለዶግማና ቀኖና እንዲሁም ሥርዓት ለሚነሱ ጥያቄዎች የሚሰጡ መልሶች የተለመዱ ናቸው:: ዶግማ ማለት የማይበረዝ የማይከለስ የማይሻሻል ማለት ነው ሥርዓትና ቀኖና ግን እንደአስፈላጊነቱ በቅዱስ ሲኖዶደስ ማሻሻያ ሊደረግለት ይችላል የሚል ነው ለዶግማ የምንሰጠው ትርጉም እንዳለ ሁኖ ሥርዓትና ቀኖናም የማይሻሻሉ መሆናቸውን መረዳት ያለብን ይመስለኛል::
በመጀመሪያ ደረጃ ዶግማ ሥርዓት ቀኖና የምንለው ምን እንደሆነ ለያይቶ ማየት ያስፈልጋል::
ሠለስቱ ምዕት
ዶግማ ስንል የማይሻሻሉ ጾምን ሃይማኖትን የመሳሰሉትን
ሥርዓት ስንል በጾም ወቅት ሥጋ ወተት ዕንቁላል የመሳሰሉትን ከመመገብ መከልከልን
ቀኖና ስንል ከ እስከ ተብለው የተቀመጡትን የጾም ሰዓታትና ቀናትን ነው፡፡ እነዚህ ሦስቱ ዶግማና ሥርዓት እንዲሁም ቀኖና የተያያዙ ናቸው ዶግማ ባለበት ሥርዓትና ቀኖና አሉ ቀኖና ሥርዓትም ሊኖሩ የሚችሉት ዶግማ ሲኖር ነው፡፡ ለምሳሌ ጾም ዶግማ ነው ሥጋ ወተት እንቁላል የመሳሰሉትን የጥሉላት ምግቦች (ጥሉላት ማለት ሰውነትን የሚያለመልሙ ማለት ነው )በጾም ወቅት ከመመገብ መከልከል የጾሙ(የዶግማው) ማስፈጸሚያ ሥርዓት ነው::
በጾም ወቅት ከምሽቱ ሦስት ሰዓት እስከ ቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ያሉት ከምግብ የምንከለከልባቸው አሥራ ስምንት ሰዓታት ቀኖና ይባላሉ ቀኖና የምንለው በአንድ የጾም ወራት ያለውን የጾሙንና የቀኑን እንዲሁም የሰዓቱን ርዝመት ነው መጻሕፍት ኃዳሪን በማኅደር ማኅደርን በኃዳሪ፣ ስሙ ያልታወቀን ሰው በሀገሩ ኢትዮጵዊ አሜሪካዊ ጀርመናዊ ብሎ እንደመጥራት ቀኖናና ሥርዓትም የሕጉ ማስፈጸሚያ ስለሆኑ ሥርዓቱንም ሕጉንም ቀኖና እያሉ ቢጠሩትም የቀኖና ተግባር ግን የጾም የሱባኤ የንስሓ ርዝመት መለኪያ ነው::
በሌላም አነጋገር አንድ ሰው ኀጢአት ሠርቶ ንስሓ ሲገባ ቀኖና ተቀበለ ይባላል:: ከዚህ አባባል እንደምንረዳው ቀኖና ብለን የምንገልጸው እንደኀጢአቱ ብዛትና ማነስ የሚሰጠውን የጾም የቀናት መጠን ነው በንስሓ አባት የሚሰጠው የንስሓ ጾም እንደኀጢአታችን ክብደትና መቅለል በንስሓ አባት የሚወሰን ሁኖ እነዚህን የሰባቱን አጽዋማት ቀናትና ሰዓታት ግን ረዘሙ ብሎ ማሳጠር አጠሩ ብሎ ማስረዘም አይቻልም ቀኖናም ሆነ ሥርዓት አይሻሻሉምና ፡፡
ከዚህ ላይ ዶግማ ብለን በምንጠራው በጾም ውስጥ ቀኖናና ሥርዓት አብረው እንደተካተቱ ማስተዋል ያስፈልጋል::ስለዚህ ሥርዓት ቀኖና ይሻሻላል ማለት በጾም ወቅት እንዳንበላቸው የተከለከሉትን የእንስሳት ውጤቶች እንድንበላ ሥርዓቱ ቢሻሻል ለመብላት መዘጋጀት ፣አርባ ቀን የጾመውን የጌታን ጾም በዝቷልና ሰላሳ ቀን ይሁን ተብሎ ቀኖናው ቢሻሻል ፈቃደኛ ሁኖ መቀበል ማለት ነውና ይህንም የሚቀበል አዕምሮ ሊኖረን አይገባምና ሥርዓትም ሆነ ቀኖና አይሻሻሉም::
ክፍል ሁለት ይቀጥላል
የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉም ይዳረስልን ዘንድ ጸልዩልን ፪ኛ ተሰሎንቄ ፫ ÷ ፩
Post Top Ad
Thursday, June 3, 2021
Tags
# ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
Share This
About አትሮንስ ሚዲያ
ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
Labels:
ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Post Bottom Ad
Author Details
Templatesyard is a blogger resources site is a provider of high quality blogger template with premium looking layout and robust design. The main mission of templatesyard is to provide the best quality blogger templates which are professionally designed and perfectlly seo optimized to deliver best result for your blog.
No comments:
Post a Comment